‹‹ኤርትራ በግዳጅ ዜጎቿን ለውትድርና መመልመሏን ቀጥላበታለች›› ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ረዳት ዋና ፀሀፊ ኢልዚ ብራንድስ ተናገሩ፡፡
በተመድ የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ዛሬ የኤርትራ ሁኔታ ለግምገማ በቀረበበት ወቅት ዋና ፀሀፊዋ ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንደሚጣረስ አስረድተዋል፡፡ ከግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በተጨማሪ ግለሰቦችን በማሰቃየት፣ ፆታዊ ጥቃት በመፈፀምና የጉልበት ብዝበዛ በማድረግ የኤርትራ መንግስት የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እየጣሰ መሆኑን የገለፁት ረዳት ፀሀፊዋ በርካታ ኤርትራዊያን ወጣቶች ይህንን በመሸሽ ከአገራቸው እየተሰደዱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
‹‹ከዚህ ቀደም በዚህ ምክር ቤት ኤርትራ ከዚህ ከድርጊቷ እንድትታቀብ ማሰሰቢያ ተሰጥቷት ነበር›› ያሉት ረዳት ፀሀፊዋ ይሁንና ማሳሰቢያውን ሰምታ ከማስተካከል ይልቅ ብሶባት የመብት ጥሰቱን መቀጠሏን አስረድተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በምክር ቤቱ የኤርትራ የሰብአዊ መብት ራፖርተር የሆኑት መሀመድ አብዲሰላም ባቢከር አመታዊ የኤርትራን የሰብአዊ መብት አያያዝ በተመለከተ ይህ ዘገባ በተጠናከረበት ወቅት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
የኤርትራ መንግስት እኚህ ራፖርተር ማብራሪያ በሰጡ ቁጥር የተቃውሞ መግለጫ የሚያወጣ ሲሆን ከዚህ ሪፖርት በኋላም ተመሳሳይ መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል፡፡