ዳሎል አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ኪልበቲ ዞን ዳሎል ወረዳ ዓዶኩዋ ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።
በዩኒቨርሲቲው የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ርዕደ መሬቱ ከዓዶኩዋ ከተማ 5 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ አቅጣጫ ነው የተከሰተው፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ በትናንትናው ዕለት ቀን 5 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ላይ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በአፋር ክልል ኮናባ ወረዳ ከትናንት በስቲያ በሬክተር ስኬል የተለያየ መጠን ያለው ርዕደ መሬት መከሰቱን አመልክተዋል፡፡
በአካባቢው የተከሰተው ርዕደ መሬት በመኖሪያ ቤቶች እና መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጸው፡፡
ሕብረተሰቡ ርዕደ መሬት ጋር ተያይዞ ከክስተቱ በፊት፣ በክስተቱ ጊዜና ከክስተቱ በኃላ ሊወሰዱ የሚገቡ የጥንቃቄ ርምጃዎችን መተግበር እንዳለበት ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ