ሙንሺዶች (ማዲሆች) ሆይ! ለተውበት ፍጠኑ‼
===============================
✍️ ይህን ስፅፍ ብዙ ነቀፋ ላስተናግድ እንደምችል አላጣሁትም። ባፉ(በብዕሩ) ባይናገርም " ይኸ ደሞ ለምን ዝም አይልም? " የሚለኝ እንደሚኖርም እገምታለሁ። የሆነ ሆኖ ሰዎችን አስቀይሞ አላህን ማስደሰት ከተቻለ ደሞወዜ እሱ ነውና ለሌላው ምንተዳየ ብየ መክተቤን እቀጥላለሁ።
ሙንሺድ( ማዲህ) ሙሐመድ ሰዒድን(አላህ ይዘንለትና) በግሌ የምወደው በቀደሙትና " ኢሽተቅናክ፣ ነቢ ጎን አርገንን ወዘተ……" በመሰሉት ከሙዚቃ መሣሪያ በጸዱ ሥራዎቹ ነው። ዋሪዳ በሚባል አደረጃጀት ታቅፎ የተጫዎታቸው መንዙማዎች( ሙዚቃዊ ድራማዎች) ሊወገዙ የሚገባቸውና እርሱንም አላህ እንዲምረው የምንማጸንለት ድክመቱ ናቸው።
በህይወት ያላችሁና የምንወዳችሁ ሙንሺዶች አላህን ፍሩ፣ ይኸው እንደምታዩት መጨረሻችን ሞት ነው። በመሆኑም የኢስላምን መልዕክት ለማስተላለፍ ከሆነ ሙራዳችሁ ከሙዚቃ መሣሪያ ውጡ። እንደ ራያ አባመጫና ሙሀመድ አወል ሳላህ ጀሊሉ በሰጣችሁ ቅላፄ አንጎራጉሩ። እናንተ በኢኽላስ ወርውሩት፣ ወደ ሰዎች ጆሮ አድራሹ አላህ ነው። እርሱ የምትፈልጉትን ጉዳያችሁን ይሞላላችኋል። ከሃራም በሃላል ተብቃቁ‼
ሁኔታውን እያያችሁት ነው ነገ እኛም እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ላይ ብንወድቅ ከኡማው ማለፊያ መስተንግዶ ይጠብቀናል ብላችሁ ራሳችሁን አትሸንግሉ። ምናልባትም ጀሊሉ የወንድማችንን ውዴታ በሰው ልብ ያደረገው በሌሎች መልካም ሥራዎቹ ሊሆን ይመቻል‼
ነግዶ እንጂ ነሺዶ(መንዙማ) ብሎ፣ መፅሐፍ ጽፎ የሚያልፍለት አንድስ እንኳን አለን? ታዲያ በባንድ እየታጀባችሁ ነሽዳችሁና መድሃችሁ ከአላህ ጋር ከተጣላችሁ በኋላ ቁርጠኛዋ ቀን መጥታ ፀሃያችሁ ስትጠልቅ ምን ሊውጣችሁ ነው?! ለአላህ ብሎ አንድን የተጠላ(ሃራም ነገር) የተወ አላህ በተሻለ ነገር ይተካዋል" —(አል ሐዲስ)‼
አላህ ሆይ! መልዕክቴን ማድረሴን መስክር‼
NB:—ይኽን የመሰለውን ምክር ችላ ብለው በጀመሩት መንገድ የሚቀጥሉ ካሉ፣ ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ የምታዩ የወንጀሉ ተካፋዮች መሆናችሁን እወቁ። አላህን ፍሩ መጪው ትውልድ ቁርዓንን በየመድረኩ የሚያንበለብል እንጂ ዘፋኝ እንዲሆን አንሻም በጀሊሉ ፈቃድ፣ ሼር ይደረግ‼
©: አቡ ቢላል