የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት ተጠናቀቀ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በስካይ ላይት ሆቴል አካሂዷል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በተገባደደው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 940.7 ሚሊዮን ትርፍ አስመዘገበ ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ26 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት እስከ ተገባደደው በጀት ዓመት ድረስ ብር 43.1 ቢሊዮን ደርሷል። አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ደግሞ ብር 35.6 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ30 በመቶ ዕድገት እና ጠቅላላ የአስቀማጭ ደንበኞች ቁጥር 2 ሚሊዮን ደርሷል ይህም ካለፈው የበጀት ዓመት በ19 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
የባንኩ የብድርና ቅድሚያ ክፍያዎች መጠን ብር 30.4 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። እንዲሁም ባንኩ ብር 5.6 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ የሰበሰበ ሲሆን፤ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የ33 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ላይ ባንኩ 13,889 በላይ ባለአክሲዮኖች፣ 6,365 በላይ ሰራተኞች እና 306 ቅርንጫፎች አሉት።
በተጨማሪም ብዙ ወጪዎችን በማይጠይቅ መልኩ አገልግሎቶችን በዲጅታል ባንኪንግ በመታገዝ እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ የወኪል እና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እንደ ቅደም ተከተላቸው 998 ሺ ማድረስ ተችሏል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.
የስኬትዎ አጋር!!
#AGM2024