ምክንያት ሁለት፦ "ዑለማኦቹ እነዚህን ጥፋቶች እያዩ ለምን ዝም አሉ" የሚል ነው።
1ኛ፦ ዑለማኦቹ ዝም እንዳሉ ምን አሳወቃችሁ? እናንተ ካላወቃችሁ ደጋፊ ናቸው ነው የሚባለው? ዘመኑ የኢንተርኔት ነው ቢቃወሙ እናገኘው ነበር የሚል አይቻለሁ። በዚህ መልኩ ከደነ -ቆረ አካል ጋር መግባቢያው ሩቅ ነው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
مَنْ أَرَادَ أَنْ يَنْصَحَ لِذِي سُلْطَانٍ فَلَا يُبْدِهِ عَلَانِيَةً، وَلَكِنْ يَأْخُذُ بِيَدِهِ فَيَخْلُو بِهِ، فَإِنْ قَبِلَ مِنْهُ فَذَاكَ وَإِلَّا كَانَ قَدْ أَدَّى الَّذِي عَلَيْهِ
"ለባለስልጣን መምከር የፈለገ ሰው ባደባባይ አያውጣው። ነገር ግን እጁን ይዞ ገለል አድርጎ ይምከረው። ከተቀበለ እሰየው። ካልሆነ ግን ያለበትን አደራ ተወጥቷል።" ሸይኹል አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። (አንዱ ሐይሠሚ ዶዒፍ ብለውታል እያለ ገፅ ጠቅሶ ሲዋሽ አይቻለሁ። ቦታው ላይ የሌለ ቅጥፈት።)
እናንተ ስላላያችሁ ብቻ ዑለማኦች ዝም እንዳሉ ነው የምታስቡት? እንዲህ አይነቱ ጥያቄ ሶሐቢዩ ኡሳመቱ ብኑ ዘይድ ላይ ተነስቶ ነበር። "ለምን ዑሥማንን ገብተህ አታናግርም?" ሲሏቸው እንዲህ ነበር ያሉት፦
إِنَّكُمْ لَتُرَوْنَ أَنِّي لاَ أُكَلِّمُهُ إِلَّا أُسْمِعُكُمْ، إِنِّي أُكَلِّمُهُ فِي السِّرِّ دُونَ أَنْ أَفْتَحَ بَابًا لاَ أَكُونُ أَوَّلَ مَنْ فَتَحَهُ
"እናንተ ካላሰማኋችሁ በስተቀር እንደማላናግረው ነው የምታስቡት። እኔ የሸር በር ከፋች ሳልሆን በሚስጥር አናግረዋለሁ፤ የመጀመሪያው ከፋች አልሆንም።" [አልቡኻሪይ፡ 3267] [ሙስሊም፡ 2989]
ኢብኑ ዐባስም የሃገር መሪን በመልካም ስለ ማዘዝና ከመጥፎ ስለ መከልከል ሲጠየቁ "የግድ የምታደርገው ከሆነ ባንተና በሱ መሀል ይሁን።" [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይበህ፡ 7/470] [ሹዐቡል ኢማን፣ በይሀቂይ]
ይሄ ነብያዊ መንገድ፣ ይሄ የሶሐቦች አካሄድ የኢኽዋንና የኸዋ - ሪጅ በቀቀኖች ዘንድ የመድኸሊያ እምነት ነው። ሐዲሦቹንና ኣሣሮቹን አትፍቋቸው እንግዲህ። ዑለማኦቹ የናንተን ክስ ፈርተው ነብያዊውን አስተምህሮት ጥለው የሰካ.ራም ህግ ይከተሉ ወይ? እነዚህ የኢኽዋን መንጋዎች ድንቁ -ርናቸውን ንቃት ያደረጉ የመሀይማን መንጋ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ከተራው ሰው አይለይም። ጭንቅላት ከሆድ የከበረ አካል ነው። ይሁን እንጂ ጭንቅላት አንድ ከሆድ የሚያንስበት ነገር አለው። ባዶ ሲሆን አይናገርም። ሳይነቃ እንደነቃ ያስባል። በዚህ ጉዳይ ላይ ንቃት ያለው በነሱ ጩኸት ውስጥ ይመስላቸዋል። ግና ንቃት ያለው በዑለማእ አካሄድ ውስጥ ነው። ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ይላሉ፦
"ረቂቅ ከሆኑ ማስተዋሎች ውስጥ የሆነው የአዛዥን ስህተት ባደባባይ አለመመለስህ ነው። ስልጣኑ ስህተቱን ለመርዳት እንዲያነሳሳው ያደርገዋልና። ይሄ ሁለተኛ ስህተት ነው። ነገር ግን ሌሎች በማያስተውሉበት ሁኔታ ተለሳልሰህ አሳውቀው።" [አጡሩቁል ሑክሚያህ፡ 1/103]
"መድኸሊይ" በሏቸው እሳቸውንም።
2ኛ፦ "የሳዑዲ መንግስት ሐቅ የሚናገሩ ዓሊሞችን ይገድላል፣ ያስራል" ትላላችሁ አይደል? ያ ከሆነ ዓሊሞቹ ዝም ለማለት በቂ ምክንያት አላቸው ማለት ነው። ሸሪዐው የሚለው "መናገር ያልቻለ ሰው በልቡ ይጥላ" ነው።
3ኛ፦ በቱርክ፣ በኢራን፣ በሙርሲ አስተዳደር ወቅት ስለተከሰቱ ጥፋቶች ዝም ያሉ አልፎም አድናቂ የሆኑ ምሁራኖች ላይ ለምን ተመሳሳይ ክስ አላነሳችሁም? ጩኸታችሁ በተለየ የሱና ዑለማኦችና ሰለፊያ ላይ የሚሆነው ለምንድነው?
4ኛ፦ ቡድናዊ ጥላቻ አስክሯችሁ እንጂ እውነት እናንተ ኢስላምን የሚያጠለሹ ጥፋቶች ላይ በመናገር ምን የረባ ታሪክ አላችሁ? "የበደዊ ቀብር ላይ በያመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ሺርክ ሲፈፅም አልአዝሀር ዩኒቨርሲቲ የታለ? የኢኽዋን መሪዎች ለምን ዝም ይላሉ? ነው ወይስ የቀብር አምልኮ ሺርክ ከጭፈራ ያነሰ ጥፋት ነው? በነ ገኑሺ የኢኽዋን አስተዳደር ላይ የቀይረዋን ዩኒቨርሲቲ፣ የቱኒዚያ ምሁራን፣ እናንተን ጨምሮ ምን አደረጋችሁ?ሱኒዮችን በመጨፍጨፍ፣ በኣሉል በይት ላይ ድንበር በማለፍ ሺርኪያት ከሚፈፅሙ፣ ሶሐቦችን ከሚያወግዙ ሺዐዎች ጋር ህብረት የመሰረተው የነ ቀርዷዊ ማህበር ተመሳሳይ ዘመቻ ተከፍቶበታል ወይ? ዐሊይን ጨምሮ ብዙ ታላላቆችን የሚያከ - ፍሩት ኢባዲያ ኸዋ -ሪጆች ከነ ቀርዷዊ ማህበር ውስጥ የታቀፉ ናቸው። የኢባ .ዲያው ሙፍቲ አሕመድ አልኸሊሊ የማህበሩ ምክትል ነው። በሱና ዑለማእ ላይ እየጮኸ ያለው የሺ0፣ የሱፊያ፣ የኢኽዋን፣ የኸዋ .ሪጅ ጭፍራ እዚህ ሰፈር ድምፁን አያሰማም። "ሙፍቲ" ዑመር ጠቅላዩን "መለይካ ይመስላል" ሲል ይሄ አሁን የሚጮኸው መንጋ ትንፍሽ አላለም። አደም ካሚል ጠቅላዩን ከታላላቅ ነቢያት በላይ አድርጎ ሲያወድስ የኢኽዋን መንጋ ያሰማው ተቃውሞ የለም። የት ነበራችሁ? ከዑለማኦቻችን ላይ እጃችሁን አንሱ። ምላሳችሁን ሰብስቡ። ኢንሻአላህ እናንተን እርቃናችሁን ለማስቀረት የሚሆን አቅም አናጣም።
5ኛ፦ ደግሞስ ሃሜት ተፈቀደ እንዴ? የተረጋገጡ ጥፋቶችን ስናስጠነቅቅ የዑለማእ ነውር እየተከታተሉ የምትሉ አይደላችሁምን? ታዲያ ምነው መርሃችሁን ለቃችሁ ያውም በሌሉበት ዑለማኦችን ታጠለሻላችሁ? ቀርዷዊ ዘፈን ሲፈቅድ፣ አጅነቢያ ሴት ሲጨብጥና መጨበጥን ሲፈቅድ፣ ዲሞክራሲ ከኢስላም ነው ሲል፣ ሰይድ ቁጥብ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ሲያስተባብል፣ ሶሐባ ሲሳደብ፣ ህዝብ ሲያከ - ፍር፣ "ሙፍቲ" ዑመር በሙስሊሞች ላይ ጠላት ሲቀሰቅስ፣ ... እስኪ የተቃወማችሁበትን አሳዩን? ጭራሽ ለምን ተነኩ ብላችሁ አይደለም ወይ የምትጮሁት? የቢድዐ ቁንጮዎች ላይ ስንናገር ሃሜተኛ፣ ዑለማእ ተሳዳቢ ስትሉ አልነበረም ወይ?
ፅሁፌን ሳጠቃልል ሰዑዲያ ውስጥ በሚፈፀም ጥፋት ሁሉ ሰለፊያን ተጠያቂ የሚያደርጉ ደናቁ - ራን ናቸው። ቱርክ ከሰዑዲያ የበለጠ ከኢስላም የራቀች ናት። ነገር ግን ቱርክ ውስጥ የሚፈፀሙ ጥፋቶችን ወደ ሱፊያም፣ ወደ ኢኽዋንም አያስጠጉም። የሰለፊያ መንገድ ዘፈንና ጭፈራ አይደለም ከዚህ ያነሱ ነገሮችን ያወግዛል። የሱና ዑለማኦች አቋም ለወዳጅ ቀርቶ ለጠላት የሚታወቅ ነው። ዘፈን የሚፈቅዱት እነ ቀርዷዊ ናቸው። ሲኒማ ለማየት ሶላት ጀምዕ ያደረጉት፣ የፈረንጅ ዳንስ እየከፈሉ የተማሩት እነ ዑመር ቲልሚሳኒ ናቸው፣ የኢኽዋን ሶስተኛ ሙርሺድ። ሺርክን ዲን አድርገው የሚዋጉለት ኢኽዋንና ሱፊያ ናቸው።
ለማንኛውም ኢብኑ ሰልማን ወይም ቱርኪ አሉሸይኽ የሰለፊያ ዓሊሞች አይደሉም። የተከሰተውን ጥፋትም የሰለፊያ አቋም ነው ብለው አላቀረቡም። እነሱ ላይ የሚታይን ሁሉ ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጋ አካል በነ ኤርዶጋን፣ በነ ዑመር አልበሺር፣ በነ ቱራቢ፣ በነ ገኑሺ፣ በነ መሃቲር ፖለቲካ ሁሉ ኢኽዋንና ሱፊያ ሲከሰስ ሊቀበል ይገባል። እንዲያውም ከፖለቲከኞቹ አልፎ የነ ሐላጅ፣ ቢስጧሚ፣ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑል ፋሪድ፣ ኢብኑ ሰብዒን፣ ቲልሚሳኒ፣ የነ ቀርዷዊ፣ ኩፍ - ሪያት ሲነገሩ የምትጮሁ እንደሆናችሁ እናውቃለን። ገዛሊና የምታስተዋውቁት ኪታቡ ኢሕያእ ዑሉሙዲን ብዙ ሙንከራት የያዘ እንደሆነ የራሱ ተማሪዎች ጭምር የተናገሩት ነው። የሱና ዑለማእ ላይ የምትሰነዝሩትን ሩብ ያህል እንኳ እዚህ ላይ አትናገሩም። ይልቁንም እንዲህ አይነቱ እውነት መነገሩ ነው የሚያበሳጫችሁ።