🤓 ሰው ሲኖር-Sew Sinor‍


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


💟 እንኳን በደህና መጡ። 🙏 ቸር አይለፋችሁ ክፉ አያግኛችሁ
😊😍 ገፁን ከተቀላቀሉበት ሰከንድ አንስቶ እጅጉን ጠቃሚ ነገሮችን ያገኙበታል።
በተጨማሪ📚 በpdf ማግኘት የሚፈልጉት ማንኛውም መፅሐፍ ካለ 👉 @Sewsinor1_bot ይጠቀሙ።
ማስታወቂያ ለማሰራት፣ማንኛውም ጥያቄ ፣ ሀሳብ ፣ አስተያየት ለመስጠት👇 Inbox 👇
👉 @Sewsinorbot
👉 @CheramlakT

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций






👉🏽👉🏽👉🏽 የ #ገና #ጾም (የ #ነቢያት ጾም) #ወቅት#ቤተክርስቲያን እንዴት ይገለጻል?

(ክፍል 2)

የዘመነ አስተምህሮ ሰንበታት (እሑዶች) ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ስያሜ ጋር ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ልዩነታቸውን ለማነጻጸርና ለመረዳት እንዲያመቸንም በእነዚህ ሰንበታት የሚነገረውን ቃለ እግዚአብሔር ይዘት እንደሚከተለው በአጭሩ እንመለከታለን

1. አስተምሕሮ
የመጀመሪያው የዘመነ አስተምሕሮ ሳምንት  "አስተምሕሮ"  ይባላል፣ ይህም ከኅዳር 6 – 12 ያሉትን ሰባት ቀናት ያካትታል፡፡

በዕለቱ (እሑድ) የሚቀርበው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር፦

👉"ኢተዘኪሮ አበሳ ዚአነ ኢኀደገነ ፍጹመ ንማስን ….(ኀጢአታችንን አላሰበብንም፤ እንጠፋ ዘንድም ፈጽሞ አልተወንም ….)" የሚለው ሲሆን፣ በተጨማሪም 

👉"ፈጽም ለነ ሠናይተከ እንተ እምኀቤነ ….፣ (በአንተ ዘንድ ያለችውን በጎነት ፈጽምልን ….)" የሚለውም እንደ አማራጭ ሊቀርብ ይችላል፡፡

👉ምስባኩ "ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ (የቀደመውን በደላችንን አታስብብን አቤቱ ምሕረትህ በቶሎ ያግኘን እጅግ ተቸግረናልና )" መዝ.78፥8 የሚለው የዳዊት መዝሙር ነው

👉ወንጌሉ ማቴ.6፥5-16 ሲሆን፣ ቅዳሴውም ቅዳሴ እግዚእ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት እግዚአብሔር አምላካችን ከአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዓመት የመርገምና የጨለማ ዘመን ዓለምን ማውጣቱ፣ ቸርነቱ፣ ርኅራኄውና ትዕግሥቱ እንደዚሁም ምእመናንን ከሞተ ሥጋ ከሞተ ነፍስ ማውጣቱ ይነገርበታል፡፡

2. ቅድስት፦ ከኅዳር 13 – 19 ያሉትን ሰባት ቀናት የሚያካትተው የዘመነ አስተምሕሮ ሁለተኛው ሳምንት "ቅድስት" ይባላል።

ቅድስት የተባለበት ምክንያትም ሰንበትን ለቀደሰ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ እንደሚገባ የሚነግርበት ሳምንት መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ዕለት (እሑድ) 

👉"ሎቱ ስብሐት ወሎቱ አኰቴት ለዘቀደሳ ለሰንበት …. (ሰንበትን ላከበራት ለእርሱ ክብር ምስጋና ይኹን (ይድረሰው፣ ይገባዋል) ….)" የሚለው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ይቀርባል።

👉በቅዳሴ ጊዜም "ኩሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር በሰማይኒ ወበምድርኒ በባሕርኒ ወበኩሉ ቀላያት፤ (በሰማይና በምድር፣ በባሕርና በጥልቆችም ሁሉ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ)" መዝ.134፥6 የሚለው ምስባክ ይሰበካል

👉ወንጌሉ ዮሐ.5፥16-28 ሲሆን ቅዳሴው ደግሞ አትናቴዎስ ነው፡፡

በዚህ ሳምንት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስትነት እና ሰንበትን ስለቀደሰ ስለ እግዚአብሔር ቅድስና ሰፊ ትምህርት ይቀርባል፡፡

✍በአንጻሩ በዓቢይ ጾሙ ቅድስት፦

👉 መዝሙሩ፡- ግነዩ ለእግዚአብሔር"

👉ምስባኩ፡- "እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ (እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ እምነትና በጎነት በፊቱ፣ ቅድስናና የክብር ገናናነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው)"
መዝ.95፥5-6


👉ወንጌሉ፡- ማቴ.6፥16-25 ቅዳሴው ደግሞ ኤጲፋንዮስ ነው፡፡

✍በዚህ ሳምንት የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር ይቅር ባይነትና ለእርሱ ስለ መገዛት፣ ስለ ቅድስና እና ስለ ክብረ ሰንበት የሚያስረዳ ነው፡፡

 3. ምኩራብ ሦስተኛው የዘመነ አስተምሕሮ ሳምንት "ምኩራብ" የሚባል ሲሆን ይህም ከኅዳር  20 – 26 ያሉትን ሰባት ቀናት የሚያካትት ሳምንት ነው፡፡

👉
በዕለቱ (እሑድ) የሚቀርበው መዝሙር፡- "አምላክ ፍጹም በህላዌሁ ዘሀሎ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ….፤ (ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የነበረው አምላክ (እግዚአብሔር) በህልውናው (አነዋወሩ) ፍጹም ነው ….)"  የሚለው ሲሆን፣

👉ምስባኩም፡- "ቅረቡ ኀቤሁ ወያበርህ ለክሙ ወኢይትኀፈር ገጽክሙ ዝንቱ ነዳይ ጸርሐ እግዚአብሔር ሰምዖ (ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማልፊታችሁም አያፍርም ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔርም ሰማው)" መዝ.33፥5-6  የሚል ነው።

👉ወንጌሉም ማቴ. 8፥28 እስከ መጨረሻው ድረስ ነው፡፡ ቅዳሴው ደግሞ እግዚእ፡፡

በዚህ ሳምንት ጌታችን፣ አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራበ አይሁድ ሕዝቡን እየሰበሰበ ማስተማሩ፣ ባሕርና ነፋሳትን መገሠፁ፣ አጋንንትን ከሰዎች ማውጣቱ ይነገራል፡፡

✍በዓቢይ ጾሙ ምኵራብ መዝሙሩ፡- "ቦአ ኢየሱስ ምኩራቦሙ ለአይሁድ"

👉ምስባኩ፡- "
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀፃዕክዋ በጾም ለነፍስየ (የቤትህ ቅናት በልቶኛልና፣ የሚሰድቡህ ስድብም በላዬ ወድቋልና ሰውነቴን በጾም አደከምኋት)"
መዝ.68፥9-10


👉ወንጌሉ፡- ዮሐ.2፥12 እስከ ፍጻሜው ሲሆን ቅዳሴው ግን ተመሳሳይ (ቅዳሴ እግዚእ) ነው፡፡

በሳምንቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራበ አይሁድ ማስተማሩንና በቤተ መቅደሱ ዓለማዊ ሸቀጥ ይለውጡ የነበሩ ገበያተኞችን ማስወጣቱን የሚመለከት ትምህርት ይቀርባል፡፡

ይቀጥላል (ክፍል 3)
    👇

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወለዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!

@Sewsinor @Sewsinor


እግዚአብሔር ይመሰገን
የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደ ሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል


👉🏽👉🏽👉🏽 የ #ገና #ጾም (የ #ነቢያት ጾም) #ወቅት#ቤተክርስቲያን እንዴት ይገለጻል?

(ክፍል 1)

✍በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዘመን አከፋፈል መሠረት

👉ከኅዳር 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 7 ወይም 13 ቀን ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ (አስተምህሮ) ይባላል፡፡

👉ከኅዳር 13 እስከ ኅዳር 19 ቅድስት ይባላል

👉ከኅዳር 20 እስከ ኅዳር 26 ምኩራብ ይባላል

👉ከኅዳር 27 እስከ ታኅሣሥ 3 መፃጉዕ ይባላል

👉ከታኅሣሥ 4 እስከ ታኅሣሥ 6 ደብረ ዘይት ይባላል (ለሦስት ቀናት ብቻ ነው)።

👉ከታኅሣሥ 7 እስከ ታኅሣሥ 13 ዘመነ ስብከት ይባላል

👉ከታኅሣሥ 14 እስከ ታኅሣሥ 20 ዘመነ ብርሃን ይባላል

👉ከታኅሣሥ 21 እስከ ታኅሣሥ 27 ዘመነ ኖላዊ ይባላል

👉ታኅሣሥ 28 እና ታኅሣሥ 29ልደት ተብለው ይጠራሉ።

ዘመነ አስተምህ(ሕ)ሮ፦ ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ እርሱ በደላችንን ሁሉ ይቅር እንደሚለን እኛ ምእመናንም እርስ በእርስ ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ ነው፡፡

✍ዘመነ አስተምሕሮ፦

👉ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ይቅርታ የምትጠይቅበት፣

👉ምእመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፣ስለዚህም በስፋት ትምህርት የሚሰጥበት ዘመን ነው፡፡

በዘመነ አስተምሕሮ የሚገኙ ሰንበታት፦ በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እንደተቀመጠው በዘመነ አስተምሕሮ ውስጥ የሚገኙ ሰንበታት (እሑዶች)፦

👉 አስተምሕሮ (ኢተዘኪሮ)፣

👉አስተምሕሮት (ሎቱ ስብሐት)፣

👉ምኵራብ (አምላክ ፍጹም በሕላዌሁ)፣

👉መጻጉዕ (ይቤሉ እስራኤል) እና

👉ደብረ ዘይት (ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ እረፍተ) ተብለው ይጠራሉ፡፡

✍ስለ አስተምሕሮ (አስተምህሮ) ትርጉም የተሰጠ ትምህርት በዚህ ሊንክ ይገኛል👇

https://t.me/yeyohannesneseha/160136

✍ሳምንታቱን በዚህ መልክ የከፋፈለውም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው (ድጓ ዘአስተምህሮ)፡፡ ከመጀመሪያው ሳምንት (ከአስተምሕሮ) በቀር የአራቱ እሑዶቹ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡

👉የሰንበታቱ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ጋር ተመሳሳይ ነውን? 

✍የዘመነ አስተምህሮ ሰንበታት (እሑዶች) ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ስያሜ ጋር ተመሳሳይ ይሁን እንጂ በእነዚህ ሳምንታት ሌሊት፦

👉 የሚዘመሩ መዝሙራት፣

👉በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ምንባባትና

👉የሚቀርቡ ትምህርቶች ግን በይዘትና በምሥጢር ይለያያሉ፡፡

ትምህርቶቹ በምስጢር ይለያያሉ ስንልም በዚህ ወቅት የሚነገረው ምሥጢርና ይዘት በወቅቱ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ በየትኛውም ጊዜ በቤተክርስቲያናችን የሚቀርበው ትምህርት አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።

ይቀጥላል (ክፍል 2)
    👇

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወለዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!

@Sewsinor


ለ 614 ጫኝ እና አውራጆች ፍቃድ ተሰቷል።

በከተማዋ 614 የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ህጋዊ ፍቃድ አግኝተዋል ተባለ።

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የምሬት ምንጭ ሆኖ የቀጠለዉ የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀት ህጋዊ አካሄድ እንዲኖረዉ እየተደረገ ነዉ ተብሏል።

ከአንድ አመት ወዲህ የጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት መመሪያ ህግ እንዲወጣ መደረጉ ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ የከተማዋ መታወቂያ አላቸዉ የተባሉ 7228 ወጣቶችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ሰምተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እየመራዉ ነዉ በተባለዉ መመሪያ በእያንዳንዱ እቃዎች የመጫን እና የማዉረድ ሂደት  ላይ የገበያ ጥናት የተደረገበት የዋጋ ተመን ማዉጣቱን የቢሮዉ ምክትል ሀላፊው አቶ ሚደቅሳ ተናግረዋል።

ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ተነሺዎችን ተከትሎ የሚጠየቁ የጫኝ እና አዉራጅ የዋጋ ተመን ክፍያዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ ተነስቶበታል።

ቢሮዉ በዚህ ዙሪያ ያሉ የቁጥጥር ክፍተቶችን ለማስተካከል ምን እየሰራ ነዉ ብለን ላነሳንላቸዉ ጥያቄ " ህጋዊ ማህበራቱ ለባለንብረቶች ንብረት ሀላፊነት እንዲወስዱ በማስገደድ  እንዲሁም የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ክትትል እያደረኩ ነዉ" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በከተማዋ አራብሳ እና ከከተማዋ መውጫ ላይ የሚገኙ ሰፈሮች ህገወጥ  የጫኝ እና አዉራጅ አደረጃጀቶች በስፋት መታየታቸዉ ሰምተናል።

ይህንን ተከትሎ ማህበረሰብ ለአገልግሎቱ ህጋዊ ደረሰኝ እንዲጠይቅ ያስፈልጋል ተብሏል።

ሆኖም ህብረተሰቡ ንብረቱን ከጫኝ እና አዉራጅ አካላት ዉጪ በራሱ አቅም የማዉረድም ሆነ የመጫኝ ሙሉ ፍቃዱ ተሰቶታል።

ማህበረሰብ ይህን ያልተከተሉ ማህበራት በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮምሽን ነፃ የስልክ መስመሮችን በመጠቀም ጥቆማዎችን መስጠት የሚችሉ መሆኑን ቢሮዉ አሳዉቋል።

(ethio fm)

@Sewsinor
@Sewsinor


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ 🧡
          🧡መጽሐፈ ሲራክ
                🧡ምዕራፍ ፲፭
ጥበብ ከትዕቢተኞች የራቀች ናት፡፡ ሐሰተኞችም ሰዎች አያስቧትም፡፡ የክፉ ሰው የአንደበቱ ነገር የሚወደድ አይደለም፡፡ የሚናገረው ነገር እግዚአብሔርን በመፍራት አይደለምና፡፡ እግዚአብሔር ሰው ኃጥእ ይሆን ዘንድ አይወድም፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ክፉና በጎን በሚያውቅ ግዕዛን ፈጥሮ በወደደው ሊኖር ተወው፡፡ እነሆ እግዚአብሔር የወደድከውን ትሠራ ዘንድ ክፉንና በጎን ለይቶ የሚያውቅ ግእዛን ሰጠህ፡፡ ሕይወትም ሞትም በሰው ፊት ይኖራል፡፡ ከእሊህም የመረጠውን ሥላሴ ይሰጡታል፡፡ ይህም ማለት ጽድቅን ቢሠራ ሕይወትን ይሰጡታል፡፡ ኃጢአትን ቢሠራ ሞትን ያመጡበታል ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጥበቡ ረቂቅ ነው፡፡ ዕውቀቱም ጥልቅ ነውና ሁሉን መርምሮ ያውቃል፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትን ይሠራ ዘንድ ያዘዘው ሰው የለም፡፡ ይበድልም ዘንድ ማንንም አያሰናብትም፡፡
                      🧡ምዕራፍ ፲፮
በክፉ ልጅ ደስ አይበልህ፡፡ ከሺህ ክፉዎች ልጆች አንድ ደግ ልጅ ይሻላል፡፡ ክፉ ልጅን ከመውለድ ልጅ ሳይወልዱ መሞት ይሻላል፡፡ በአንድ ብልህ ልጅ ሀገር ትጸናለች፡፡ በክፉዎች ብዛት ግን ትጠፋለች፡፡ ኃጥእ ሰው ከፍዳ አያመልጥም፡፡ ጻድቅ ሰው ግን የትዕግሥቱን ዋጋ አያጣም፡፡ ምጽዋት ሁሉ ይቅርታን ያመጣል፡፡ ኃጢአትን ሠርተህ ከእግዚአብሔር አመልጣለሁ በሰማይም የሚያገኘኝ የለም አትበል፡፡

© በትረ ማርያም አበባው

ላይክና ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያጋሩ።
🌹@Sewsinor






++ምክር8+++

አባት
ስማኝማ ልጄ..
በዚች ምድር ላይ ደስታን ስትፈልግ ፣
እህ በለኝና እምልህን አድርግ ።
*
ምክር 1
እድሜህ እንዲባረክ
ጉዞህ እንዲሰምር ፣
ታልቅህን አክብር
አባትህን ሰማ ፣
እናትህን ስማ ፣
ለታናሽህ ብስለት ሁንለት ዋዜማ
+
ምክር 2
በንባብ በእውቀት ራስህን ገንባ፣
የሰው ድንበር ዘለህ ባልገባህ አትግባ ።
አምሮ አለህና ጥንትም ስትፈጠር ፣
በጎውን ተመልከት ክፈትን አትቁጠር ።
+
ምክር 3
ለጓደኛህ ታመን እንደራስህ ውደድ ፣
ይጎዳሀልና በሱስ አትጠመድ ፣
ስርቆት ይቅርብህ ውሸትም አትልመድ፣
በአይንህ ያየህው ፤
የሰማሀው ሁሉ ልክ አይሆንም እና ፣
በምልካም ስራ እንጅ በክፋት አትቅና ።
+
ምክር4
መብላትን ከወደደህ መስራትን አትጥላ ፣
ማንንም ለመርዳት አትበል ወደኋላ፣
ፌስቡክ ላይ ተጥደህ
ሀገር አታባላ ፣
ነገር አታብላላ ።
+
ምክር 5
ግልፍተኛ አትሁን ስከን ተረጋጋ ፣
ከውሳኔህ በፊት ማስተዋል አትዘንጋ ፣
ጥርስህን አሳይተህ ልብህን አትዝጋ።
ልክ አይሆንም እና አፍ ከልብ ሲልቅ ፣
ካልሲህን ለመስጠት ጫማህን አታውልቅ ።
+
ምክር 6
ሁሉን ለኔ አትብል ልክህን እወቀው ፣
ያለህን አክብረህ ኑሮህን አድምቀው ።
በራስህ ተማመን በሁሉም አትንፈስ ፣
እንደመስኖ ውሀ በመሩህ አትፍሰስ ።
+
ምክር 7
ሰላም እንዳይርቅህ ክብር አንዳያሳጣህ ፣
በህይወት እስካለህ ክፉ ቃል አይውጣህ ።
ሰማህ ልጄ...

ልጅ
እየስማሁህ ነው ፣
ቀጣዩስ ምንድን ነው ?
+
7ቱን ምክሮቸን አጥብቀህ ያዛቸው ፣
ከማዳመጥ አልፈህ
ሰርተህ ኑርባቸው ።
=
ምክር8
ሰው ሁን !!!

@Sewsinor
@Sewsinor
@CheramlakT


ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡

@Sewsinor


#እውነተኛ__ታሪክ ይነበብ፤ሁሉም ያንብብ አደራ።
➡በአንድ ቀን በአንድ ቤት አንዲት ብቻዋን የምትኖር ሴት ከመኝታዋ ስትነሳ #አንድ_ፖስታ አልጋዋ አጠገብ ካለ ኮመዲኖ ላይ ተቀመጦ ታገኛለች፡፡
➡ወዳው ፖስታውን ስትከፍት በውስጡ አጠረ ያለች #ደብዳቤ አገኘች፡፡
➡ደብዳቤው እንዲህ ይላል፦

➡"ዛሬ በእንግድነት ለእራት አንቺ ቤት ስለምመጣ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ፡፡"
ከታች ላኪ በሚለው ቦታ " #አምላክ" የሚል ተፅፏል።
#ሴቲቱ ደነገጠች፡፡
➡ነገር ግን ከተረጋጋች በኀላ ያላትን ገንዘብ ከዚም ከዛም ለቃቅማ ማታ ለእንግዳ የሚሆን ነገር ለማዘጋጀት የሚረዳትን የሚበላ፣ የሚጠጣ ነገር ለመግዛት ከቤት ወጣች፡፡

➡ገበያ ውላ ለእራት ግብዣው የሚሆናትን ነገር ገዛዝታ ወደ ቤት ስትመለስ እመንገድ ላይ አንድ #ርሀብ_ያጎሳቆለው ህፃን ከያዘችው ዳቦ እንድትሰጠው ለመናት፡፡
➡ዳቦውን የገዛችው ማታ በቤትሽ እንግዳ ነኝ ላላት ፈጣሪ ነው፤እና ለእዚህ ህፃን ከሰጠችው ማታ ለአምላኳ የምታቀርበው ልታጣ ነው ትንሽ ካመነታች በኃላ ለተራበው ልጅ #ሰጠች፡፡

➡አሁንም ትንሽ እንደተራመደች አንድ በእድሜ የገፉ አባት "ልጄ ተጠማው፤ እባክሽ አትለፊኝ" እያሉ ለመኗት፡፡ አሁን ልቧ ትንሽ ካመነታ በኃላ ለአምላኳ የገዛችውን ለስላሳ ለተጠሙት አባት ሰጠቻቸው፡፡
➡አሁን የገዛችውን ምግብና መጠጥ ለተቸገሩ ሰጥታ ስለጨረሰችው በቀራት ገንዘብ ትንሽ ነገር ለመግዛት ወደ ሱቅ ስታመራ ሌላ "የዕለት ጉርሴን እባካችሁ" እያሉ ሲለምኑ ተመለከተች፡፡ አሁንም አላስቻላትም እጇ ላይ የቀረችውን ገንዘብ ሰጠቻቸው።
➡ሲለመኑ ማለፍ የማያስችላቸው አሉ።

በስተመጨረሻ አምላክን ማታ ምን እንደምታበላ፣ እንደምታጠጣ እያሰበች #ባዶ_እጇን ወደ ቤት ስትመለስ "አንድ በእድሜ የገፉ እናት የለበሱት ልብስ ተቀዳዶ አይደለም ሳይለብሱ በጃንጥላ ውስጥ እንኳን አልፎ የሚያቃጥለው ፀሀይ ቀጥታ ቆዳቸውን እያገኛቸው ሲቃጠሉ ተመለከተች፡፡
➡ወዲያው የለበሰችውን ሹራብ አውልቃ አለበሰቻቸው።
በስተመጨረሻ መሸና ፈጣሪ ከቤቷ መጣ፡፡
ምንም ስላላዘጋጀች ደነገጠች፡፡

"#ጌታ_ሆይ_ይቅርታ ምንም #የሚጠጣና_የሚበላ አላዘጋጀሁም አለች፡፡
➡"#ፈጣሪም በመቀጠል "እንዴ #አበላሽኝ፤ #አጠጣሽኝ፤ እኮ" አላት፡፡
➡"እንዴ መች አግኝቼህ ነው ያበላውህ? ያጠጣውህ?" አለች።
#ፈጣሪም "ቀን #ስታጠጪ፣ #ስታበይ፣ እንዲሁም #ስታለብሺ የነበረው #እኔን ነው፡፡" አላት፡፡

➡ብዙዎቻችን ማለትም የየትኛውም #ሀይማኖት ተከታይ እንሁን ሀይማኖታችን ለፈጠረንን አምላክ መልካም እንድንሰራ እንደሚያዝ እናምናለን፤ ለእሱ ሁሉን እናረጋለን እንላለን፡፡
➡ነገር ግን አጠገባችን ያሉትን #ርሀብተኞች አንድ ጉርሻ አናጎርስም፤ አንዲት ጉንጭ አናጠጣም፤ አይደለም አዲስ ጠቦንና አርጅቷል አንለብሰውም ያልነውን ብጫቂ ጨርቅ አንሰጥም፡፡

➡ታዲያ ምኑ ላይ ነው ፈጣሪያችንን መውደዳችን?
➡የቱ ጋር ነው ሀይማኖታችን የሚለውን መፈፀማችን?
➡ቢገባን ፈጣሪ ተጠምቶ ልናጠጣው የሚገባን ወገናችን ነው፤ ቢገባን ተርቦ ልናበላው የሚገባን ጎረቤታችን ነው፡፡
➡ፈጣሪ መልካም ልቦናን ይስጠን፡፡
እኔም ለራሴ የሚበቃኝ የለኝም ትል ይሆናል ያለህን አካፍል ያለሄው ይባርክሃል።
➡ሰላማችሁ ይብዛ።
እሄ መልእክት ከፈጣሪ ወደ አንተና ወደ አንቺ አለመምጣቱን እርግጠኛ ናችሁ ?
እውነተኛ የሆነ የአንዲትን ሴት ታሪክ ነው።


➡ከወደዳችሁ ለጓደኞቻቸሁ አጋሩ።
➡በጎነት ይለምለም።
@Sewsinor
@Sewsinor


"አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም።

ምን ለማለት ነው 👇👇👇👇
የሰውን ድክመት የምትነግረውም ስህተትን እንዲያርም እንጂ ሰውዬው በእራሱ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ አይደለም እንደማለት ነው።"


🤝 SHARE TELEGRAM👉  @Sewsinor
@CheramlakT


አሁን ቲክታክ ስዞር የሰማሁት ቪድዮ
ዲዛይነር ሮድሪጌዝ ትባላለች በካንሰር በሽታ ሂወቷን አታለች ከሞተች አመታት ቢቆጠሩም
ከመሞቷ በፊት ያስተላለፈችው መልክት ግን አስገረመኝ🙂

አንብቡት እስኪ

በአሁን ሰዓት ለእኔ ምንም ማድረግ የማይችል ውጭ የቆመ ቆንጆ አዲስ መኪና አለኝ
ለእኔ ምንም ሊያደርጉልኝ የማይችሉ ሁሉም አይነት ልብሶች፣ ጫማዎች እና ቦርሳዎች ከሁሉም የፋሽን ዲዛይነሮች አሉኝ…

ለእኔ ምንም ማድረግ የማይችል በጣም በጥሩ ሁኔታ የተሸፈነ የሚያምር እና በጥሩ ሁኔታ ያጌጠ ቤት አለኝ

ምንም ማድረግ የማይችል ብዙ ገንዘብ በአካውንቴ ውስጥ አለኝ

አሁን ግን እዩኝ እዚህ 2በ 2 በሆነ ሆስፒታል ድርብ ሆኜ ተኝቻለሁ

ስለዚህ ማናቹም ብትሆኑ የሌላቹን ነገሮች እያሰባቹ እንዲከፋቹ አትፍቀዱ
በተቃራኒው በሚያስደስታቹ ነገሮች ተደሰቱ

እዝች ምድር ላይ ቁሳቁስ አይደለም አስፈላጊው በጣም አስፈላጊው ነገር ሰላም , ፍቅር እና ጤናቹ ብቻ ነው በመጨረሻም, የሚወዷቹን ሰዎች አስደስቱ ..... የሚል ነበር መልዕክቷ

እናንተ ከዚህ ምን ተማራቹ?

እኔ ግን ባለኝ ነገር ደስተኛ እንድሆን እና ሁሉም ነገር ከንቱ እንደሆነ!🖤

Join & Share
@Sewsinor
@SewsinorBot


🧡መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ 🧡
                   🧡መጽሐፈ ሲራክ
                        🧡ምዕራፍ ፲፩

ድኻ በጥበቡ ይከብራል፡፡ በመኳንንትም መካከል ይቀመጣል፡፡ መልኩ አማረ ብለህ ለመልከ መልካም ሰው አታድላለት፡፡ መልከ ክፉውንም ሰው መልኩ ከፋ ብለህ አትንቀፈው፡፡ ንብ ከአዕዋፍ ሁሉ ተለይታ በመልክ ስትከፋ ማሯ ከሁሉ ይልቅ ይጣፍጣል፡፡ በልብስህ ጌጥ አትኩራ፡፡ በተሾምክበትም ወራት ራስህን አታስታብይ፡፡ ሳትመረምር አትንቀፍ፡፡ አስቀድመህ ነገሩን ጠይቀህ ተረዳ እንጂ፡፡ በሰው ነገር ጥልቅ ብለህ አትግባ፡፡ የእግዚአብሔር ረድኤቱ ጻድቃንን ትጠብቃቸዋለች፡፡ በገንዘብህ ዕወቅበት ከእግዚአብሔርም ታረቅበት፡፡ በሥራህም ጸንተህ ኑር፡፡ እግዚአብሔር ለጻድቃን ዋጋቸውን አብዝቶ ይሰጣቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለሰው እንደሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል፡፡ በጎ ቢሠራ ዋጋውን ይሰጠዋል፡፡ ክፉ ቢሠራ ፍዳውን ያመጣበታል፡፡ ፍጻሜውን ሳታይ ሰውን ዕፁብ ዕፁብ አትበለው፡፡ ያገኘኸውን ሰው ሁሉ ሳትመረምር አትሹም፡፡ ተንኮለኛ ሰው በጎ ያደረግህለትን ያህል ክፉ ነገር ይመልስልኻል፡፡ ነውርም ሳይኖርብህ ነውረኛ ያደርግኻል፡፡
                    🧡ምዕራፍ ፲፪
እሾማለሁ ባልክ ጊዜ የምትሾመውን ሰው መርምረህ ዕወቅ፡፡ ለድኻ በጎ አድርግለት፡፡ ጠላትህን አንድ ጊዜ ብታምነው ሁልጊዜ አትመነው፡፡ ከብረት ዝገት እንደማይጠፋ ከልቡ ክፋት አይጠፋምና፡፡

© በትረ ማርያም አበባው


🌹@Sewsinor
@CheramlakT


GUYS እባካችሁ ሊንክ ሲላክላችሁ እንዳትነኩ ምክንያቱም ብዙ ሰው HACK እየተደረገ ነው ፤ ከምታውቁት ሰው ቢሆንም እንኳን ምታውቁት ሰው በ አጋጣሚ hack ከተደረገ እናንተንም ይዟችሁ ገደል ነው ሚገባው

@Sewsinor @Sewsinor


የሸማ ተራው እሳት 🔥 አደጋ 🧑‍🚒 ምን ታስባላችሁ?


አዲስአበባ ዉስጥ መጠነኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ተከስቶ ነበር የመሬት መንቀጥቀጡ የት ሠፈር ተሠማችሁ?


ሰላም ለሁላችሁ፡- ጌታ ወንድምሽ ይነሳል ባላት ጊዜ ማርታ አዎ በትንሳኤ ሙታን እንደሚነሳ አምናለሁ አለችው፡፡ዮሃ 11፤24 አሁን እንደሚነሳ ግን ለማመን ተቸገረች፡፡አምላካችን እንዳለ እና እንደሚችል ማመን አንድ ነገር ነው፡፡ አሁን እንደሚያድን ለማመን ግን የሚቸግራቸው ብዙ የብርሃን ልጆች/ክርስቲያኖች/ ይኖራሉ፡፡ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ/ወደፊት/ አስበኝ ሉቃ 23፤42 እንዳለው ወንበዴ ተስፋቸውን አርቀው የሚጠብቁ፣ ለችግራቸው መፍትሄ ብዙ ዘመን እንደሚያስፈልጋቸው የሚያስቡ፣ ብዙ ከጸለዩ በኃላ፣ጥሩ ሆኛለሁ ካሉ በኋላ እንዲረዳቸው ይጠብቃሉ፡፡ ጥሩ ሆኛለሁ ላለ ሰው የሚሰጥ ደሞዝ እንጂ ቸርነት አይደለም፡፡ደጅ ጥናት በሞላበት ምድራዊ አሰራር የእግዚአብሄርን ቸርነት ለክተው የሚጠብቁት ብዙ ናቸው፡፡ እርሱ ግን ለመርዳት የቸኮለ አሁን የሚያድን ነው፡፡ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ የሚል ነው፡፡ሉቃ 23፤43 ብታምኚስ ወንድምሽ አሁን ይነሳል የሚል ነው፡፡ዮሃ 11፤40 ሲሰማም ሲረዳም ሲያዝንም ሲደግፍም አምኖ ለጠበቀው አሁን! አሁን! አሁን! መልስ አለው፡፡እባካችሁ ለሌሎች ሼር አድርጉት

@Sewsinor



Показано 20 последних публикаций.