Репост из: STEM with Murad 🇪🇹
በነገራችን ላይ የቲክቶክ CEO የሆነው Shou Zi Chew በፊት የፌስቡክ (የሜታ) ኩባንያ ተቀጣሪ Intern እንደነበር ታውቃላችሁ? ከ10 አመታት በኋላ ለፌስቡክና ለኢንስታግራም እንዲሁም ለትሪድ ከባድ ተገዳዳሪ ሆኖ መጣ። ከማርክ ዙከርበርግ ዘንድ እንደወጣ እንደ Xiaomi, Goldman Sachs, ByteDance አይነት ተቋማት ላይ ተቀጥሮ ሠርቷል። ይህ ፈጣን እድገቱ በአንድት ምሽት ቅፅበት የተገኘ ሳይሆን የቴኩን ዓለም መውጫና መግቢያውን በልምድና በተግባር ካጠና በኋላ የተገኘ ነው።
ይህን የፎርቹን ጋዜጣ አምድ አንብቡት። https://fortune.com/2025/01/15/tiktok-ceo-shou-zi-chew-mark-zuckerberg-intern-facebook/
አንዳንድ ጊዜ መቀጠርን አትጥሉ፤ ኢንተርን ከሆነ ደግሞ እንኳን ተከፍሏችሁ ባይከፈላችሁም በነፃ ላገልግላችሁ በሉና ተግባር ተኮር ዕውቀት ቅሰሙበት። ከ4 አመታት ቲዎሪ ይልቅ የ4 ወራት ኢንተርን የውጩን የሥራውን ዓለም ምንነት ለመረዳት ትጠቅማለች። እኔ የማልወደው በቅጥር ኮምፎርት ዞን መዘውተርን ብቻ ነው። ሳይበዛ መቅመሱ ብዙ በገንዘብ የማይተመኑ ጥቅሞች አሉት። ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ባለ ጊዜ ተነሱ ሲል መንገዱን ይከፍተዋል። እስከዛ ሰበብ እያደረሱ በትዕግስት መጠበቅ ነው።
||
t.me/STEMwithMurad