Personal Opinion:
ሩበን አሞሪም በሊቨርፑሉ ጨዋታ ላይ ከመጀመርያው ደቂቃ አንስቶ ምንም አይነት የታክቲክ ስህተት ሊፈጽም አይገባውም። በ3-4-2-1 አቀራረብ ከራስመስ ጀርባ ኮቢ ማይኑን እና አማድ ዲያሎን በማድረግ መጀመር የሚኖርበት ሲሆን፡ ኡጋርቴና ብሩኖን በማጣመር መሃሉን ጠጣር ማድረግ ይጠበቅበታል።
ዋናው አስፈላጊው ነገር ከፊት የሚሰለፉት 3 ልጆች ወደኋላ በመመለስ የሊቨርፑል የመሃል ሜዳ ተጫዋቾች ምቾት እንዳይሰማቸው እግር በእግር መከተል ይኖርባቸዋል። በኒውካስትሉ ጨዋታ ሳንድሮ ቶናሊ በአማድ ዙርያ ጥብቅ ክትትል ያደርግ እንደነበረው ሁሉ እነአማድም በሊቨርፑሉ ጨዋታ እነግራቨንበርችን እግር በእግር በመከታተል የማጥቃት ክፍሉን እንዳያግዙ ሰው በሰው የሆነ ታክቲካዊ ሚናቸውን ሊወጡ ያስፈልጋል።
የሊቨርፑል አጥቂዎች ወደ መሃል በመመለስ አማካኞቹን በማገዝና በፈጣን ሩጫ ችግር ለመፍጠር ስለሚንቀሳቀሱም የመሃል ሜዳው ላይ በርከት ያሉ ተጫዋቾች የሚፋለሙበት ይሆናል። በዚህ ሰአት ከሶስቱ ተከላካዮቻችን መሃል ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ወደ መሃል በመግባት ኳሶችን ማሰራጨት እና ያሉ ክፍተቶችን በመገንዘብ የማጥቃት ሂደቱን ማስተዳደር ይኖርበታል። ሊቻ ወደ ፊት በሚሄድበት ሰአት ዊንግባኮቹ በመናበብ አንደኛው የሊቻን ስፍራ ሲሸፍን ሌላኛው መስመሩን ለጥጦ የማጥቃት ክፍል ተጫዋቾች በመናበብ ሂደቱን እንዲፈጽሙት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ከባድ ጫና ክለባችን በሚያስተናግድበት ወቅትም ኳሱን ጥቅም አልባ ቢሆንም ባይሆንም ወደ ኋላ በመመለስ እግራቸው ስር አድርገው የሊቨርፑልን ቴምፖ ማቀዝቀዝ እና እራሳቸውን ካላስፈላጊ ሩጫዎች መጠበቅ ጠቃሚ ነው።
@Manchester_unitedfansz