ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


Join @Rovibook
😎

/\
👢👢
መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው!!
ለማንኛውም ማስታወቂያ ነክ ጉዳዮች @RASNAMRUD ያናግሩን

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций






ደራሲ አሌክስ አብርሃም ታሪክ ሲያዋቅር ለጉድ ነው። በጥቂት ገጾች ርቀት ውስጥ ከገጸ ባሕርያቱ ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዲኖረን ያደርገናል። የራቀውን አቅርቦ፥ የቀረበውን ደግሞ እያራቀ ያሳየናል። ቢፈልግ እያዝናና፥ ቢያሻው እያስለቀሰ ያስተምረናል።

በዚህ ሳምንት "አልተዘዋወረችም" የተሰኘውን መጽሐፉን ይሸምቱ ብለን ጥቆማችንን ሰጥተናል። የእርሱን ሌሎች ሥራዎች መግዛት ለምትሹ ደግሞ፥ ሁሉንም መጻሕፍቱን ሰብሰብ አድርገው ከወሰዱ፥ በልዩ የቅናሽ ጥቅል እናስተናግድዎታለን!

#book_world
#ከመጽሐፍ_ዓለም 🌍🌍


ንባብ ነጻነትን ያቀዳጃል!

ብዙዎቻችን በልጅነታችን የፊደል ገበታን የመቁጠር እድልን አግኝተናል። ይህም የንባብ ችሎታን አጎናጽፎን መጻሕፍትን ማንበብ እንችላለን። ይህ እድል ባይኖረን ኖሮ ብላችሁ አስቡት። ለፍሬድሪክ ዳግላስ ግን ሕይወት በፊደል እውቀት ያልታጀበች ነበረች። በባርነት ውስጥ ከሚማቅቁ ወላጆች የተወለደው ፍሬድሪክ፥ መማር ስለማይፈቀድለት፥ የሚከፍለውም ስላልነበረው፥ ምግብ ለሌላቸው የነጭ ማኅበረሰብ ድሃ ልጆች እንደክፍያ ዳቦ እየሠጠ በድብቅ ይማር ነበር። 

ይህ ሰው በንባብ እየጎለመሰ ሲመጣ፥ ከሚያነባቸው የተለያዩ ጽሑፎች ውስጡ የነጻነት ሐሳቦችን ይመለከት ጀመር። ይህም ደግሞ ጨቋኞችን አምርሮ እንዲጠላ አደረገው። ከባርነት ካመለጠ ወዲያም በሁሉም ዘንድ የሚፈለግ ተናጋሪ እና የጥቁሮች መብት ተሟጋች ለመሆን ቻለ። የፍሬድሪክ ዳግላስ የነጻነት ጉዞ የተጀመረው ከንባብ ነበር። እርሱም ሲናገር "ማንበብ ከቻላችሁ ለዘለዓለም ነጻነትን ትቀዳጃለችሁ" ይል የነበረው ለዚህ ነበር። 

ለመሆኑ እርስዎስ? "እንኳን ማንበብ ቻልኩ!" ያሉበት አጋጣሚ ነበር?

#ከመጽሐፍት ዓለም 🌍


ከመጽሐፍ ጋር የተያያዘ ሌላ ልዩ ቃል ደግሞ ይዘን መጣን!

"ቢብሊዮስሚያ" ማለት የመጻሕፍት ገጾች መዓዛ ማለት ነው። በተለይ ደግሞ የድሮ መጻሕፍት ያላቸው ልዩ ሽታ የማይረሳ እንደሆነ አንባቢዎች ሲናገሩ ይሰማል። ለመሆኑ፥ እርስዎ እስካሁን መዓዛው በአፍንጫዎ ውል የሚልብዎት መጽሐፍ የለም?

እርግጠኛ ነን፥ ይኖራል! እስቲ ስለ መጽሐፍ መዓዛ የሚያወራ ጓደኛ ካለዎት ይህንን ፖስት አጋሯቸው!

#ከመፅሐፍት_ዓለም

9k 0 13 6 30

'የሕይወቴ ብሩህ መልክ፥ ጨፍጋጋ መልክን ለበሰ። እናም ጨለማን መጋፈጥ ነበረብኝ። በሐሰተኛ ብርሃን ውስጥ መኖር የለመዱ ዓይኖቼ በእውነተኛ ጨለማ ውስጥ ተጥበረበሩብኝ። ድንጋጤ ወረደብኝ። ላለማመን ፈልጌ ነበር። ጸንቼ መቆምና መራመድ አልቻልኩም። ሀሞቴ ፈሰሰ። እንደ እጄ መዳፍ የማውቀው፥ በውብ ቀለማት ያጌጠና የተንቆጠቆጠ የሚመስለው ዓለም ክንብንቡ ተገፈፈ።'

-- ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? (ደራሲ እሱባለው አበራ ንጉሤ)

መደብራችንን ይጎብኙ! በጥሩ ቅናሽ እና በመልካም አቀባበል እናስተናግድዎታለን!

#ከመፅሐፍት ዓለም
#ምርጥ_ንባብ


አንዳንድ ሰዎች "ልብወለድ ማንበብ ለምን ይጠቅማል?" ብለው ይጠይቃሉ።

በንባብ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፥ ልብወለድ አንባቢያን ልብወለድ ከማያነቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ የሌሎችን ስሜት መረዳት (Empathy) ላይ የተሻለ ሆነው ይገኛሉ። በእያንዳንዱ ገጸ ባሕርይ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን ስለሚያስቡ፥ የስሜት ውጣ ውረዱ በራሱ ስሜትን የማስተናገድ እባ የመረዳት አቅማቸውን የተሻለ ያደርገዋል። ይህ እንግዲህ ልብ ወለድ ማንበብ ካሉት ብዙ ጥቅሞች መካከል አንዱ ነው።

ምን ለማለት ነው? ጥሩ ጥሩ የልብ ወለድ መጻሕፍትን አዘጋጅተን እየጠበቅንዎ ነውና፥ ጎራ ብለው ይሸምቱ!




Репост из: የንባብ ሱሰኞች
እንዲህ ያለ ወርቃማ እድል ቢሰጥዎት ከማን ጋር ራት ይበሉ ይሆን? እስቲ ከጓደኞችዎ ጋር ይወያዩበት!

#የንባብ_ሱሰኞች
#የንባብ_ሱሰኞችን_እንፈጥራለን
#reading_addicts


Репост из: የንባብ ሱሰኞች
#የንባብ_ሱሰኞች


Join @kazinpharm12 for better life


Репост из: Неизвестно
👉የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ አሪፍ ቻናል ይቀላቀሉ ❗


ዉድ ደንበኞቻችን ከማንኛውም ጤና ተቋማት የታዘዙላችሁን መድሀኒቶች ማዘዣውን በፎቶ በመላክ መድሀኒቶችን ያለምንም ድካምና መንከራተት ያሉበት እናደርሳለን  ከገበያ ላይ በቀላሉ መገኘት ያልቻሉትን መድሀኒቶች ፈልገን እናቀርባለን

ድካሞን ቀንሰው ጤናዎን ይጠብቁ !

Photo ለመላክ comment box አልያም @Rovi_Ben ላይ መጠቀም ይችላሉ

ለወዳጅ ዘመዶ share ማድረጉን አይርሱ        
kazin pharmacy

@kazinpharm12 @kazinpharm12 ይቀላቀሉን


ይሉኝታ
አቤት...ህፃንነት ያለው  ጥረት ትጋት
ተወላግዶ መውደቅ ተኮላትፎ ማውራት
ደግሞ እየወደቁ ደጋግሞ መነሳት .....
እኔ ግን አሰብኩት.......
እንዳሁኑ ባስብ በህፃንነቴ
መዳህ ላይ ነበርኩኝ አሁን በጉልበቴ
ማውራትም አልችልም ቃላቶች አውጥቼ
እንዳይሳቅብኝ፤ መሞከሬን ትቼ


Bewuket S


የወቶአደር ቅኔ


ከአምባው ላይ ቆሜ
ከሰላሙ ፍቅርሽ ትዝታን ቀስሜ
በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
አልታየኝ ይሆናል ፂሜም ሲያቀመቅም

ችግር በቆፈረው በቀበሮ ጉድጓድ
የአረሩን ፉጨት በጣቶቼ ሳግድ
በእንዲህ ያለ ኑረት ያ ልቤ ቢዛክር
አይቻለው ጎኔ ሳያስብሽ ሊያድር

ፈገግታሽን ቋጥረሽ ላኪልኝ በአህያ
ውብ አይንሽን ላኪው ይደር ከእኔ ጉያ
ፈገግታሽ በሶዬ ህይወቴን ማቆያ
ስንደዶ ፀጉርሽን ላኪልኝ እባክሽ
የጠላት መትረየስ ሲንደቀደቅ ቢያድር ተከልዬ ልሽሽ
ውብ ከንፈርሽ ይምጣ ባይኔ ይበል ውልብ
ጠላት ማርኮ ከቦኝ ይሰማኝ የልብ ልብ
ትንፋሽሽን ላኪው ህመሜን ማበሻ
ይሆነኛል እና ለቁስሌ ፋሻ

አንቺ የአይኔ አበባ
በኔ ስጋት ምድር ወዲያ ዳር ያልሽው
ቅዠት ብቻ ሆኗል ሰሞኑን የማየው

እንጃ እኔን ዘንድሮ (፪)
የጥይት ዝናማት በኔ ባይዘንቡብኝ
ናፍቆትሽ ነው ቀድሞ አፈር የሚያለብሰኝ
ፍቅርሽ ጢያራ ነው ክንፍ አውጥቶ በሯል
ከጠላቴ በላይ ዙሪያዬን ከቦኛል
ናፍቆትሽ አዜብ ነው ያነጋግረኛል
በአድማስ ሹክሹክታ ድምፁን ያሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል
ድምፁ ይሰማኛል

በተራራው አናት በተኙ ጉሞች ላይ
እንደእኔ ሆድ ብሶት ከሚያለቅሰው ሰማይ
መሀከል ላይ ቆሜ ትዝታን ሳስታምም
ባክሽ ተሰቃየው ህይወት ሆናኝ አረም

እናልሽ አንቺዬ
#እኔ በሀገሬ ወቶአደር ነኝ አሉ
ለሀገራቸው ሲሉ ነፍሴን ከማይሉ
አጠገብ ምመደብ (፪ )

ስጋዬ ጦር ሜዳ ፍቅርሽን ያቀፈ
ልቤ ካንቺ ጋር ነው በናፍቆት ያደፈ
ልቤ ከኔ የለም ሆኗል ወጥቶ አዳሪ
ስጋ ብቻ ለጦር #ይህን_ጊዜ_ፍሪ_(፫)

✍️✍️ሲራክ

@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹


sharing is carring...😊😊


ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች👨‍👨‍👧👨‍👨‍👧‼️‼️
      በእዚህኛው አዲስ አመት ለእናንተ የሚሆን ጥሩ ውድድር አዘጋጅተናል።
      የእዚህ ውድድር  አሸናፊ ለመሆን
      1⃣....ወደ እዚህ channel የቻሉትን ያህል ሰው መጋበዝ 
      2⃣.....በመቀጠል የጋበዛችሁትን ሰው መጠን በማስረጃ መያዝ
      3⃣........ከዛማ ምን ትጠብቃላችሁ @RASNAMRUD በውስጥ መስመር ላኩልን
 
የዚህን ውድድር አሽናፊ ሰንገልጽ ከነ ማስረጃው ስለሆነ  ምንም መደበቅ የለም!!
       💥💥ማሰባሰቢያ 💥💥
         ##  የአሸናፊዎች ብዛት 5  ነው።
         ##  በእዚህኛው ውድድር ያሽነፉ ሰዎች  በቅርቡ በከፈተው የልብስ መሸጫ channel ለይ
                የgive away ተሳታፊለመሆን ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።


ውድድሩ ይህን መልእክት ካነበባችሁበት ሰአት ይጀምራል።
         መልካም እድል🍀🍀

@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹


መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን🌼🌼
      በአዲሱ አመት የታመመው ድኖ፤
      የጠፋው ተገኝቶ፤
      ሀገራችንን ከገባችበት መከራ አውጥቶ፤
      በአመክንዮ እንጂ በአሉባልታ የማናም
      ፍጹም ምክንያታዊ ሰው የምንሆንበት           
       አመት ያድርግልን🌼🌼🌼
@ከመጻሕፍት ዓለም
🇪🇹@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹


ርዕስ ? አንባቢ ያውጣ
አዳሞች ሆይ ንቁ ሄዋንን ጠብቋት
ይዛችኋት ሂዱ ስትወጡ መዝናናት
ተማሩ ከታሪክ አትድገሙ ስህተት
አዳም እግር ጥሎት ለሰከንድ ሲለያት
      እባብ ጀነጀናት
      እራትም ጋበዛት
      የንቀቷ ንቀት
ወደቤቷ መጣች ቴክ አዌ ይዛለት
አያድርስ ነው ብቻ የሄዋንስ ድፍረት

Just for fun😂😂
#Share
#share

✍Bewuket S


ዋ!
ቀጥረሽ ማስጠበቁ ኩራት አይሁንልሽ
ዋ!... አንቺ ልጅ እንዳትረሽ
እሷን ስጠብቅ ነው አንቺን ያገኘሁሽ
እናማ ቆንጅዬ ምን ልልሽ መሰለሽ
አንቺ እንደተካሻት መተ'ካት ካልፈለግሽ
የተቀጠርሽበት በሰዓቱ ድረሽ

Bewuket S
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
@ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

Показано 20 последних публикаций.

26 615

подписчиков
Статистика канала