በአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ መንደር በደረሰ የእሳት አደጋ ስድስት ብሎኮች በዉሰጣቸዉ ከያዙት ንብረት ጋር ወደመ
ለሀሙስ አጥቢያ ሌሊት 7 ሰአት ከ45 በአራዳ ክፍለ -ከተማ ወረዳ 2 ራስ እምሩ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ባለ ኢንደስትሪ መንደር ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ስድስት ብሎኮች በዉሰጣቸዉ ከያዙት ንብረት ጋር ሙሉ በሙሉ መቃጠሉን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 14 የአደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪና ሁለት የዉሃ ቦቴ እንደዚሁም 96 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አራት ሰዓታት ፈጅቷል ብለዋል።
እሳቱንም ለመቆጣጠር በተደረገ ርብርብ ከ15 በላይ ብሎኮችን ከነሙሉ ንብረታቸዉ ማትረፍ የተቻለ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።አደጋዉ የደረሰባቸዉ ቤቶች የተሰሩበት ግብዓት ቆርቆሮ በቆርቆሮ መሆናቸዉ እና የእንጨትና መሰል ተረፈ ምርቶች ክምችትና የቦታዉ ምቹ አለመሆን እሳቱ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል።በዚህ ኢንዱስትሪ መንደር ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ አደጋ ማጋጠሙን ኮሚሽኑ አስታውቋል።