የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ማኔጅመንት በባንኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከባለአክስዮኖች ጋር ምክክር አካሄደ።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው እና የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ ዳንኤል ተከስተን ጨምሮ ሌሎች የቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ. ም በካፒታል ሆቴል አጠቃላይ የባንኩ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል።
በምክክር መድረኩ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ያሳየው አፈፃፀም አበረታች እና ከቀዳሚዎቹ ዓመታት በእጅጉ የተሻለ እንደሆነ ተመልክቷል።
ባንኩ ከበርካታ የንግድ ተቋማት እና የብድርና ቁጠባ የህብረት ስራ ማሕበራት ጋር አብሮ ለመስራት ያስቻለው የአጋርነት ስምምነት ተፈራርሞ ወደ ስራ መግባቱ፣ ከአጋር ድርጅቶች እና ወደ ስራ ካስገባቸው አዳዲስ አገልግሎቶች ጋር የሲስተም ኢንተግሬሽን ስራዎች መስራቱ አበረታች እንደነበር ተመልክቷል።
ተደራሽነትን ለማስፋት የተሰራው ስራ የተቀማጭ ሐብት የማሰባሰብ ጥረቱን ስኬታማ እንዳደረገው እና ከአቻ ባንኮች በተሻለ ደረጃ ለመገኘት ያስቻለው መሆን ተገልጿል።
በምክክር መድረኩ የቀረበው አጭር ሪፖርት እንዳመለከተው በተጠናቀቀው የበጀት አመት የባንኩ አፈፃፀም በሁሉም የመመዘኛ መስፈርቶች ብቁ እና ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ላይ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የተገለፀ ሲሆን፣ መንግስት እያወጣቸው ካሉ ፖሊሲዎች ጋር አብሮ መጓዝ እንዲያስችለው የካፒታል አቅም ማጎልበት ወሳኝ በመሆኑ ባለአክሰዮኖች ተጨማሪ አዳዲስ አክሲዮኖችን እንዲገዙ እና ሌሎች ደንበኞችንም አክስዮን ማስገዛት በሚችሉበት መንገድ ላይ ውይይት በማድረግ በተቻለ ፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጧል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!