ዘወረደ እምላዕሉ | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
ዘወረደ እምላዕሉ
መድኃኒተ ኩሉ
ወወረደ እምሰማያት
ቤዛ ኩሉ ፍጥረት
በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም
በፈቃዱ ታየ ኢየሱስ በሚል ስም
አካላዊ ቃል ነው ከላይ የወረደ
አዳምን በሞቱ ሊያድን የወደደ
ከዙፋኑ መጣ ከአባቱ ሳይለይ
በድንግል አደረ የማይታይ ሊታይ
ትንቢተ ነቢያት ይኸው ተፈጸመ
እርቀ አዳም ሆነ ሕይወት ለመለመ
ምን ይሆን ምስጢሩ ከሰማይ መውረድህ
ከመላእክት አይደል ከሰው መወለድህ
እንዴትስ ብትወደን ካንተ የተዛመድነው
ሰውን ታስበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው
እውነተኛ ፍቅር ከሰማይ ያወርዳል
አማናዊ ፍቅር ኃጥእ ያስወድዳል
በዚህ ፍቅር አክመኝ ዳግመኛ ልወለድ
ከጎኔ ያሉትን ወንድሞቼን ልውደድ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ዘወረደ እምላዕሉ
መድኃኒተ ኩሉ
ወወረደ እምሰማያት
ቤዛ ኩሉ ፍጥረት
አዝ
በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም
በፈቃዱ ታየ ኢየሱስ በሚል ስም
አካላዊ ቃል ነው ከላይ የወረደ
አዳምን በሞቱ ሊያድን የወደደ
አዝ
ከዙፋኑ መጣ ከአባቱ ሳይለይ
በድንግል አደረ የማይታይ ሊታይ
ትንቢተ ነቢያት ይኸው ተፈጸመ
እርቀ አዳም ሆነ ሕይወት ለመለመ
አዝ
ምን ይሆን ምስጢሩ ከሰማይ መውረድህ
ከመላእክት አይደል ከሰው መወለድህ
እንዴትስ ብትወደን ካንተ የተዛመድነው
ሰውን ታስበው ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው
አዝ
እውነተኛ ፍቅር ከሰማይ ያወርዳል
አማናዊ ፍቅር ኃጥእ ያስወድዳል
በዚህ ፍቅር አክመኝ ዳግመኛ ልወለድ
ከጎኔ ያሉትን ወንድሞቼን ልውደድ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All