#ቀን_ሲጥል
ወር ሞላኝ ቤት ከተቀመጥኩ ከህመሜ ድኛለው ማለት ይቻላል በየቀኑ ሰምሃል ሳትደውል የዋለችበት ቀን ትዝ አይለኝም ሁሌ ትደውላለች ክላስ ትንሽ ተጨናንቀው ስለነበር መጥታ ለመጠየቅ አልተመቻትም ዛሬ ግን ከጓደኞቿና ከኪያር ጋር መጥተው እንደምትጠይቀኝ ነግራኛለች ያው ኪያር ሁሌ ቅዳሜና እሁድን እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር እነሰምሃልም ቤታችንን ስለማያውቁት ይዟቸው ይመጣል።
ቤት ውስጥ መቀመጥ ሲሰለቸኝ ውጪ ወጥቼ ከቧንቧው በጎማ አድርጌ አትክልቶቹን ውሃ እያጠጣው እያለ ታናሽ እህቴ ከፀጉር ቤት መጣች አምሮባታል እየሳቅኩ ምን ተገኘ እንዴ ዛሬ አልኳት እሷም እየሳቀች በፍጥነት ኪያር ይመጣል አይደል ዛሬ? አለችኝ እቺን ይወዳል ለኪያር ነው እንዲ ፏ ያልሺ ሃ..ሃ..ሃ... ኪያር እኮ እኔን ሊጠይቅ ነው የሚመጣው አንቺ ምን ቤት ነሽ እምትኳኳይው ብዬ ሳቅኩባት አኩርፋኝ ለምቦጫን ዘፍዝፋ ገባች እኔም እየሳቅኩ ታናሽ እህቴና ኪያር ምን አይነት ጥንዶች ሊሆኑ እንደሚችሉ እያሰብኩ በሳቅ እየፈረስኩ አትክልቶቹን ማጠጣት ቀጠልኩ በርግጥ ኪያር በጣም ጥሩ ልጅ ነው ከእህቴ ጋር አንድ ላይ ቢሆን ምንም ቅር አይለኝም። እንዲ ብዙ እያወጣው እያወረድኩ እያለ አንድ ላዳ ታክሲ በራችን ጋር አቆመ እያጠጣሁበት የነበረውን ጎማ ሰብስቤ ማን እንደመጣ ለማየት ወደ ላዳዋ ሄድኩ እነ ስምሃል እና ኪያር ናቸው።
ሰምሃል ከመኪናው ወጥታ እየሮች መጥታ አቀፈችኝና አንገቴን ሳመችኝ በየቀኑ በስልክ ስናወራ ስለነበር በጣም ተቀራርበናል ሁሌም ስለኤቤጊያ ሳልጠይቃት አልውልም ምን እንደሰራች ከማንጋር እንደዋለች እየጠየቅኩ አሰለቻታለው ዶርም ውስጥ ሆና ስታወራኝ ደሞ ጓደኞቿ ሊዲያ እና ራኬብ ስልኳን በግድ እየቀሙ ያወሩኛል ሶስቱም ደስ እሚሉ ጓደኛሞች ናቸው ፍቅራቸው ያስቀናል። ኪያር ሊዲያና ራኬብም እየተሳሳቁ መጥተው ሰላም አሉኝና ተያይዘን ወደቤት እየገባን እያለ ኪያር ጮክ ብሎ እንግዲ ይህ የምታዩት ትልቅ የተንጣለለ እልፍኝ የጋሽ ናኦል እልፍኝ ነው ቤተመንግስ አይደለም እንዳትደናገጡ እሺ አላቸው ወደነስምሃል ዞሮ እያየ ሁሉም ሳቁ። ለእናቴ ዛሬ ጓደኞቼ ሊጠይቁኝ እንደሚመጡ ስለነገርኳት ለነሱ እሚሆን አሪፍ ምሳ እያዘጋጀች ነበር በአንድ ወር ውስጥ ከኪያር እና የቅርብ ዘመዶቼ ውጪ ማንም ሊጠይቀኝ የመጣ ሰው አልነበረም ብቸኛ የሆንኩ ያህል ነበር የሚሰማኝ። እናቴ ልክ ስትወጣ ኪያር ድምፁን ዝግት አድርጎ ዝም አለ እናቴ ሰላም አለቻችው ሰምሃልዬ የኔ ቆንጆ እንዴት ነሽ በደህና መጣችው አይደል አለቻት እናቴ ሰምሃልን በጣም ትወዳታለች ህይወቴን ስላተረፈችልኝ።
አንድ ቀን እንደውም ለምን እሷን አታገባም ቀለበት አድርግላት በጣም ጥሩ ልጅ እኮ ናት ብላኝ በሳቅ ፍርስ ስታረገኝ ነበር እናቴ ጣጣ የለባትም ፈታ ያለች ናት ነገር አታከርም። አይ እማ ጉዴን አላወቀች እንዴት በሌላ ሴት ፍቅር እንደምሰቃይ። ሳሎን ውስጥ ቁጭ ብለን እህቴ ዝንጥ ብላ ከላይ መጣች እኔ ስለገባኝ ከት ብዬ ሳቅኩ መጥታ ሁሉንም ሰላም አለቻቸው እሷ ሰላም ስትላቸው እኔ የኪያርን ሁኔታ እያየው ነበር በመሃል አቅቶኝ ድጋሚ ፍርስ ብዬ ሳቅኩ ሁለትም እንደሚዋደዱ እማውቀው እኔ ብቻ ነኝ ደስ ሲል። እህቴ መጥታ ከኔ አጠገብ ተቀመጠች። ወሬ ለማስጀመር ይመስል ኪያር አንተ በጣም ተስማምቶህ የለ እንዴ ወዝህ መለስ አለ ዛሬ ደሞ እንዴት ነው በሸበጥ እና ቁምጣ አለኝ እህቴ ስትቅለበለብ ናዲ እኮ እንዲ ነው ቅዳሜና እሁድ ቀለል ያለ ልብስ ነው ሚለብሰው ደሞ እቺን ነጭ ቁምጣ ሲወወወ..ዳት አለችው ፍጥነቷ አስደንግጧት ዝም ብላ ትንሽ ከቆየች በኃላ እናቴን ላግዛት ለናንተ ዶሮ እየሰራች ነው አለቻቸውና ተነስታ ወጣች።
ልክ እንደወጣች ሊድያ ወደኔ እያየች ደስ እምትል እህት አለችህ አለችኝ እኔም እየሳቅኩ አው ባክሽ እንዲ ናት ብዙ ግዜ ቅልብልብ ናት አሁን 12ኛ ክፍል ናት ያው ስትጨርስ እኛ ጋር ትመጣለች አልኳት ሰአቱ ገና ረፋድ ስለነበር ጨዋታችንን ቀጠልን በጨዋታችን መሃል ወደሰምሃል ዞሬ ኤቤጊያ እንዴት ናት አልኳት ፈገግ እያለች ደና ናት አለችኝ። ርብቃ እንደመቆጣት እያለች የት አናግረሻት እምታውቂውን ነው ደና ናት ምትይው እስካሁን እንደተኮራረፋችው አይደል እንዴ ብላ አፋጠጠቻት። ሁለቱ እየተከራከሩ እያለ በመሃል አቋረጥኳቸውና ሰምሃልን ምን ሆናቹ ነው የተኮራረፋቹት ስላት ዝም አለችኝ ወደ ርብቃ ስዞር እኔ ምን አውቄላት እቺ ዝምብላ ከመሬት ተነስታ ነው የዘጋቻት አለችኝ አይኗን እያጉረጠረጠች። ዝምታው ሲበዛ በቃ የዛኔ አንተን ደባሪ ንግግር ስለተናገረችህ አናዳኝ ነው ያኮረፍኳት አለችኝ።
ይቀጥላል ....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot