Orthodox Mezmur Channel


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✞✞✞ Orthodox Mezmur Channel ✞✞✞

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቆየት ያሉ እና አዳዲስ መዝሙሮችን ያገኛሉ።
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

ለማንኛውም ሀሳብ ፣ ጥቆማ ፣ አስተያየት
👇👇👇
@Orthodox_Mezmurs
@Orthodox_Mezmurs

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ስሜን በደም ጻፍከው | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ስሜን በደም ጻፍከው በህይወት መዝገብ
ከመፍጠርህ ልቋል የማዳንህ ጥበብ
ህመምህ ህመሜ ቁስልህ ቁስሌ ነበር
በእኔ መቃብር ውስጥ ሦስት ቀን ባታድር /2/
አዝ

ሕይወቴን በዋዛ በከንቱ ስጥላት
በእኔ ላይ ሰልጥኖ እርግማንና ሞት
ሕይወቴን ልትመልስ ሕይወትህን ሰጥተህ
ከሞት ልታድነኝ ሞቴን አንተ ወስደህ
አዝ

ሕዝብህን በጉዞ በፍቅር የተከተልክ
አለቱ አንተ ነህ በቃዴስ የነበርክ
ሌንጊኖስ ቢመታህ የጎንህን አለት
የፈሰሰው ውሃ አረካኝ ከጥማት
አዝ

መውደቅህ አቆመኝ ተወግዶ ነውሬ
መስቀል ስትሸከም ወደቀ ቀንበሬ
በመገረፍ ቁስል ከቁስል ፈወስከኝ
እጅ እግርህ ሲታሰር ከእስር ተፈታሁኝ
አዝ

መናቅህ ክብሬ ነው የሆነልኝ ለኔ
ይህንን መስክሬ አያቆም ልሳኔ
ከወንበዴዎቹ ጋር አብረህ ስትቆጠር
ለኔ በአፌ ሞላህ ውዳሴና መዝሙር

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


በርባን ነኝ | ዘማሪ አቤል ተስፋዬ

በርባን ነኝ በአንተ መስቀል የዳንኩኝ/2/
አዝ

በኃጢያት በበደል የኖርኩኝ በክፋት
ወንበዴ ነበርኩኝ የሚገባኝ መሞት
ሁሉንም እረስተህ በፍቅር ያየኸኝ
ንገረኝ አምላኬ እንደምን ወደድከኝ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ
አዝ

ወንበዴው እኔ ነኝ ሀገር ያስቸገርኩኝ
እጆቼን በበደል በደም የታጠብኩኝ
አንተ ግን ራርተህ ተሰጠህ ስለ እኔ
ዋጋ ከፈልክልኝ ክርስቶስ መድህኔ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ
አዝ

ሞቴን ስጠባበቅ እኔ እንደ ስራዬ
ትክክል ነውና የክፋት ዋጋዬ
አንተ ግን ንጹሁ እኔን የወደድከኝ
ለነፍስህ ሳትሳሳ እስከ ሞት ደረስክ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ
አዝ

በዋጋ ገዝተኸኝ ዳግመኛ እንዳልሞት
ብርታት ሁነኝ እና ልለይ ከኃጢአት
መልካምም እንዳስብ መልካም እንድሰራ
በጽድቅ ልመላለስ ልቦናዬን አብራ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ
አዝ

በዋጋ ገዝተኸኝ ዳግመኛ እንዳልሞት
ብርታት ሁነኝና ልለይ ከኃጢያት
መልካምም እንዳስብ መልካም እንድሰራ
በጽድቅ ልመላለስ ልቦናዬን አብራ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ
አዝ

በዋጋ ገዝተኸኝ ዳግመኛ እንዳልሞት
ብርታት ሁነኝ እና ልለይ ከኃጢአት
መልካምም እንዳስብ መልካም እንድሰራ
በጽድቅ ልመላለስ ልቦናዬን አብራ

ጌታዬ በርባን ነኝ በሞትህ ያዳንከኝ
አምላኬ በርባን ነኝ በመስቀል ያዳንከኝ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


የኢዮብ መልሱ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እንደምነህ ቢሉት ዘመዶች ከድተዉት
ሚስቱ ትታው ሄዳ ልጆች ሞተዉበት
ዓይኖቹ በምሬት እንባ አላፈሰሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ነበር የኢዮብ መልሱ/2/
አዝ

በሕይወት ገጥሞት የበረታ ፅልመት
በአንድ ቀን ሲነጠቅ ልጆችና ንብረት
አካሉ በቁስል ተይዞ በፀና
ኢዮብ እንዴት ቻለ ለአምላኩ ምስጋና
አዝ

በሰጠበት መንደር ሲቆም ለልመና
ሚስቱ ሙት ስትለው ጌታን እርገምና
የስንፍናን ነገር አይሰማም ጆሮዬ
ይክሰኛል እርሱ ይችላል ጌታዬ
አዝ

ቅን ነገር መናገር ለአፌ ከቸገረኝ
አምላኬ እንዳያዝን ምነው ዝም በአልኩኝ
ልሳኔ እንዳይጠራ ሞት እና መከራ
ለምስጋና ቆሜ ነገን ዛሬ ልስራ
አዝ

እግዚአብሔር ይመስገን ቢጎድልም ቢሞላም
ለዓይኔ ሽፋሽፍት እንቅልፍ እንኳን ባጣም
ብዙ እንደነበረው ትናንትና ደጄ
ክፉውንም ደግሞ ይቀበላል እጄ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️

የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት

ቅድስት

ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ፤ ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡


በስራዬ የት ይሆን መግቢያዬ | ሊቀ-መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ /4/
ጨነቀኝ ጠበበኝ/ከበደኝ/ ነፍሴ ወዲያልኝ /2/
አዝ

ተሸክሜ የኃጢአት ክምር /2/
ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር /2/
ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ /2/
ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ /2/
አዝ

በድያለሁ ወዳንተ እጮሃለሁ
ይቅር በለኝ እማፀንሃለሁ
ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜአለሁ /2/
አዝ

አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ /2/
እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዬ /2/
በንስሐ ሳላጥበው እድፌን /4/
ልትደርስ ነው ያች ፈተና ቀን /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ኃጢያት በደሌን ትቼ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ኃጢያት በደሌን ትቼ
በፍቅር ወደርሱ መጥቼ
በእንባዬ እግሮቹን ባጠብኩት
ብቻ ጌታዬን በካስኩት/2/
አዝ

ነፍሴን እያሳደፍኩ በበደል ስኖር
ለካ ሳፈርስ ነበር ሕንፃ እግዚአብሔር
አሁን ግን አፅድቶኝ በልቤ በገባ
እሰዋለታለሁ የእንባዬን መባ
አዝ

ድካሜን ሳይቆጥር ጌታዬ ከጠራኝ
ወደኋላ አላይም ከእንግዲህ ምን አለኝ
መቅጫዬን ትቼ እከተለዋለሁ
ከእርሱ ጋራ ውዬ ከእርሱ ጋር አድራለሁ
አዝ

ምሬሃለሁ ብሎ ካበዛልኝ ፀጋ
እለዋለሁ ቅዱስ ሲመሽም ሲነጋ
ፍቅሩ በልቤ ላይ ስሙ በአንደበቴ
ዘወትር አይጠፋም እርሱ ነው ጉልበቴ
አዝ

ልጄ ብሎ ጠራኝ እጆቹን ዘርግቶ
እርሱን ማሳዘኔን በደሌን እረስቶ
በፍታን አለበሰኝ ፍሪዳን አረደ
የፈጠረኝ ጌታ መዳኔን ወደደ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ማስተዋል ስጥልን | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ማስተዋል ስጥልን አእምሮን ስጥልን
አከበርንህ ብለው ለጣሉት ክብርህን /2/
አዝ

አለቱን ፈልፍላ መቅደስ ለተከለች
ሥጋዉና ደሙን ለሕይወት የሰጠች
በአምስቱ አዕማድ የጸናችው ቆማ
የነፍስ እረፍት ነች ያለች አስቀድማ
አዝ

ያላቸው ከሚመስል የአምልኮ መልክ
ኃይልህን ለካዱት ሀሰት በመስበክ
የሰራሃት ቅፅርህ በፅኑ መሠረት
ከመንጋው ተለዩ በኑፋቄ ትምህርት
አዝ

ማርያም ማርያም ብትል በሠርክ በማለዳ
ስለሰጠችን ነው መድሃኒትን ወልዳ
ነገረ ቅዱሳን ቢሰበክ በአዋጅ
መች ጋረዱንና ገለጡልን እንጂ
አዝ

ከሦስት ሺህ ዘመን ቀድማ ለታነጸች
አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን ላመነች
አይሆንም ኢየሱስ እንግዳ ዜናዋ
እርሱ ነው ያስገኛት እርሱ ነው ሰሪዋ
አዝ

የሥጋን ነው እንጂ የነፍስን ሳያዩ
የጸጋው ግምጃ ቤት እርቀው ተለዩ
ሃይማኖት እያለኝ ምግባር ለጎደለኝ
ለእኔም ማስተዋሉን አእምሮን ስጠኝ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


❤️ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤️

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት

ዘወረደ

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡


ክበር ተመስገን | ዘማሪ ቀሲስ ዳዊት ፋንታዬ

ምነው ወዳጄ ምነው
ክበር ተመስገን
ጌታችን ለዚህ ያደረሰከን
አዝ

ሰላምን ስጣት ለምድሪቱ
አላስተኛ አለን ሁከቱ
የዘንድሮስ ጠብ ክፋቱ
ወንዱ ከወንዱ ሴት ከሴቱ
ምነው ወዳጄ ምነው
አዝ

ይፍቱኝ አባቴ በጠዋቱ
ወጥቶ ቀሪ ነው ሰው ከንቱ
ይፍቱኝ ሳይል የበረረ
እንደታሰረ በዘያው ቀረ
ምነው ወዳጄ ምነው
አዝ

ቅዳሴ ቅኔ ማኅሌቱ
አቤት ማመሩ አይ ውበቱ
ሥራውም ቀሏል ከትላንቱ
ተከፋፍለዋል ካህናቱ
አዝ

ተጣልቻለሁ ከአባቶቼ
የጾሙን መብዛት ጠልቼ
አርባ ቀን ጾመን በነበር
ምነው ማማቱ ቢቀር
አዝ

ወንድሜ ሲሄድ ሸኘሁት
መናፈቁን ግን ፈራሁት
የርሱ ሳይበቃኝ ደግሞ እህቴ
ተኩላ መጣች ከቤቴ
ምነው ወዳጄ ምነው

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


የኔ ጌታ | ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

የኔ ጌታ
ሰምቼ አድምጬ ልቀመጥ በእርጋታ
መንፈሴን አበርታ/2/
አዝ

ፈጥኖ ይስማማና ሐሳብህ ከሀሳቤ
ስጋት መከራዬ ይነቀል ከልቤ
ጭንቀትን ይነቅላል እርጋታን ይተክላል
ቃልህ ስልጣን አለው ያፈርሳል ይሰራል
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ

ችግሬ ታላቅ ነው አይበል ከንፈሬ
ታላቅነትህን ለንገር ለችግሬ
ጠላቴ ፊት ስቆም ፊትህ ተንበርክኬ
የድል ነው ዘመኔ የድል ነው ታሪኬ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ

ዝናብ ታመጣለህ ባይኖርም ደመና
በረከትን ልጥገብ እሺ ልበልና
ያደረክላትን ልንገራት ልነብሴ
ልጠማ ጧት ማታ ልስማ በመንፈሴ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ

በፊትህ ምንድን ነው የሴረኞች ሴራ
ቃልህ ጉልበት አለው ይንዳል ተራራ
በእርሱ መዶሻነት በደሌ ሲመታ
ጫጫታው ያልፍና ይሰፍናል ጸጥታ
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ
አዝ

አያፍረኝ አይፈራኝ ቃልህ መስታወቴ
ሁሌ ይነግረኛል ስለማንነቴ
ወዴት እንደወደኩ ወዴትስ እንዳለው
ሽንገላን በማያውቅ በቃልህ አውቃለው
አይወድቅም አንተን የሰማ
ድምጽህን ልጅህ ልጠማ
በቅዱስ መንፈስህ
ይዋሃደኝ ቃልህ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


የትኛው ስራዬ | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

የትኛው ስራዬ ነው የትኛው ህይወቴ/2/
ሞገስ ሆኖኝ እንጂ እግዚአብሔር አባቴ/2/
አዝ

ልጅዋን ትረሳ ዘንድ እናት እንኳን ብትስት
አንተ ግን ወደድከኝ ላትረሳኝ በሞት
በመዳፍህ ቀርፀህ ሁሌ ታየኛለህ
መድሀኒቴ ኢየሱስ በደሌን እረስተህ
ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ
አዝ

የአብርሀምን ምግባር የዮሴፍን እምነት
ፅድቅን ባልኳለው ባላደርግ መቀነት
ማህተቡን ይዣለሁ የደሙን ጠብታ
መድሀኒቴ ኢየሱስ አክብሮኛል ጌታ
ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ
አዝ

እንዳልፈው የረዳኝ የእሳቱን ባህር
ምን ምግባር ኖሮኝ ነው ከፅድቅ የሚቆጠር
የልቤ ኩራት ነው የአይኔ ከፍታ
መድሀኒቴ ኢየሱስ የሠራዊት ጌታ
ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ
አዝ

ዘይቱ እንዴት ፈላ በራሴ ያፈሰስከው
ዙፋን ልታወርሰኝ ልቤን የመረጥከው
የኔ የተወደደው ከኤልያም ደም ግባት
መድሀኒቴ ኢየሱስ ሆነኸኝ ነው ውበት
ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ/2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ዘወረደ እምላዕሉ | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

ዘወረደ እምላዕሉ
መድኃኒተ ኩሉ
ወወረደ እምሰማያት
ቤዛ ኩሉ ፍጥረት
አዝ

በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም
በፈቃዱ ታየ ኢየሱስ በሚል ስም
አካላዊ ቃል ነው ከላይ የወረደ
አዳምን በሞቱ ሊያድን የወደደ
አዝ

ከዙፋኑ መጣ ከአባቱ ሳይለይ
በድንግል አደረ የማይታይ ሊታይ
ትንቢተ ነቢያት ይኸው ተፈጸመ
እርቀ አዳም ሆነ ሕይወት ለመለመ
አዝ

ምን ይሆን ምስጢሩ ከሰማይ መውረድህ
ከመላእክት አይደል ከሰው መወለድህ
እንዴትስ ብትወደን ካንተ የተዛመድነው
ሰውን ታስበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው
አዝ

እውነተኛ ፍቅር ከሰማይ ያወርዳል
አማናዊ ፍቅር ኃጥእ ያስወድዳል
በዚህ ፍቅር አክመኝ ዳግመኛ ልወለድ
ከጎኔ ያሉትን ወንድሞቼን ልውደድ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


እኔ አንተ ቤት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ፊት
የምቆም ሠው አይደለሁም
ግን ፍቅር ነህ ለዘለዓለም
የሚመስልህ ማንም የለም/2/
አዝ

ፀሎቴ ቢሆን ለወረት
ጎዶሎ ቢሆን የኔ እምነት
ባረከኝ እኔን ከሠማይ
በደል ጥፋቴንም ሳታይ
ቀባኸኝ ጠርተኸኝ ከዱር
ሠጠኸኝ ከፍ ያለ ወንበር
ሳይኖረኝ አንድም በጎነት
ባረከኝ በእጅህ በረከት
አዝ

ቃልኪዳንህን አክባሪ
ታማኝ ነህ ሁሌም መሀሪ
የማልከውንም መሀላ
አትረሣም አትልም ችላ
መካሪ ድንቅ መምህሬ
ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ
ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ የሠማይ የምድር ሲሣይ
አዝ

መሻቴን ብቻ ስላየህ
ደካማ ልጅክን ጎበኘህ
ብቃቴ መቼ ሆነና
ያቆመኝ ላንተ ምስጋና
አንኳኩ ስላልክ አንኳኳው
ጠይቁ ስላልክ ጠየኩኝ
ከፍተሃል በርህን ለኔ
የታተምኩብህ መድህኔ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


እግዚአብሔር መልካም ነው | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እግዚአብሔር መልካም ነው 
በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው/2/          
አዝ

ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን 
ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን 
ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነው
በመከራው ጊዜ መሸሸጊያ ሆነው/2/ 
አዝ

አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት 
ከነአን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት 
ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎልበት 
እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት/2/ 
አዝ

በሐዘን በችግር በመከራ ጊዜ 
ጭንቄን የሚያርቅ ነው የነብሴን ትካዜ 
የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ 
እግዚአብሔር መልካም ነው ሐዘኔን አስረሳኝ 
የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ 
ክርስቶስ ኢየሱስ ሀዘኔን አስረሳኝ 

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

አምላካችን መድኃኒታችን ልዑል እግዚአብሔር ጾሙን የበረከት ፣ የረድኤት ፣ የድኅነት ፣ የንስሐ ፣ ዲያቢሎስን ድል መንሻ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችንን ፣ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከመዓት ሕዝቦቿን ከክፉ መቅሰፍት የምንታደግበት ያድርግልን ፤ አሜን።


ክነፈ ርግብ | ዘማሪ ዲያቆን ሀብታሙ እሸቴ እና ዘማሪት ሰብለወንጌል እሸቴ

ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ ሐመልማለ ወርቅ
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ አማን በአማን/3/
ኢይኃልቅ ኪዳንኪ ወላዲተ ቃል
አዝ

ዘመርን በትህትና ይገባሻልና
ሆነሻል ከለላ የፅድቃችን ጥላ
ማርያም ፊደላችን ፅድቁን ማንበብያችን
የሁሉ መማርያ የአምላክ ማደርያ
አዝ

ጌታሽን ወልደሻል አዝለሽ ተሰደሻል
ፍቅርሽ ገደብ የለው ከቶ እዳንቺ ማነው
የእግዚአብሄር ከተማ የተመላሽ ግርማ
ስምሽ ይጣፍጣል ከፍጥረት ይልቃል
አዝ

በዱር በገደሉ የኖሩ በቃሉ
ሆነሻል ስንቃቸው አንባ መጠጊያቸው
በእንተ ማርያም ብሎ የጠራሽ ለምኖ
ያጣ የለምና ይድረስሽ ምስጋና
አዝ

ምክንያት አለን እኛ ተሰተሻል ለኛ
ሁሌም በልባችን አለሽ እናታችን
የምትሆኚ ተስፋ አዝኖ ለተከፋ
ቀርቦ ለለመነሽ አፅናኝ እናት ነሽ

አንቺ ምስራቅ ነሽ ልጅሽም የጽድቅ ፀሐይ ነው እውነት በእውነት/3/
አያልቅም ቃልኪዳንሽ የአምላክ እናት

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ኪዳነ ምህረት | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ለዘላለም ንፅሕት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ሕያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሐዘኔን አልፌ
አፅናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ከጥፋት ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእግሬ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት
አዝ

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መጥተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
ኪዳነምሕረት/3/ አምባ መጠጊያ ናት

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ኪዳነ ምሕረት እናቴ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛዬ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ /2/
አዝ

አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ /2/
አዝ

ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ /2/
አዝ

አልልም መቼ ነው ቀኑ
የኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አምናለው
ሁሉን በጊዜው አያለው /2/
አዝ

የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ /2/

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ኪዳነ ምሕረት | ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃልኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር /2/
አዝ

የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
አዝ

የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
አዝ

የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
አዝ

የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All


ማን እንዳንቺ ከፍጥረት መሀል | ዘማሪት ሰላማዊት ሶርሳ

ማን እንዳንቺ ከፍጥረት መሀል
የወለደ ፍጡር ፈጣሪን
ከህሊና ከአይምሮ በላይ ነው
ይሄ ምስጢር እጹብ ነው ድንቅ ነው
አዝ

ፀሐይ ወጥቶልናል ለጨለማው ህይወት
አማኑኤልን ወልደሽ የሁሉን መድኅኒት
ክብርን ከተሞሉ ከሁሉ ቅዱሳን
ብልጫ አለሽ ማርያም ምክንያተ ድኂን
የሚመስልሽ የለም አንድም ከፍጥረቱ
ለማንስ ተችሏል ሊዳሰስ እሳቱ
ጸጋ የሞላብሽ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ
ማርያም/2/ እያልኩ አንደበቴ ይቀደስ
እናት ነሽና ለንጉሱ
ምስጋና ይድረስሽ በመቅደሱ
ብጽዕት ነሽና ብጽዕት ልበልሽ
በየትውልዱ ይዘከር ስምሽ/2/
አዝ

ዘርን አስቀርቶ ፍጥረቱን ለማዳን
ስጋሽን ለበሰ ሰው ሆነ ጌታችን
በረቀቀው ምስጢር ፍጥረት በማይደርሰው
ከአንቺ ተወለደ አንቺን የፈጠረው
መልዐኩ ገብርኤል የመሰከረልሽ
ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ
ማን እንዳንቺ ልበል ከፍጥረት መሀል
ሰው ለሆነው አምላክ እናት ሆነሻል
አዝ

የነቢያት ትንቢት የሐዋርያት ስብከት
የሐዲስ ኪዳን ኪሩብ የተገባሽ ስግደት
ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ጌታ
ማደሪያ ሆንሽለት ላክብርሽ በእልልታ
የጌታዬ እናት ልበል እንደ ኤልሳቤጥ
እንዴት ይቻለኛል ልትመጪ ከእኔ ዘንድ
ትህትናሽ የሳበው ወልድን ሀያል ፍቅር
ኦ ግርምት ድንግል ለክብርሽ ልዘምር
አዝ

በፍጹም ንጽሕና ግሩም ቅድስና
የኖርሽ እንደ ቃሉ ስብሕት በኩሉ
ያመንሽ ብጽዕት ነሽ ትውልድ የሚያገንሽ
የአምላካችን እናት በምን እንመስልሽ
የባርያይቱን ውርደት ጌታ ተመልክቷል
ያከበርሽው አምላክ ከፍ ከፍ አድርጎሻል
ነፍሴ ሀሴት ታድርግ በደስታ ትዘምር
አንቺን ስለሰጠኝ መድኃኒቴ ይክበር

@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All

Показано 20 последних публикаций.