ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb
+ ግሩፕ ለመቀላቀል +
https://t.me/NablisNablis
+ facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
TikTok
https://www.tiktok.com/@zdfitsumkebede1?_t=8pguEgtdsVq&_r=1

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በአጭር ጊዜ ህይወታቹን የሚቀይሩ የተረጋገጡ የ Draw ትኬቶች መሸጫ ቻናል እንጠቁማቹ ተጠቀሙ 👇

betting ሁሌ ማሸነፍ ከፈለጋቹ ይሄንን ቻናል ተቀላቀሉ 👇


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???


ስለ ሰሞኑ ጉዳይ ...
***
1. ያለሕግ ፍርድ የግድያ ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል ነው። እስከምናውቀው ድረስ ኢትዮጵያ ለሃይማኖት የማይወግን (secular) ሕገ መንግሥት ያላት ሀገር እንጂ በሸሪዓ የምትተዳደር ሀገር አይደለችም። በመሆኑም የሚያስቆጣ ነገር ሲኖር ወደ ሕግ መውሰድ እንጅ በደቦ ለመግደል መነሣት ትልቅ ስሕተት ነው። ሰው ሁሉ ፍርድን በእጁ አድርጎ መገዳደል ከጀመረ የሚነደው እሳት መጥፊያው ጭንቅ ይሆናል።
2. የሃይማኖት ውይይት (ክርክር) መደረጉ አስፈላጊ እና የማይቆም ነገር ነው። ሁሉም ሃይማኖቶች ዕቅበተ እምነት የመሥራት እና ሌላውን ወደራስ የማምጣት ኃላፊነት አለባቸውና።
3. በውይይቶች ምን ዓይነት መንገድ እንከተል? የሚለው ወሳኝ ነገር ነው። Double standard አያስኬድም። "እኔ እንደ ልቤ ልናገር። ሌሎች ግን እኔ እስከፈቀድኩት ልክ ብቻ ይናገሩ" ማለት ፍትሕ አይሆንም። ዘላለማዊ እውነትን ከሚፈልግ ሃይማኖተኛ የሚጠበቀው ለራስም ለሌሎችም አንድ አይነት መሥፈርት ማውጣት ነው። በመሆኑም አንዳንድ ጠንከር ያሉ የእቅበተ እምነት አካሄዶችን የሚያወግዝ ሰው በሁለቱም በኩል ያለውን ቢያወግዝ ቢያንስ ፍትሐዊ ይሆናል።
4. ከሰሞንኛው ችግር ተነሥተን የክርስትና-እስልምና ተዋሥኦ እንዴት ይሠራ? እኛ ላለንበት ሁኔታ ትክክለኛው ተግባራዊ አካሄድ የትኛው ነው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ቢደረጉ ጥሩ ይመስለኛል።

(መምህር በረከት አዝመራው )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


🌨በዚህ በ2017 ዓ.ም የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ‼️
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ ግእዝ መማማሪያ ቻናላችን ግእዝ በነፃ እየገለፅን  ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  ስለሆነ ትምህርቱም በonline ስለሆነ በዚህ #ዙር ላይ 100 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ ለጀማሪችሁ እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለመማር የምትፈልጉ ለመመዝገቢያ ብቻ 200 ብር   ብቻ ነው ክፍያው መማር ለሚፈልጉ ሼር አድርጉ ።

   🤲 የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
🌨በዚህ  ዓመት የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ‼️

ለመመዝገብ ምትፈልጉ ከታች ባለው አካውን አናግሩን
@rufael_yiliybegal
@rufael_yiliybegal
@rufael_yiliybegal

የቻናሉ ሊንክ 👇👇👇
https://t.me/+MQhYKhzFQK05ZmY0
https://t.me/+MQhYKhzFQK05ZmY0
https://t.me/+MQhYKhzFQK05ZmY0


ኮርሱ ሊጀምር ነው ቮይስ ቻት ግቡ❤


➢ ነገረ ድኅነት ተከታታይ ኮርስ

◉ በማኅበረ ኤዶምያስ መንፈሳዊ ጠቅላላ ማኅበር

ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3ሰአት ጀምሮ

ኮርሱ የሚሰጥበት ሊንክ👇👇👇
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ




ከሀገር ውጪም በሀገር ውስጥም ላላችሁ ለክራር አፍቃሪያን በሙሉ በጠየቃችሁኝ መሰረት የአጭር ጊዜ የክራር ስልጠና ስለተዘጋጀላችሁ መማር የምትፈልጉ #0926314162 #0961369536 ላይ በመደወል መመዝገብ ትችላላችሁ
ሌላው ሞደፊክ የተሰራ ስራችሁን የሚያቀልላችሁ ቲውነርም ከፈለጋችሁ ለአገልግሎት የሚሆኑ ቆንጆ ክራሮችም ስላሉ ፈላጊ ብቻ ይደውሉ ሁሉንም በአንድ ቦታ ታገኛላችሁ ።


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


➢ ነገረ ድኅነት ተከታታይ ኮርስ

◉ በማኅበረ ኤዶምያስ መንፈሳዊ ጠቅላላ ማኅበር

ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3ሰአት ጀምሮ

ኮርሱ የሚሰጥበት ሊንክ👇👇👇
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21


ኹለት ጉዳዮች...

1ኛ፦

ነገረ ማርያም፥ እንኳን የአዳምን መርገም የተፈጥሮን ሕግ የሻረ ነው።
አሮጌው ክርክር በቤታችን እንደ አዲስ ባይነሣ ጥሩ ነበር።

ለማንኛውም፥
አምጦ መውለድ የመርገም ውጤት ነበር።
“ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ።” እንዲል
ዘፍጥረት 3፥16።
ጌታችን ክርስቶስ ይኽን ቀዳማዊ(አበሳ ዘጥንት) መርገምንና ኀጢኣትን ከደመሰሰልንም በኋላ፥በሰማንያ ቀን ተጠምቀው ከእግዚአብሔር ለተወለዱ እናቶችም በምጥ መውለድ አልቀረም።
እንግዲህ ሴቶች በምጥ ስለወለዱ፥ የወደቀ ሥጋ ስለያዙ ነው እንላለን?? አንልም።

እንዲኽ የምንል ከኾነማ የክርስቶስ ቤዛነት ከመርገም ከፍሎ ያስቀረው አለ ያሰኝብናል።
ነገረ ማርያም፥ የተፈጥሮን ሕግ እንኳ የሻረ መኾኑ፥ ሰይጣን እንኳ ያወቀው ፀሓይ የሞቀው ዕውነት ነው።
ለዚኽም ምስክራችን ብዙ ነው።አንዱን ብንጠራ እንዲኽ ይለናል።
"ወሊድ ዘእንበለ መወልዲት ወዘእንበለ ሕማም፤
ያለ አዋላጅ ያለ ሕመም መውለድ"። እያለ ይደነቃል ኤራቅሊስ።

ጌታችን ክርስቶስ ከመሰቀሉ አስቀድሞ የውድቀት ውጤት የኾነው ምጥ በወሊድ ጊዜ ካላገኛት
የመርገም ምልክት የነበረ መስቀልን የድል ምልክት አድርጎት የኀጢኣት ውጤት የነበረ ሞትን በሞቱ ክቡር አድርጎት ሳለ፥ የእመቤታችን ሞት እንዴት የውድቀት ምልክት ይኾናል?አይኾንም።
ሲጠቃለል
ነገረ ማርያም፥ እንኳን የአዳምን መርገም የተፈጥሮን ሕግ የሻረ ነውና ዕፁብ ብለን ማለፍ ይሻለናል።

2ኛ፦
በማኅበራዊ ሚዲያ ብዙ ወጣት ከሚሰማቸው አንዱ ወንድማችን፥ አገልግሎቱን ለጊዜው እንዳቆመ ሰማኹ። እኔ ግን እላለኹ። አገልግሎቱን ከምታቆም አቋምኽን አስተካክል። ምን ማለት ነው? ዕይታኽ ከውስጥ ወደ ውጭ ይኹን።
እና ደግሞ በአብነት ትምህርት ወይም በነገረ መለኮት ትምህርት ቤት የሚነሱ አከራካሪ ጉዳዮችን በማኅበራዊ ሚዲያ አታንሣ።
የጥብርያዶስ ቀለም ለዮርዳኖስ አይኾንም። ቦታው አይደለምና።

ወንድማችን ላይ ጥርጣሬ ያለን ሰዎች፦
ከመቶ ዘጠና ያመጣውን ተፈታኝ ከትምህርት ማባረር አግባብ አይደለም። ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዲያልፍ ከተፈለገ እንዲያነብብ ያነበበውን በውስጣዊ ዐይን እንዲረዳ ማድረግ ነው ትርፍ። ማባረር ኪሳራ ነው።

ውስጣዊ ዐይን የምለው ምኑን መሰላችኹ?
ኹሉም የሊቃውንት መጻሕፍት ትርጓሜዎች ናቸው። ለምሳሌ የቄርሎስ የዮሐንስ... መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውን ጨምሮ ራሳቸው ሊቃውንቱ ሲጽፏቸው በትርጓሜ መልክ ነው።
የእኛ ሊቃውንት ደግሞ ትርጓሜውን ተረጎሙት። ዐውድ እንዳንስት በሀገርኛ ምሳሌ አብራሩት። የሊቃውንት መጻሕፍት የትርጓሜ ትርጓሜ ናቸው። ውስጣዊ ዐይን ያልኩት ይኽ ነው።

Edited
"የወደቀ ሥጋ" ማለት ሞት የሚስማማው ማለት ነው የሚል መልስ እያየኹ ነው፡፡ መልካም፡፡
አዳም ከመውቁ በፊት ሞት የሚስማማው እንጂ የማይስማማው አልነበረምኮ፡፡ ስለኾነም "የወደቀ ሥጋ" ማለትና ሞት የሚስማማው ማለት፥ እንዴት አንድ እንደሚኾን ለሚነግረኝ ሰው እርማቴ ፈጣን ነው፡፡

መጭው ዐቢይ ጾም የፍቅር ጾም ይኹንልን።

( ሊቀ ሊቃውንት ሥሙር አላምረው )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


የየእለቱን የቅዱሳንን ዜና ገድል ስንክሳር ማንበብ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ከታች ያለውን  linkun ነክቸው join ይበሉ

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan


ጉዞውን መመዝገብ የምትፈልጉ በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች እየደወላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ። የእናታችን ቅድስት ኪዳነምህረት በረከቷ ረድኤቷ አይለየን🥰🙏


ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ስለት ሰሚዋ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

የካቲት 16 እሁድ ቀን
የእመቤታችን የኪዳነምህረት አመታዊ መታሰቢያን በዓል ምክንያት በማድረግ ይህን የበረከት ጉዞ አብራችሁን መጓዝ የምትፈልጉ
👉 መነሻ ሰአት 11:00 ሰአት
👉 ትራንስፖርት መስተንግዶ ጨምሮ
👉 ዋጋ 600 ብር

መነሻ ቦታዎች፦ ፒያሳ ጊዮርጊስ
መገናኛ ውሃ ታንከሩ
ወሰን/ጧፎ አደባባይ

ለበለጠ መረጃ
+251940301386
+251967722490
+251903845380
+251954998757

አዘጋጅ ማኅበረ ኤዶምያስ መንፈሳዊ ጠቅላላ ማኅበር


+ በብርሃን ተናገሩ +

"በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ " ይላቸዋል (ማቴ1.፥27) ። "ጌታችን ለሐዋርያት"

ይህን በሚነግራቸው ጊዜ ፍጹም ጨለማ አልነበረም ። ይህንኑ ራሱ ጠንካራ ምስልን ተጠቅሞ ነግሯቸዋል እንጂ በስውር አልነገራቸውምና ። ይኽውም ማለት ከዚህ በኋላ ሊሰጣቸው ካለው የንግግር ጥብዓት አሁን እየነገራቸው ከነበረው የንግግር ቃና አንጻር ሲታይ ከእነርሱ ጋር ብቻና በአንዲት ትንሽዬ የፍልስጤም ጥግ ላይ እየተነጋገረ ስለ ነበረ "በጨለማ" እና "በጆሮ" አላቸው ። "

ያን ጊዜ የብስን እና ባሕርን ተሻግራቹ ሰው የሚኖርባትንና የማይኖርባትን ቦታ ኹሉ አካልላቹሁ ለመኳንንት ለነገዶችም ለፈላስፎችና ለንግግር ዐዋቂዎች ፈታችሁን ገልጣችሁና በታላቅ ጥብዓት የምትሰብኩት ለአንድ ወይም ለኹለት ወይም ለሥስት ከተማዎች አይደለምና ለዓለም ኹሉ ነው እንጂ ። ስለዚህ ያለ ምንም መሸማቀቅ በነጻነት ፦ "በሰገነት ላይ " እና " በብርሃን " አለ ።

"በሰገነት ላይ ስበኩ " እንዲሁም "በብርሃን ተናገሩ" ብቻ ሳይኾን ጨምሮ "በጨለማ የምነግራችሁን " እና "በጆሮ የምትሰሙትን " ያለውስ ለምድነው ? ይቀጥላል .....

(የማቴዎስ ወንጌል -ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደ ተረጎመው ትርጉም ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገጽ-208-209 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


የየእለቱን የቅዱሳንን ዜና ገድል ስንክሳር ማንበብ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ከታች ያለውን  linkun ነክቸው join ይበሉ

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan


😍ሁዳዴ ቻሌንጅ😍


ቻሌንጁ በነፃ ነው ምንም ክፍያ አናስከፍልም ። ለሁሉም የሚሆን መፅሐፍ

🔰  " የኤፌሶን ወንዝ "

➤  በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የተፃፈ መፅሐፍ ነው
  መፅሀፉን በቻሌንጅ   መልክ ለእናንተው  መልካም እድል ።

  እጣው ላይ ለመካተት 200 ሰዎችን ብቻ ወደ ማኅበረ ኤዶምያስ ቴሌግራም ግሩፕ አድ ያድርጉ ካደረጉ በኃላ  ቴሌግራም ፔጁ ላይ 16 ቁጥርን ፅፈው ይላኩ ።

● ማሳሰቢያ የመፅሐፉ ባለእድለኛ መፅሐፉ ባለበት ይደርሰዋል

  መልካም እድል

የግሩፑ ሊንክ 🔰 በመጫን ይቀላቀሉ
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21


በመቄዶንያ የበረከት ስራ እንስራ !!

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ


+ የተሰበረ ጽዋዕ +

እዚኽ ፎቶ ውስጥ በአካል የማውቀው ዘማርያምን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ግን በማኅበራዊው ሚዲያ መልስ ሲሰጡና ሲጠይቁ አያቸዋለሁ እንጂ ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም፡፡በወንድሞቻችን ፊት ፕሮቴስታንት ሰባክያን ምላሳቸውን ሲተሳሰር ብዙ ጊዜ አይቻለኹ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ከኦርቶዶክስ ወንድሞች ጋር እንዳትከራከሩ" የሚል አዋጅ ሲያውጁ ሰምቻለኹ ጰንጤዎቹ፡፡
በአጭሩ፥ እኒኽ ወንድሞቻችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መላእክትና ሰዎችን ታመልካለች የሚለውን ፕሮቴስታንታዊ የድር ምሽግ ሲበጣጥሱ ተመልክቻለኹ፡፡ ከዐይን ያውጣችኹ አልላችኹም፡፡ ዐይንም ጆሮም ውስጥ ናችኹና፡፡
ጽንዑ ወኀይሉ፡፡ ለማለት ነው አመጣጤ፡፡
ከእኒኽ ወንድሞች መኻል አንዱ ወይም ኹሉም ሊሳሳቱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቀለም ሠረገላ የማያሰናክለው የለምና፡፡
ደግሞም እኔ እንኳ የሰማኋቸው የሚታረሙ ስሕተቶች አሉ፡፡ የሚታረም ነገር ተገኘ ማለት ግን፥ ሙሉ እርሻው አረም ነውና አያስፈልግም የሚል ቧልት መናገር ቅንነትና ወንድማዊ ፍቅር ይጎድለዋል፡፡

በአንድ ወቅት፦
አንድ እጅግ የተከበሩ ሊቅ ከአንዲት ሴት ጋር ድቀት አገኛቸው፡፡ እኒኽን ሊቅ ብዙ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ በዚኽኛው ታሪክ ግን ሰፊው ሕዝብ ስለማያውቃቸው ስማቸውን ልለፈው፡፡
ይኽን ድቀታቸውን የሰማ ደብተራ አንድ ቀን ማሕሌት ውስጥ አገኛቸው ሊቁን፡፡"ደግሞ አንተ እዚኽ ምን ልታደርግ ገባኽ?"
ሲል በፍና ተሣልቆ አፌዘባቸው፡፡ እርሳቸውም "እኔኮ የተሰበርኩ ጽዋዕ ነኝ" ብለው አንጀት የሚበላ መልስ ሰጡት፡፡
የተሰበረ ጽዋዕ ሰባራ ስለኾነ አይጣልም፡፡ንዋይ ቅዱስ ነውና በክብር ከዕቃ ቤት ይቀመጣል እንጂ፡፡

እንደዚያ ደብተራ ለቤተክርስቲያን የቀናን እየመሰለን ጥቂት ሸራፋ ያገኘንባቸው ጽዋወችን ኹሉ አውጥተን እንጣል ማለት እጅግ የከፋ በደል ነው፡፡ክርስቶሳዊውን መንገድ የረሳ ነውና፡፡ "ድኅረ ተሰብረ አጽንዖ ለሰብእናነ ልሕኵት፥ ለብሓዊ ክርስቶስ በማየ ሐዲስ ጥምቀት" የምትል ድንቅ የንጉሥ ጉባኤ ቃና አለች፡፡ ግርድፍ ትርጉሟ፦ ገላ'ችን ከተሰበረ በኋላ ሸክላ ሠሪው ክርስቶስ በአዲስ የውኀ ጥምቀት እንደገና ሠራው፡፡ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ከጌታዋ የተማረችው የተሰበረን መጠገን ነው፡፡
ችግሩ፥ መጠገን እንደመስበር ቀላል አይደለም፡፡ ለመጠገን ዕውቀትና ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ለመስበር ግን ኦርቶዶክሳዊ የዘብነት ቀለም የተቀባች ምላስ በቂ ናት፡፡
ወንድሞች በጎ ሲሠሩ እናበርታ፡፡ሲስቱ እንክርዳድ ከስንዴ እየለየን በፍቅር እናርም፡፡አልታረምም የሚል ካለ ደግሞ የቤክርስቲያን ቱንቢ ያርመዋል፡፡እንደ ግለሰብእ እኔ ነኝ ቱንቢው ማለት ግን የስሕተት ስሕተት ነው፡፡

በየሚዲያው ሌሎች ጥሩ ወንድሞችም አሉ፡፡ ነገር ግን በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የተገለጡ ናቸውና ተውኳቸው ፡፡

( ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ



Показано 20 последних публикаций.