#Code_4
---ዳግመኛ ከመልካም ስብዕና ተወለድ!!
--------------------------------------------------
ሰው ሆነህ መኖርህ አንተንና ሌሎችን ካልጠቀመ ገና አልተወለድክም........!!የሰው ልጅ በፍጥረቱ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር ላይ ቢፈጠርም(ቢወለድም) ሰው ለመሆን ግን ከመልካም ስብዕና ማህፀን ዳግመኛ መወለድ ይኖርበታል።ብዙዎች ከዚህ ማህፀን ስላልተወለዱ (ስላልወጡ)ዛሬ ለምናያት ሀገራችን ችግር መንስኤ ሆነው እናያቸዋለን ከሀገርም አልፎ ለአለም የችግር ምንጭ ሆነው ይኖራሉ።
ሰው ሲኖር ለግሶ እንጂ ተቀብሎ መኖር የለበትም ከራስ በላይ በዙሪያው ለሚገኙ ሰዎች ኖሮ ማለፍ አለበት ሰው ሆኖ መገኘት ቀላል ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ ግን ሰው መሆንን ይፈራል.. ምክንያቱም ሰው በመሆን ውስጥ ስለራስ ጥቅም ማሰብ ስለሌለ,ሰው በመሆን ውስጥ ማግበስበስ ስለሌለ ሰው በመሆን ውስጥ ዬኔ የሚባል ነገር ስለሌለ ሰው በመሆን ውስጥ ራስን ማበልፀግ ስለሌለ...ሰዎች ሰው መሆንን ይፈራሉ ለዚህም ነው ዳግመኛ ከስብዕና ማህፀን ያልተወለዱ ሰዎች በኔነት ስሜትና በራስቸው ደስታ ብቻ መኖር የሚያስደስታቸው።
እነዚህ አይነት ሰዎች ከራሳቸው ዘላቂ ደስታ ውጭ የወንድማቸው ችግር ለነሱ ምንም ነው የሰውን ችግር መስማት ለነሱ ምቾት ይነሳቸዋል ስለዚህ በራሳቸው የተጣመመ የህይወት መንገድ ጉዟቸውን ያደርጋሉ።አንተ ግን ሰው ሁን ዳግመኛ ከስብዕና ማህፀን ተወለድ ከራስህ ደስታ ይልቅ ለሌሎች ደስታ ኑር ከራስህ በላይ ሌሎችን ወደህ ተገኝ ለሌሎች አርአያ ሆነህ የደስታቸው ምንጭ ለመሆን ጥረት አድርግ ለችግሮቻቸው የመፍትሔ ሀሳብ አቅርብ።ያኔ ሰው መባልህ ብቻ ሳይሆን ሰው ሆነህ መፈጠርህ ዘላለማዊ ጥቅሙ ይገባሀል።
በምድር ላይ ካንተ በላይ ደስተኛ አይኖርም በመጨረሻም በምድር ላይ ሰው ተብለህ መጥተህ ዳግመኛም በመልካም ተግባርህ ከስብዕና ማህፀን ተወልደህ ህያው መሆንህን ታረጋግጣለህ።
✍ገዛኸኝ መስፍን
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot