📢 እንደምን አደራችሁ፣ ዛሬ ወሳኝ በሆነ ርዕስ ላይ የተጻፈ ጹሑፉ ላጋራችሁ ነው፤ ለመሆኑ ፕረዘንቴሽን ላይ የሚፈጠረውን ፍርሀትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን❓
Here it is ...🙌🏾
ፕረዘንቴሽን በትምህርት ሂወታችን ውስጥ ከሚያጋጥሙን ሂደቶችና የመፈተኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው።በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ላይ መምህራን አሳሳይንመንቶችን፣
ፕሮጀክቶችን፣ የምርምር ስራዎችን እና የመሳሰሉትን ተማሪዎች በክላስ ውስጥ ፕረዘንት እንዲያደርጉ ይጠይቃሉ፡፡
ከትምህርት አለም ውጪም በተለያዮ የስራ ጉዳዮች ላይ ፕረዘንት እንድናደርግ ሊጠበቅብን ይችላል፡፡
ታዲያ በፕረዘንቴሽን ጊዜ የብዙዎች ችግር ፍርሀት ነው፡፡ሰው ፊት ቆሞ የመናገር ፍርሀት፡፡
የፕረዘንቴሽን ፍርሀት የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እስከ 80% የሚሆኑት ሰዎች ጋር ያለ ችግር ነው፡፡ በእርግጥ ችግር ነው ተብሎም ሊነሳም አይችል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መምህራንን ጨምሮ የ public speaking ልምድ ያላቸው አርቲስቶች፣ ፓለቲከኞች፣ የሀይማኖት መሪዎች ሁሉ የሚጋሩት common ስሜት ስለሆነ ነው፡፡
ይህ የፕረዘንቴሽን (public speaking) ፍርሀት ጤናማ ስሜት ነው፡፡ የሁሉም ሰው የጋራ ሰሜትና እንዲያውም የራሱ ጥቅሞችም ያሉት ስሜት ነው፡፡ ችግር የሚሆነው ፍርሀቱ በጣም ከበዛና ቅጥ ካጣ ነው፡፡
የሚከተሉት መንገዶች የፕረዘንቴሽንን ፍርሀት ለመቀነስና ውጤታማ ፕረዘንቴሽን ለማድረግ ያግዛሉ፡፡
1. የፕረዘንቴሽን ፍርሀት ጤናማና common ስሜት እንደሆነ መረዳት። Literally ሁሉም ሰው ይፈራል፡፡ ልዮነቱ አንዳንዶች ማኔጅ ያደርጉታል አንዳንዶች አያደርጉትም፡፡ይህ የፍርሀት ስሜት ሊያስደነግጠን ሳይሆን በደንብ እንድንዘጋጅ ሊያመላክተን ይገባል፡፡ፍርሀት ጥቅም አለው፡፡ ይሄውም ባዮሎጂካሊ በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞንን መጠን ከፍ በማድረግ የበለጠ ኢነርጂ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
2. ፕረዘንቴሽን ልምምድ (rehearsal )
ፕረዘንቴሽን ልምምድ ይፈልጋል፡፡ ፕረዘንት የምናደርገውን ነገር በደንብ ማወቃችንን፣ ቋንቋችንን፣ ድምፃችንን እንዲሁም ሰአት አጠቃቀማችንን የምናስተካክለው በልምምድ ነው። ፕረዘንት የሚያደርግ ሰው ልክ እንደ መድረክ ተዋናይ ነው፡፡ ፕረዘንቴሽንም በራሱ በተወሰነ መንገድ ትወና ነው፡፡
.
በመሆኑም ማንም ተዋናይ በደንብ ሳይለማመድ መድረክ ላይ እንደማይወጣ ሁሉ ፕረዘንት የሚያደርግ ሰውም በበቂ ሁኔታ ልምምድ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
በምንለማመድበት ጊዜ ጓደኞቻችን ፊት ሊሆን ይችላል ወይም ብቻችንን ቆመን ሰው ፊት እንዳለን በማሰብ መለማመድ ይቻላል፡፡" Practice makes perfect"
3. መረጋጋት፣ እራስን ማረጋጋት
4. በቂ አየር መውሰድ ፣ መተንፈስ
5. ፕረዘንት የምናደርግበትን ቦታና መምህራኑን ቀድሞ ማወቅ፡፡ ይህም ሲባል ፕረዘንት የምናደርግበት ቦታ ቀደም ብለን በመሄድ ማየትና የምንቆምበትን ቦታ ስሜቱን መረዳት ነው፡፡
6. አለባበስን ማስተካከል፡፡ ጥሩ አለባበስ በራስ መተማመንን ይጨምራል፡፡
7. ፕረዘንት የማድረግ ፍላጎትን ማዳበር፣ ይህም ሲባል ፕረዘንቴሽንን እንደ ግዴታ ሳይሆን የሰራነውን ነገር ለሰዎች እንደምናሳይበት እንደ ጥሩ አጋጣሚ መውሰድ፡፡
8. በቂ አረፍት ወስዶ መገኘት
9. ቀደም ብሎ መገኘት (አለማርፈድ)
10. ከመጀመሪያው ውጤታማ ስራ መስራት፡፡ ምክንያቱም የአንዳንዶች የፍርሀት ምንጭ በቂ ስራ ካለመስራትና ካለመዘጋጀት ነው፡፡
©Psychology Zone
@Qesem_University