(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኳታር አየር መንገድ እየተጓዙ የነበሩ ቻናዊያን በመደባደባቸው አውሮፕላኑ ኬንያ ለማረፍ መገደዱ ተዘገበ፡፡ ከስፍራው እንደተሰራጩ ዘገባዎች ከሆነ አውሮፕላኑ ወደናይጄሪያ ሌጎስ እየተጓዘ የነበረ ሲሆን በአየር ላይ በሁለት ቻይናዊያን መካከል ፀብ ይፈጠራል፡፡
በድብድቡ አንደኛው ቻይናዊ ተጎድቶ በመውደቁ የተነሳ አውሮፕላኑ ጆሞ ኬንያታ አየር ማረፊያ ሊያርፍ መቻሉን ዘገባዎቹ አስረድተዋል፡፡ የተጎዳው ቻይናዊ በአየር ማረፊያው የህክምና እርዳታ የተደረገለት ሲሆን ጥቃት የፈፀመው ቻይናዊ ከአውሮፕላኑ እንዲወርድ ተደርጎ በዚያው መታሰሩ ተገልጿል፡፡
አውሮፕላኑ ለአንድ ሰአት ያህል ከቆየ በኋላ መንገደኞቹን ይዞ ወደሌጎስ ሊበር እንደቻለ ዘገባዎቹ አስረድተዋል፡፡ ይህ ድርጊት የተፈጠረው እሁድ እለት ሲሆን በዚሁ እለት አንድ ሱዳናዊ ደግሞ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ሲጋራ ሲያጨስ በመገኘቱ መታሰሩን ዘገባዎቹ አስታውቀዋል፡፡
አውሮፕላኑ ከካርቱም ተነስቶ በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ ኬንያ የደረሰ ነበር፡፡ ልክ አውሮፕላኑ እንዳረፈ ይህ ሱዳናዊ ሲጋራውን በመለኮስ ህግ መተላለፉን ዘገባዎቹ ገልፀዋል፡፡