ጥቂት ስለዚህ ነገር‼
===============
✍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ በተለይም በዋና ከተማዋ ሪያዽ አንዳንድ የሚያሳዝኑና የሚያሳፍሩ ነገሮችን እየታዘብን ነው። በተለይም በፈረንጆቹ 2019 ላይ በሃገሪቱ General Entertainment Authority በኩል የተጀመረው Riyadh Season (موسم الرياض) ብለው በየአመቱ የሚያዘጋጁት የመዝናኛ ፈሳድ ፕሮግራም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሃገሪቱን ሰናይ ገፅታ በሙስሊሙ ዓለም ዘንድ እያጠለሸው ነው። ሃገሪቱ በሁሉም ዘርፍ ተግታ የያዘችው Vision 2030 እንደ ማጠናከሪያ አድርገው ያሰቡት ይህ ፈሳድ፤ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከነዳጅ ጥገኝነት ለማውጣት ከሚያግዙት መንገዶች መካከል አንዱ ነው ተብሎ ቢታሰብም ከዲን አንፃር ኪሳራ ነው።
ይህንን ድርጊት ጤነኛ ሙስሊም ሁሉ ያወግዘዋል። እንዳውም ይህን በማውገዝ ረገድ ሳዑዲን የሚወዱ ይቀድማሉ። ምክንያቱም የምትወደው አካል ላይ መጥፎ ማየት ስለማትሻ! ግን የሚያወግዙት ከዚህ ፈሳድ የባሰ ፈሳድ በማያመጣ መልኩ እንጂ ይህን ተገን አድርጎ ቀድሞውንም የነበረን ጥላቻ መሰንዘሪያ አይደለም።
እንደ አለመታደል ሆኖ፤ እንኳን እንዲህ አይነት ፈሳድ ሲሠራ ተመልክተው ሳዑዲ የትኛውንም መልካም ነገር ብትሠራ ምንም የማይመስላቸው አካላት፤ ሁልጊዜ የርሷን መጥፎ ገፅታ ሰዎች ዘንድ አጉልተው በማሳየት በሙስሊሙ ዓለም ጭራቅ ተደርጋ እንድትሳል በብዙ ዘመቻዎች ይፈታተኗታል። ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ እኛው ሃገር ውስጥ ያሉ ህልማቸው ከሽፎባቸው መሃል መንገድ ላይ ሟምተው የቀሩት ኢኽዋኖች እና ቀድሞውኑም ሳዑዲን የውሃብያ መፈልፈያና ደጋፊ አድርገው የሚስሉት አሕባሾችና ሱፍዮች እንዲሁም ወይ በግልፅ ሺዓህ አልሆኑ አሊያ የለየላቸው ኢኽዋን ወላዋዮች፤ እንዲህ አይነት ነገሮችን ሳዑዲ ላይ ማየታቸው መተቻ መንገድ ስላገኙ ድርጊቱ ሰርግና ምላሽ ነው።
በተሽሞነሞኑ ቃላት፣ ተቆርቋሪ በሚመስል ስሜታዊ ሰበካ የአዞ እንባ እያነቡ ሳዑዲን የሚተቹት በተፈፀመው ድርጊት አዝነውና የእውነት ለዲን ተቆርቁረው ሳይሆን፤ ጥላታችን የሚሏትን ሳዑዲ ከህዝበ ሙስሊሙ መነጠያ ዘዴና ጥሩ አጋጣሚ ስለመለሰላቸው ነው።
ለዛም ነው በዚህ ድርጊት ላይ ተረማምደው ብርቅዬ ዑለሞቿን ቂጣ በቀደደ አፋቸው ያለ አቅማቸው ተንጠራርተው የሚወርፉት፣ እንደ ጥቅል እንደ ጭራቅ የሚስሉትንና የፈሳድ ህልማቸው አክሻፊ የሆነውን ሰለፊያ ዳዕዋን በደፈናው የሚተቹት።
እነዚህን የፈሳድ ቪድዮዎችና ምስሎች ከልክ በላይ አቀናብረውና አጋነው ተቆርቋሪ በመምሰል ሲያሰራጩ፤ ለዲኑ የሚቆረቆረው ንጹሕ ሙስሊም ቅድሚያ ለዲኑ ይሰጣልና ሳዑዲን ይወርፋል፤ ቀስ በቀስ ወደ ዑለሞቿም «ለምን አያወግዙም!» ብሎ ይወርፋል። ያውግዙ አያውግዙ አይተሃል? እንኳንን ይህንን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመረ ግልፅ ፈሳድ፤ እንደነ ኢብኑ ባዝ ያሉ ታላላቅ ዑለማዎች የሳዑዲን የምስረታ ቀን ማክበርንም ሳይቀር አውግዘዋል። ግን የሃገሪቱ መሪ በዑለሞች የተወገዘውን ሁሉ ሰምቶ ሁሉንም ይተገብራል ማለት አይደለም። የዑለማዎቹ ሥራ በሸሪዓው መሠረት ሐራምን ሐራም፣ ሐላልን ሐላል ማለት እንጂ ጦር ሰብቆ መንግስት ላይ ማዝመት አይደለም።
ደግሞ አንዳንዶች ቅዲሲቷን ሳዑዲ የምትሉት «ከመካና መዲና» ውጭ ቅዱስ ስፍራ አለ እንደ? ሪያዽ ቅዱስ ስፍራ ነው ያለው ማነው? ባይሆን ቅዱስ ካልሆነ ፈሳድ ይሠራበት እያልኩ አይደለም። አላህ የትም ቢሆን መታመፅ የለበትም። ነገር ግን እይታችንን አናጥበው ለማለት እንጂ!
በነገራችን ላይ ሳዑዲን ለመተቸት ከመቋመጣቸው የተነሳ ሰሞኑን እንደ አዲስ እያሽከረከሩት ያለውና በካዕባህ አምሳያ የተሠራ ብለው እያሽከረከሩት ያለው ከታች ያያዝኩት ምስል ባለፈ አመት በ2023 የነበረ ነው። የእውነት የሐቅ ተቆርቋሪ ከሆኑ ያኔውኑ ለምን አላወገዙትም? ግን ሰሞኑን በፈለስጢን ጉዳይ የሆነ ጠበቅ ያለ ተቃውሞ አሰምታለች መሰል ያንን ሸፋፍነው ይህንን ካለፈ ቪድዮ ቆርጠው አምጥተው እያሰራጩት ነው። በርግጥ ሌላ አለ ዘንድሮ ያዘጋጁት። የሰዎቹ ነገረ ሥራ እንጂ ጉዳዩ ባለፈ አመትም ይሁን ዘንድሮ የሚወገዝ መሆኑን ልብ ይሏል።
እነዚህ ሰዎች ኢራን ወይም ቱርክ ወይም ኳታር ወይም ሑቲዎች ወይም ሒዝቡ-ል'ሏህ ቢፈሱ፤ ፈለስጢንን ለማገዝ "ወደ እስራኤል ሚሳኤል እያስወነጨፉ ነው!" ነው የሚሉት፤ ሳዑዲ ወደ እስራኤል ብትተኩስ ግን "ሙከራ ለማካሄድ አስባ በስህተት አቅጣጫ ስቶባት ነው!" ብለው ሊፈስሩት ይችላሉ።
ለማንኛውም ሰዎች እንዳይሸወዱ በማሰብ፣ ማስተማርን በማሰብ፣ ሸሪዓውን ባማከለ መልኩ የሚደረገውን ፈሳድ ሁሉ ጥቅምና ጉዳቱን አመዛዝነን ሳናሽሞነሙን እንቃወማለን። ሳዑዲም ትፈፅመው ኢራን አሊያም ቱርክና ኳታር!
ግን ይህ ማውገዛችን ስሜታቸውን ጋልበው ለሚሄዱ ሳዑዲ ጠሎች የልብ ልብ በሚሰጥና እኩይ አላማቸውን ለማሳካት በር በሚከፍት መልኩ መሆን የለበትም።
ምክንያቱም ፈሳድ ለማውገዝ የግድ ፈሳድ መፈፀም አያስፈልግምና! ሽንት በሽንት ስለማይፀዳ!
አላህ ሳዑዲንና መሪዎቿን፣ ዑለማዎቿንና ህዝቦቿን ይጠብቃቸው፣ በዚህ ፈሳድ ላይ ለተሰማሩ ሁሉ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራቸው።
♠
||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse
fb.com/MuradTadesseOfficial