ክነፈ ርግብ | ዘማሪ ዲያቆን ሀብታሙ እሸቴ እና ዘማሪት ሰብለወንጌል እሸቴ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ ሐመልማለ ወርቅ
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ አማን በአማን/3/
ኢይኃልቅ ኪዳንኪ ወላዲተ ቃል
ዘመርን በትህትና ይገባሻልና
ሆነሻል ከለላ የፅድቃችን ጥላ
ማርያም ፊደላችን ፅድቁን ማንበብያችን
የሁሉ መማርያ የአምላክ ማደርያ
ጌታሽን ወልደሻል አዝለሽ ተሰደሻል
ፍቅርሽ ገደብ የለው ከቶ እዳንቺ ማነው
የእግዚአብሄር ከተማ የተመላሽ ግርማ
ስምሽ ይጣፍጣል ከፍጥረት ይልቃል
በዱር በገደሉ የኖሩ በቃሉ
ሆነሻል ስንቃቸው አንባ መጠጊያቸው
በእንተ ማርያም ብሎ የጠራሽ ለምኖ
ያጣ የለምና ይድረስሽ ምስጋና
ምክንያት አለን እኛ ተሰተሻል ለኛ
ሁሌም በልባችን አለሽ እናታችን
የምትሆኚ ተስፋ አዝኖ ለተከፋ
ቀርቦ ለለመነሽ አፅናኝ እናት ነሽ
አንቺ ምስራቅ ነሽ ልጅሽም የጽድቅ ፀሐይ ነው እውነት በእውነት/3/
አያልቅም ቃልኪዳንሽ የአምላክ እናት
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ ሐመልማለ ወርቅ
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ አማን በአማን/3/
ኢይኃልቅ ኪዳንኪ ወላዲተ ቃል
አዝ
ዘመርን በትህትና ይገባሻልና
ሆነሻል ከለላ የፅድቃችን ጥላ
ማርያም ፊደላችን ፅድቁን ማንበብያችን
የሁሉ መማርያ የአምላክ ማደርያ
አዝ
ጌታሽን ወልደሻል አዝለሽ ተሰደሻል
ፍቅርሽ ገደብ የለው ከቶ እዳንቺ ማነው
የእግዚአብሄር ከተማ የተመላሽ ግርማ
ስምሽ ይጣፍጣል ከፍጥረት ይልቃል
አዝ
በዱር በገደሉ የኖሩ በቃሉ
ሆነሻል ስንቃቸው አንባ መጠጊያቸው
በእንተ ማርያም ብሎ የጠራሽ ለምኖ
ያጣ የለምና ይድረስሽ ምስጋና
አዝ
ምክንያት አለን እኛ ተሰተሻል ለኛ
ሁሌም በልባችን አለሽ እናታችን
የምትሆኚ ተስፋ አዝኖ ለተከፋ
ቀርቦ ለለመነሽ አፅናኝ እናት ነሽ
አንቺ ምስራቅ ነሽ ልጅሽም የጽድቅ ፀሐይ ነው እውነት በእውነት/3/
አያልቅም ቃልኪዳንሽ የአምላክ እናት
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All