ጌታችን ወደዚህ ዓለም የመጣው ቤዛ ሆኖ ሊያድነን ነው። ቅዱስ ጳውሎስ " ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው።" እንዳለ(1ጢሞ 1:15)። እርሱ ራሱ ለቤዛነት ሰው መሆኑን "እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" ብሎ እንደተናገረ(ማቴ. 20:28)።
ይህም ማዳን በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ከፅንሰቱ ጀምሮ በእያንዳንዱ መንገድ ካሳ እየከፈለልን መጥቶ በመስቀል ላይ የተፈጸመ ነው። እርሱ በእያንዳንዱ ጉዞው ካሣ እየከፈለልን ለድኅነታችን የሚያስፈልገውን ሥራ ሠራ። ስለዚህም የቤዛነት ሥራው በጽንሰት የተጀመረ ነው። እርሱ በጽንሰቱ ተስፋ ሰጠን፥ በጽንስ ይቆራኝ የነበረ ዲያብሎስንም አራቀ። በልደቱ የዲያብሎስን ልብ አራደ፥ ሰውና መላእክትም አብሮ እንዲዘምሩ አደረገ። በስደቱ ከገነት የተሰደደ አዳምን ክሶ ስደታችንን ሻረልን፥ ተሰዶ የሰማዕታትን ስደት የባረከላቸውም እርሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በጥምቀቱ የአዳምና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤ ፋቀ፥ በእኛ ላይ የነበረችውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰ። በጾሙ አርእስተ ኃጣውዕን አደከመ፥ ዲያብሎስን ድል የምንነሳባትን ሥርዓተ ጾም ሠራልን። በተአምራቱ ኃይል ሰይጣንን አደከመ። በስቃዩ ስቃያችንን አራቀ። በሞቱ ሞትን ደመሰሰ። በትንሣኤው ትንሣኤን አበሠረ። በዕርገቱ ወደ ቀደመ ክብራችን መመለሳችንን አበሠረ። በዚህ ጉዞ እኛ ድኅነትን(መዳንን) አገኘን።
ሥራ በሠራበት ሁሉ ካሳ ከፍሎልን(ቤዛ ሆኖን) ያዳነን መድኃኒታችን እርሱ የተመሰገነ ነው።አሜን በእውነት🤲