#ማስታወቂያ
የካቲት 23/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
#ለሽያጭ_መመዝገቢያ_መሳሪያና_ሶፍትዌር/ሲስተም_አቅራቢዎች_በሙሉ
የገቢዎች ሚኒስቴር የአሰራር ስርዓቱን ለማዘመን በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝነት ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በቀጣይ ለመተግበር ባቀደው የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አስተዳደር ስርዓት ላይ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ፣ ሶፍትዌር ወይም ሲስተም አቅራቢዎች በሚከተሉት አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ለማድረግ አቅዷል፦
1. ከገቢዎች ሚኒስትቴር የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ አስተዳደር ስርዓት ጋር ሶ
ፍትዌር/ሲስተም ለማስተሳሰር በሚጠበቁ ተግባራት ፤
2. ስለ ግብይት ምዝገባ እና ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ለገዥ/ከፋይ ስለማስተላለፍ፤
3. ከተሳታፊዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ መስጠት።
በዚህ ምክክር በነባሩ አሰራር መሰረት የካሽ ረጂስተር ማሽን ፣ ፖስ እና ሌሎች የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በተጨማሪ በቀጣይ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ጋር በመተሳሰር ግብር ከፋዮች ግብይታቸውን መዝግበው ደረሰኝ እንዲያስተላልፉ የሚያስችሉ ሶፍትዌር ወይም ሲስተሞችን የማልማትና በገቢዎች ሚኒስቴር እውቅና የማግኘት እቅድ ያላቸው ድርጅቶችም እንዲሳተፉ ይበረታታል።
በመሆኑም እርስዎ በስራው ላይ ካሎት ተሳትፎ አኳያ በውይይቱ ላይ ለመገኘት ያለዎትን ፈቃደኝነት እስከ ማክሰኞ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ በተዘጋጀው የጉግል ፎርም ላይ እንዲገልጹልን እየጠየቅን፤ የውይይቱ መድረክ የሚካሄድበትን ቦታ፣ ቀንና ሰዓት ፎርሙን በሞሉበት የኢሜይል አድራሻዎ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የመመዝገቢያ ፎርም፦ https://forms.gle/DUqR7V3t34ppK8757