Репост из: ሳዳት ከማል ማነው?(Sadat kemal)
ዘካተል ፊጥርን ወደ ሃገር ውስጥ መላክ
~
ውጭ ሃገር ያላችሁ ወገኖች ዘካተል ፊጥርን ወደ አገር ቤት ብትልኩ ነው የሚሻለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሃገራችን ህዝብ በጣም ችግር ላይ ነው ያለው። የዋጋ ንረቱ እሳት ሆኗል። የሰላሙ መጥፋት ችግሩን ይበልጥ አባብሶታል። አእላፍ ወገን ተፈናቅሎ አውላላ ሜዳ ላይ ፈስሷል። ስለዚህ ውጭ ያላችሁ ወገኖች በተቻለ መጠን ዘካችሁን ወደ አገር ቤት ብትልኩ ትንሽም ቢሆን ትደጉማለች። እንዲያውም የ 2 እና 3 ኪሎ ዱቄት ዋጋ ከምትገደቡ በራሳችሁ ፈቃድ ጨመርመር ብታደርጉት ከአላህ ዘንድ የበለጠ ታተርፉበታላችሁ።
እንደሚታወቀው ዘካተል ፊጥርን በተመለከተ በላጩ አንድ ሙስሊም በፆመበት ሃገር መስጠቱ ነው። በሰዎች ወይም በድርጅቶች አማካኝነት ከመስጠትም በራስ መፈፀሙ የተሻለ ነው። ምክንያቱም ወኪሎች ምናልባት ጊዜውን ጠብቀው ለመስጠት የማይጠነቀቁበት፣ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ በሌለበት በገንዘብ የሚሰጡበት፣ ወይም ደግሞ በማይገባ ቦታ ላይ የሚያውሉበት ሁኔታ ሊገጥም ይችላልና።
ነገር ግን አንድ ሙስሊም በሆነ ምክንያት በራሱ መፈፀም ከቸገረውና እምነት የሚጥልበት ሰው ካለው በውክልና እንዳይፈፅም የሚከለክል ምንም ማስረጃ የለም፣ ምንም! እንዲያውም አስገዳጅ ሁኔታ ባይኖር እንኳ ፍላጎቱ ከሆነ በታማኝ ወኪል ቢያስፈፅመው ምንም የሚከለክለው ማስረጃ የለም። ይህንን የማነሳው አንዳንዶች ክልክል የሆነ አስመስለው ስለሚያቀርቡት ነው። ልብ በሉ! በዚህ ላይ የሚጠቀሱ የዑለማዎች ንግግሮች ከጥንቃቄ አንፃር የተሰነዘሩ ምክረ ሃሳቦች እንጂ ከልካይ መረጃ ሆነው የመቅረብ አቅም የላቸውም። ሐራም ማለት ሸሪዐ ሐራም ያለው ብቻ ነው። እንዲያውም ዛሬ ዛሬ በውክልና ለማስፈፀም አስገዳጅ ሁኔታዎች የሚገጥሙበት ጊዜዎች አሉ።
ስለዚህ በዚህ ጉዳይ በራሳችሁ ለመፈፀም የተቸገራችሁ ሙስሊሞች በምታምኗቸው ወኪሎች አማካኝነት ለማስፈፀም ተንቀሳቀሱ። "ዘካተል ፊጥርን አንድ ሰው ተሰዶ በሚኖርበት ሃገር ነው የሚያወጣው ወይስ በነባር ሃገሩ ነው? " ተብለው የተጠየቁት ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
إذا كان لديه فقراء فيجوز ، كما أنه يجوز أن يوكل غيره بأن يخرج الزكاة في بلده الأصيل
"እሱ ዘንድ ድሃዎች ካሉ (ተሰዶ በሚኖርበት ማውጣት) ይፈቀድለታል። ልክ እንዲሁ ሌላን ወክሎ ዘካውን በነባር ሃገሩ እንዲያወጣለት ማድረግም ይፈቀዳል።" [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር: 694]
ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት ዘካችሁን ወደ ሃገር ቤት ብትልኩ የተሻለ ይሆናል። ወላሁ አዕለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor