የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ነብዩ ሙሀመድ "ﷺ" እና እስልምናን የዘለፈውን ግለሰብ ተግባር አወገዘ!
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በማኅበራዊ ሚድያ ሃይማኖትን በመጠበቅ ሽፋን እየተሰራጩ ስለሚገኙት የጥላቻ እና ጠብ ጫሪ መልእክቶችን አስመልክቶ ወቅታዊ መግለጫ አውጥቷል።
ጉባኤው በመግለጫው ከሰሞኑ በአንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ነኝ በሚል ግለሰብ የእስልምና ሃይማኖት ነብይ በሆኑት በነቢዩ መሃመድ ሰ.ዐ.ወ ላይ ክብረ ነክ እና ኢ-ሥነ ምግባራዊ ንግግሮች መነገራቸው ተከትሎ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል። ይህ ድርጊት ሁሉም ማህበረሰብ ሊወግዘው የሚገባ ተግባር መሆኑን አንስቷል።
የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነ ምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ገልጿል፡፡
የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል።
በማኅበራዊ ሚድያ ሃይማኖትን በመጠበቅ ሽፋን እየተሰራጩ ስለሚገኙት የጥላቻ እና ጠብ ጫሪ መልእክቶችን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
የተከበራችሁ የሁሉም ሃይማኖቶች ቤተሰቦች እና ወገኖች !!
በሀገራችን ሕገ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች የሃይማኖት ነፃነት እና እኩልነት የተረጋገጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የሃይማኖት ተቋማትም ይህንን ነፃነትና እኩልነት ሲጠቀሙ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ባከበረ፣ ሰላማዊና መተሳሰብ የሞላበት እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
የሃይማኖት ተቋማት በአስተምህሮአቸው እና መልእክቶቻቸው ለአብሮነት፣ ወንድማማችነትና አንድነት ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተቋማችን ሃይማኖቶች ለማኅበረሰብ መከባበር፣ አብሮነትና ወንድማማችነትና መተሳሰብ ያላቸውን ፋይዳ በውል ይገነዘባል። ለዚህም አበክሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ምክክሮች ከሌሎች ተቋማት በተለየ መልኩ ፈጣሪን ከመፍራት፣ በሥነ-ምግባርና በግብረገብ ዕሴት የሚመራ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡
ሃይማኖት ተቋማት በውስጣቸውና ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት ምክክር የውስጥ ጥንካሬን፣ ለርስ በርስ መተማመን እና ለጋራ ርእይ በጋራ መሥራትን ሲያጎለብት በሃይማኖቶች መካከልም መከባበርን ፣ መተባበርን እና አብሮነትን በማሳደግ ጥርጣሬንና ስጋትን የሚቀርፍ ይሆናል፡፡
ችግሩ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንድ አንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በማኅበራዊ ሚድያዎች ሃይማኖታዊ ውይይትን እና ሃይማኖትን በመጠበቅ ሽፋን በሚተላለፉ መልእክቶች ወሰን ያለፋ ድፍረቶች መታየት ጀምረዋል።
የዚሁ ቀጣይ ጥፋት የሆነውና ከሰሞኑ በአንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ነኝ በሚል ግለሰብ የእስልምና ሃይማኖት ነብይ በሆኑት በነቢዩ መሃመድ ሰ.ዐ.ወ ላይ ክብረ ነክ እና ኢ-ሥነ ምግባራዊ ንግግሮች መነገራቸው ተከትሎ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል። ይህ ድርጊት ሁሉም ማህበረሰብ ሊወግዘው የሚገባ ተግባር ነው።
ጉባኤያችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነ ምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ተገቢ አለመሆኑን እና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እናሳስባለን፡፡
በአንፃሩ አንዳንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ነን የሚሉ ግለሰቦች ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ክብረ ነክ እና ኢ-ሥነ ምግባራዊ መልዕክቶች በመተላለፋቸው የክርስትና እምነት ተከታዮችን እንዳሳዘነ እና ቅሬታዎች መኖራቸውንም አስተውለናል፡፡
እንዲህ ዓይነት የሌሎችን የሃይማኖት አስተህምሮና ሃይማኖታዊ ሥርዓትን በማኅበራዊ ሚዲያ የማነወርና የማጥላላት ግለሰባዊም ሆነ ቡድናዊ ድርጊት የትኛውንም የሃይማኖት ተቋማትን የማይወክል ነው።
ሆኖም ግን እነዚህ ኢ-ሃይማኖታዊ እና ሕገ ወጥ ተግባራት የቆዩ ሲሆኑ፥ ባለፈው ዓመት በተቋማችን ሃይማኖትን ሽፋን ያደረጉ የግጭት መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችን በዳሰሳ ጥናት ከተለዩት ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ ነበር።
በማኅበራዊ ሚድያ የሚሰራጩ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች በጊዜ መፍትሔ ካልተበጀለት የሰላምና የጸጥታ ሥጋት እንደሚሆንና በተናጠልና በጋራ ሥራ መሰራት እንዳለበት ምክረ ሐሳብ የቀረበበት ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ተቋማችን ባሉት መዋቅሮች በሚድያ አጠቃቀምና ሌሎች በዳሰሳ ጥናቱ በተለዩ ጉዳዮች ላይ ስልጠና በመስጠትና ምክከሮች በማድረግ ችግሮቹን ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቶአል። አሁንም ይህንኑ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በተለይ ሰሞኑን ማህበራዊ ሚድያን በመጠቀም በአንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች የሌሎች የሃይማኖት ተቋማትን አስተምህሮ ፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን እና ትወፊቶችን የመንቀፍና የመዝለፍ ድርጊት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳዩ አሳሳቢና አፋጣኝ መፍትሔ ሊፈለግለት የሚገባ እንደሆነ ጉባዔያችን ግንዛቤ ወስዶአል፡፡
በችግሩ ወስጥ እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ባንድም በሌላ በሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የሚገኙ በመሆኑ፥ ችግሩ ከተወሰኑ የሃይማኖት ተቋማት ጋር ብቻ የሚያያዝ አይደለም፡፡ በመሆኑም ለችግሩ የሰከነ፣ ሚዛናዊ፣ ፍትሐዊ እና የጋራ መፍትሔ መፈለግ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ጉባኤያችን ያምናል፡፡ በመሆኑም የሚከተለውን የጉባኤያችንን አቋም እና ምክረ ሐሳብ ማስተላለፍ እንወዳለን፦
በማኅበራዊ ሚድያ የሌላ ሃይማኖትን አስተምህሮ እና ሃይማኖታዊ ሥርዓትን የማነወርና የማጥላላት ተግባራት ላይ እየተሳተፉ ያሉ የየትኛውም ሃይማኖት ተከታዮች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እናሳስባለን።
የተፈጠረውን ችግር መነሻ በማድረግ፣ በግለሰቦችና በቡድኖች በማኅበራዊ ሚድያ የሚተላለፋ አደገኛ መልእክቶችና ጉዳዩን የሚያባብሱ የድጋፍና ተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ እናሳስባለን።
የተለያዩ ሚድያዎችን በመጠቀም የሚሰጡ መግለጫዎች የቆየውን የሕዝባችንን አብሮነት፣ መከባባርና ወንድማማችነት በሚያጎለብት መልኩ ሚዛናዊ እና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲደረጉ እንጠይቃለን።
በማኅበራዊ ሚድያ የሌሎችን የሃይማኖት አስተምህሮና ሃይማኖታዊ ሥርዓትን የማነወርና የማጥላላት ተግባራት የሃይማኖት ተቋማቱን በቀጥታ ባይመለከትም፤ ግለሰቦቹም ሆነ ቡድኖቹ በአንድም ሆነ በሌላ የሃይማኖት ተቋማቱ አባላት በመሆናቸው የሃይማኖት አባቶች በዚህ ጉዳይ እየተሳተፉ ያሉ የመንፈስ ልጆቻቸውን የመምከርና የመገሰጽ ኃላፊነቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን፡፡
ሁሉም ሃይማኖት ተቋማት አገልግሎት በሚሰጡባቸው መድረኮችና ሚድያዎች የሚተላለፉ መልእክቶች የሌሎችን ሃይማኖቶች የሚነቅፍና የሚያጠለሽ እንዳይሆንና የሰላም ፈተና እንዳይሆን እንደ ተቋምና ግለሰብ (አገልጋይ) ኃላፊነትና ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ እንጠይቃለን።
ሀገራችን በሕግና በሥርዓት የምትተዳደር በመሆኗ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች በማኅበራዊ ሚድያ የሚሰነዝሩአቸውን ዛቻዎች ፤ የደቦ ፍርድ እና ሌሎች አፍራሽ ተግባራትን በማቆም፥ ችግሮች በሕግና በሕግ ብቻ እንዲፈቱ ጥያቄዎቻቸውን ለሚመለከታቸው የሕግ አካላት እንዲያቀርቡ እንመክራለን።