TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
ኢትዮ ግጥም እና ፍልስፍና ethio poem&philosophy

31 Oct 2024, 18:20

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

#ፍቅር ነው የራበኝ

ደህና ነኝ እንዳልል
  ደህንነቴ ጠፍቷል
እሞኛል እንዳልል
ይሄው ፊቴ ፈክቷል
ሰው ሲያየኝ ጤነኛ
ውስጤ በሽተኛ❤️‍🩹
ቆይ ምን ብየ ላውራ
ሰሚ ሰው አግኝቼ
በልቤ ጠራ ውስጥ
የትኛውን ትቼ

አይቶ በሚፈርድ
ጆሮ ጠቢ ምላስ በሞላበት ሀገር
ለየትኛው ሰሚ
ለየትኛው ሀኪም ህመሜን ልናገር?
ከማንነት በላይ
ከምንነት በላይ
ምን ቃል ሊተነፈስ?
በሽፋን መለኪያ
ምን እውነት ሊታፈስ?

ፍቅር ነው የራበኝ💔
እሱ ነው ያመመኝ💘
የሀገሬ መሬት ሰው እያካሰሰ
ሰው እያናከሰ
የሀገሬ ቋንቋ
ዘር እያስቆጠረ
ክልል እያጠረ

ያዳም የአብራክ ክፋይ
ሰውነት ቀረና
በጎሳ በብሄር
ታጥሮ ህልውና

በሽብር አይምሮ
ሀገር ይታመሳል
ለማይጠቅም አለም
ንጹህ ደም ይፈሳል
ክብር የሰው ስጋ
በግፍ ይቆረሳል
አፍ እየቀደመ
የህሊና ደወል
መሰማት ተስኖት
የአምላክ ቃል ይፈርሳል።

ይሔው ነው ህመሜ
የእድሜያችን ጣሪያ
ሰማኒያ ላይሞላ
በሳር በቅጠሉ
ባፈር ስንባላ
እኔ ነኝ የኔ ነው
ማንነቴ እንትን ነው
የሚል እድር ፈላ
በሉ እስኪ ንገሩኝ
ማንነት ምንድን ነው?
ምንነት የቱ ነው ?

ሰው ከመባል ወዲያ
ምን ትርጉም ተገኝቶ?
ከአምላክ ፍጡር ውጭ
ምን ጠላት መጥቶ?

ምንድን ነው ነገሩ
ዝንትአለም መናከስ
ድምበር እያጠሩ
በመግባቢያ ቋንቋ
በትውልድ ቀየ ዘር እየቆጠሩ
ምንድን ነው ዘር መቁጠር
ዘር ማሳለይ እንጅ
ሰው ላይ ምን ያደርጋል
ማን በሀሩር ደርቆ
ማን በዝናብ ያድጋል?

አመሉ ነው እንጅ
ሞኝነት ነው እንጅ
ጥንትም ተፈጥሮውን
ሰው በአምላክ ካመነ
ማን ሀበሻን መርጦ
ማን ፈረንጅ ሆነ?
ከግዜሩ ሆኖ እንጅ
ፍጥረት የተሰጠ
ይሁንልኝ ብሎ
ማን ፆታ መረጠ።

ከአፈር ተፈጥሮ
አፈር የሚሆን ሰው
ከአፈር ጋር ታግሎ
አፈር የሚቆርሰው
ምነው? ይሄ ትውልድ
ከራስ የዘለለ ማስተዋል አነሰው ።

ይገርማል...
በማለዳ ፀሀይ
በምሽት ከዋክብት ቀን እየተዋጀ
ህዝቤ አንደጎበጠ
ቅን ሆኖ ቀን ሳያይ ሰማኒያውን ፈጀ።
አዎ እኔ ፍቅር ነው የራበኝ💔
ቼር ምሽት
🙏

#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot

7.9k 1 87 28
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Наш блог Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot