ሌላ ሴት ልታገባ ያልክ ቀን እንኳ ብደውልልህ እሷን ትተህ እኔ ጋር ነው አይደል የምትመጣው? እለዋለሁ ሁሌ …. ፈገግ ብሎ ያየኝና “ደፋር ኮ ነሽ….ይለኛል።
ካለሁ ነገር ሁሉ እኔን አስበልጦ እንደሚወደኝ አውቃለሁ ሲሳሳልኝ ከራሱ ሲያስቀድመኝ ሲጨነቅልኝ ለኔ ሲኖር አይቻለሁ በእርግጥ እንዲ ማለት ከባድ ይመስላል።
እኔ ግን አይኑን ሳያርገበግብ ይሄን ልጅ ግን ምን አስነክታው ነው እስኪባል የሚያውቁን ሁሉ እስኪገረሙ ድረስ ….ሳናድደዉ ሳበሳጨው ችሎ በክፉ ቀናቶቼ ላይ ለደስታዬ ሲፈጋ አብሮነታችንን ለማቆም ብዙ ሲለፋ አውቅ ነበር።
ይመስለኛል የበዛ መውደዱ የትም አይሄድም ብዬ እንዳስብ ለኛ እንዳልጨነቅና በተወዳጅነት ተኮፍሼ ለሚሰጠኝ መውደድና ክብር ትንሽ እንኳ አፀፌታን መስጠት የማልችል ሴት አደረገኝ።
ከዛ በአንዱ ቀን በትንሽ ነገር ተጋጨንና ….ሂድልኝ አልኩት...ለመነኝ አስለመነኝ….ከቀልቤ መሆን ያልቻልኩት እኔ ግን ግድ አልሰጠኝምና ምንም እንደጎደለብኝ አልተሰማኝም መሄዱ እንደሚያም እንዴት እንደሚናፍቀኝ ለመረዳት ብዙ ረፈደብኝ።
ሄደ ከዛ አልተመለሰም ልመልሰዉ ሞከርኩ….መሄድ አለማምጄው ኖሮ መመለስ አቃተኝ።
እናማ አሁን የገፋሁት እኔ ወዶኛል አይጠላኝም ያልኩት እኔ በተራዬ እጅግ እየናፈቀኝ:እያመመኝ እያስመሰልኩ አብሮነታችን ማክበር ያልቻልኩት እኔ … ሲያቅፈኝ ህይወት እንደሚቀለኝ ችግሮቼን ችሎ ማሸነፍ ብቻን ያለማመደኝ እሱ እንደነበር በጣም እንደሚናፍቀኝ በጣም እንደማመሰግነው ያልነገርኩት እኔ የሄደበትን ቀን ሻማ እያበራሁ አከብራለሁ።
በስመአብ ጊዜው እንዴት ይሮጣል? አትመጣም በቃ?🙄🙄🙄🙄
✍ By MaHi
------------------------------------------------
ግድ የላችሁም በኔ ይሁንባችሁ ...ዝም ብላችሁ ቤተሰብ ሁኑ
👇👇
🗣 @Sewsinor