“የህዳሴ ግደቡን በተመለከተ ሰሞኑን የሚነሳው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው” ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
“ለህዳሴው ግድብ ይህን ያህል ያስፈልጋል በሚል ከመንግስት የተገለጸ የገንዘብ መጠንም የለም” ሲሉ ዶክተር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ዶ/ር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም መንግሥት ለህዳሴው ግድብ ይህን ያህል ያስፈልጋል በሚል ከመንግስት የተሰጠ የገነዘብ መጠን የለም ብለዋል፡፡
በተለያየ ምክንያት ለህዳሴ ግድቡ ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች የሚያሥፈልጉ ገንዘቦች አሉ ግን "በተለያዩ ሰዎች" እንደሚወራው ይሄንን ያክል አይደልም ብለዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያውን ተከትሎ የወጪ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ ለዚህም መንግስት የሚያስፈልገውን ወጪውን ያውቀዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በዚህም የተጠቀሰውን ገንዘብ ያክል እንኳን ለህዳሴ ግደቡ ቀርቶ የሌሎች ፕሮጀክቶችም ተደምሮ ይሄን ያህል ሊያስፈልግ ይችላል በመሆኑም የሚነዛው ወሬ ማህበረሰቡን ለማደናገር ያለመ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ግንባታው ሊጠናቀቅ 2 ነጥብ 4 በመቶ ብቻ የቀረው ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ 80 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል መባሉን መዘገቡ ይታወሳል።