ኢትዮጵያ በሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ መሆኑን ገለጸች
የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዶሎ በተባለ ከተማ በተፈጠረው ክስተት የኢትዮጵያ ኃይሎችን መክሰሱ ኢትዮጵያን ማስቆጣቱን እና ክሱም ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታለመ ነው ብሏል።ይህም የአፍሪካ ቀንድን ሰላም ለመበጥበጥ የሚፈልጉ እና በቀጣናው ሁልጊዜም ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የሶስተኛ ወገን አካላት ተግባር መሆኑን መግለጫው አትቷል።
በአንካራው ስምምነት ላይ እንደተገለጸው ሁለቱ ሀገራት ለሰላም የሚያደርጉት ቁርጠኝነት እንዳይደናቀፍ ክፍተት መፍጠር የለባቸውም ሲል ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።የኢትዮጵያ መንግስት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚቀጥልም መግለጫው አካቷል።
ኢትዮጵያ በአንካራ ስምምነት መሰረት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማደስ እና ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ ትቀጥላለችም ተብሏል።
የሀገራቱ መሪዎች ለሰላም ያላቸው ቁርጠኝነት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ትብብርን እንደሚያጠናክርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስታውቋል።