ንባብ ነጻነትን ያቀዳጃል!
ብዙዎቻችን በልጅነታችን የፊደል ገበታን የመቁጠር እድልን አግኝተናል። ይህም የንባብ ችሎታን አጎናጽፎን መጻሕፍትን ማንበብ እንችላለን። ይህ እድል ባይኖረን ኖሮ ብላችሁ አስቡት። ለፍሬድሪክ ዳግላስ ግን ሕይወት በፊደል እውቀት ያልታጀበች ነበረች። በባርነት ውስጥ ከሚማቅቁ ወላጆች የተወለደው ፍሬድሪክ፥ መማር ስለማይፈቀድለት፥ የሚከፍለውም ስላልነበረው፥ ምግብ ለሌላቸው የነጭ ማኅበረሰብ ድሃ ልጆች እንደክፍያ ዳቦ እየሠጠ በድብቅ ይማር ነበር።
ይህ ሰው በንባብ እየጎለመሰ ሲመጣ፥ ከሚያነባቸው የተለያዩ ጽሑፎች ውስጡ የነጻነት ሐሳቦችን ይመለከት ጀመር። ይህም ደግሞ ጨቋኞችን አምርሮ እንዲጠላ አደረገው። ከባርነት ካመለጠ ወዲያም በሁሉም ዘንድ የሚፈለግ ተናጋሪ እና የጥቁሮች መብት ተሟጋች ለመሆን ቻለ። የፍሬድሪክ ዳግላስ የነጻነት ጉዞ የተጀመረው ከንባብ ነበር። እርሱም ሲናገር "ማንበብ ከቻላችሁ ለዘለዓለም ነጻነትን ትቀዳጃለችሁ" ይል የነበረው ለዚህ ነበር።
ለመሆኑ እርስዎስ? "እንኳን ማንበብ ቻልኩ!" ያሉበት አጋጣሚ ነበር?
#ከመጽሐፍት ዓለም 🌍