እግዚአብሔር አብ የኢየሱስ ክርሰቶስ አባት የሚባለው ሰው ሆኖ በተወለደበት የኋለኛው ልደቱ በኩል በተናጠል ሳይሆን ዘመን ከመቆጠሩ በፊት ከአብ በተወለደው ረቂቅ ልደቱ በኩል ነው ። ነገር ግን ቀድሞ ዘመን ሳይቆጠር ከአብ የተወለደውም በኋለኛው ዘመን ሰው ሆኖ ከድንግል ማርያም የተወለደውም አንድ ወልድ (ልጅ) ነው እንጂ ሁለት አይደለም። ሰው ሲሆን ከተፈጸመው ረቂቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተነሣ አብ አባት ሲባል ለወልድ መለኮት ብቻ አይደለም ፤ ድንግል ማርያምም እናት ስትባል ለወልድ ሰውነት ብቻ አይደለም ፤ ክርስቶስ ከዋሕዶ በኋላ አንድ እንጂ ሁለት አይደለም። (የልቦና ችሎት ገጽ-14 )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ