በአዲስ አበባ ከተማ 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ቀረበ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 14 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ አቀረበ፡፡
የሊዝ ጨረታው ከጥቅምት 8 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ክፍት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
መግለጫውን የሰጡት በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍና የሊዝ ክትትል ዳይሬክተር ጫሊ አብርሀም÷ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለጨረታው የቀረቡ መሬቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።
ይህ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ አራተኛው ዙር ሲሆን÷ በዚህኛው ዙር ብቻ አጠቃላይ የቀረበው 143 ሺህ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ነው ተብሏል።
ይህም በከተማ አስተዳደሩ ታሪክ በቁጥር ከፍተኛው መሆኑ ተመላክቷል።