የኢዮብ መልሱ | ሊቀ-መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እንደምነህ ቢሉት ዘመዶች ከድተዉት
ሚስቱ ትታው ሄዳ ልጆች ሞተዉበት
ዓይኖቹ በምሬት እንባ አላፈሰሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ነበር የኢዮብ መልሱ/2/
በሕይወት ገጥሞት የበረታ ፅልመት
በአንድ ቀን ሲነጠቅ ልጆችና ንብረት
አካሉ በቁስል ተይዞ በፀና
ኢዮብ እንዴት ቻለ ለአምላኩ ምስጋና
በሰጠበት መንደር ሲቆም ለልመና
ሚስቱ ሙት ስትለው ጌታን እርገምና
የስንፍናን ነገር አይሰማም ጆሮዬ
ይክሰኛል እርሱ ይችላል ጌታዬ
ቅን ነገር መናገር ለአፌ ከቸገረኝ
አምላኬ እንዳያዝን ምነው ዝም በአልኩኝ
ልሳኔ እንዳይጠራ ሞት እና መከራ
ለምስጋና ቆሜ ነገን ዛሬ ልስራ
እግዚአብሔር ይመስገን ቢጎድልም ቢሞላም
ለዓይኔ ሽፋሽፍት እንቅልፍ እንኳን ባጣም
ብዙ እንደነበረው ትናንትና ደጄ
ክፉውንም ደግሞ ይቀበላል እጄ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
እንደምነህ ቢሉት ዘመዶች ከድተዉት
ሚስቱ ትታው ሄዳ ልጆች ሞተዉበት
ዓይኖቹ በምሬት እንባ አላፈሰሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ነበር የኢዮብ መልሱ/2/
አዝ
በሕይወት ገጥሞት የበረታ ፅልመት
በአንድ ቀን ሲነጠቅ ልጆችና ንብረት
አካሉ በቁስል ተይዞ በፀና
ኢዮብ እንዴት ቻለ ለአምላኩ ምስጋና
አዝ
በሰጠበት መንደር ሲቆም ለልመና
ሚስቱ ሙት ስትለው ጌታን እርገምና
የስንፍናን ነገር አይሰማም ጆሮዬ
ይክሰኛል እርሱ ይችላል ጌታዬ
አዝ
ቅን ነገር መናገር ለአፌ ከቸገረኝ
አምላኬ እንዳያዝን ምነው ዝም በአልኩኝ
ልሳኔ እንዳይጠራ ሞት እና መከራ
ለምስጋና ቆሜ ነገን ዛሬ ልስራ
አዝ
እግዚአብሔር ይመስገን ቢጎድልም ቢሞላም
ለዓይኔ ሽፋሽፍት እንቅልፍ እንኳን ባጣም
ብዙ እንደነበረው ትናንትና ደጄ
ክፉውንም ደግሞ ይቀበላል እጄ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All