ልቤ በራ!
፨፨///፨፨
ከራስ ጋር ንግግር፦ "ሰውነት ድካም አለው፣ ሰውነት ዝለት አለው፣ ብዙ የስሜት ውጣውረዶች ይፈራረቁበታል። እንደዛም ሆኖ ግን በፈጣሪው መልካም ፍቃድ ሁሉን የማለፍ አቅም አለው፣ በተሰጠው መንፈሳዊ ሃይል ሁሉን መቋቋም ይችላል። እኔም እንዲሁ እንደ ሰውነቴ የመጣብኝን ክፉም ሆነ መልካም ነገር ተቋቁሜ አልፌያለሁ። ብቻዬን ሳይሆን በፈጣሪዬ እገዛ፣ ለግሌ ሳይሆን በተሰጠኝ ብርቱ ሃይል ታግዤ። አሁን አሁን ደጋግሞ የሚታወሰኝ ጊዜ አለ። ያኔ ያንንም ይሔንንም ስነካካ፣ ከዚህም ከዛም ጥሩ ስሜት ሳፈላልግ፣ ከማውቀውም ከማላውቀውም ሰው ውለታን ስጠብቅ የነበረበት ጊዜ። የዋህነቴ ሲታወሰኝ ራሴን እታዘበዋለሁ፣ ሞኝነት ይሁን ቅንነት ምኑም አይገባኝም። ሰው ሁሉ እኔ እንደምሆንለት የሚሆንልኝ ይመስለኛል፣ የፈለኳቸው ነገሮች በሙሉ በቀላሉ እጄ የሚገቡ ይመስለኛል። ልቤ ደንድኗል፣ ውስጤም ተጃጅሏል፣ ማንነቴም ተዳክሞ ነበር። ራሱ ፈልጎ ማግኘት የሚችለውን ነገር ሰው እንዲሰጠው ይጠብቃል። ሳይሰጠው ሲቀርም ከራሱ በላይ ሰው ላይ ያዝናል። አምላኩ ያስቀመጠለትን አጋጣሚ ተሸጋግሮ በሰዎች እድል ለመጠቀም ይሯሯጣል። ይሔ የቀደመ ማንነቴ ዛሬ ላይ ሳየው ብዙ ያስገርመኛል፣ አንዳንዴም ያሳፍረኛል። ነገር ግን ዛሬ ላይ ሆኜ ትናንቴን ለመታዘብ በመብቃቴ እጅጉን ደስተኛ ነኝ።
አዎ! የደስታዬ ምንጭ የአምላኬ መንገድ ነው፣ የለውጤ ፋና ወጊ የፈጣሪዬ ህያው ቃል ነው። ልቤ በራ፣ ውስጤ ሀሴት አደረገ፣ ማንነቴ አደገ፣ ከፍ አለ፣ ፍፁም ተቀየረ። ማንም ሰው የተሻለውን ነገር ለራሱ ይመኛልና እኔም ብዙ መልካም ነገሮችን ተመኘው። የሆነልኝ ግን ከምኞቴ በላይ፣ ከሃሳቤም የላቀ ነው። ልቤ የበራልኝ ቀን ሁሉም ነገር የተሻለ እንደሚሆን አወቅሁ፣ ውስጤ አቅጣጫውን የተረዳ ቀን ህይወቴ መረጋጋትን ማጣጣም ጀመረች። በብዙ ገዢ ሀሳቦች ተውጬ ነበር፣ ከዛ መሃል ግን የነቃው መንፈሴ ወደሚበጀኝ ገዢ ሀሳብ ወሰደኝ። በእርግጥ ታጋይ ነበርኩ፣ መቼም እጅ የማልሰጥ፣ እንዴትም አንገቴን የማልደፋ። ትግሌ ግን እውቀት አልነበረውም፣ ድካሜ ግን መዳረሻ አልነበረውም። ስለታገልኩ የማሸንፍ፣ ስለሮጥኩ የምቀድም፣ ስለደከምኩም የሚታዘንልኝ ይመስለኝ ነበር። ነገር ግን ከሁሉም በፊት ልቤ መብራት እንደነበረበትና የምፈልገውንም ማወቅ እንደነበረብኝ ዛሬ ከበራልኝ ቦሃላ ተረዳው።"
አዎ! ጀግናዬ..! ፈጣሪህ ፊት ደጋግመህ ከመቆምህ በፊት የልብህን እውቀት መርምረው። ምን ይፈልጋል? አምላኩ ቢሰጠው የሚያስደስተው ምንድነው? በፍቅር ሊገዛለት የሚችለው ነገር ምንድነው? ባገኘው ቅፅበት "በቃ የፈለኩት ይሔ ነው።" የሚልለት ነገር ምንድነው? ብዙ ችኩል ሰዎች የት እንደገቡ አይተሃልና በፍፁም አትቸኩል፣ ብዙ የሚፈልጉትን ያላወቁ ሰዎች እንዴት እየኖሩ እንዳለ ታውቃለህና ፍላጎትህን ለማወቅ ቆም በል። ገና ያልተገለጠልህ ጥበብ በውስጥህ እንዳለ እመን። የአሁን እውቀትህ በየአቅጣጫው ውሱንነት ውስጥ ገብቷል። ፈጣሪ ልብህን እንዲያበራ ደጋግመህ ጠይቅ፣ እውነተኛውን ፍላጎትህን እንዲያሳውቅህ፣ የጉዞ አቅጣጫህን እንዲጠቁምህ ደጋግመህ ጠይቀው። ዝቅታህ ለሰው ሰይሆን ከፍ ለሚያደርግህ አምላክህ ነው፣ የምትጠይቀው የሚታዘብህን ሰው ሳይሆን ሁሉነገርህን የሚውቀውን ፈጣሪህን ነው። ጠይቅ፣ እወቅ፣ በትክክለኛው መንገድም ተጓዝ።