Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


كناشة ابن منور

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!
ክፍል - 9
~
"የለተሞን ጀርሕ እና ተዕዲል ለምን አልተቀበላችሁም" እያለ የሚጮኸው መንጋ ለተሞን ተከትሎ እነ ሸይኽ ሱለይማን አሩሐይሊን እና እነ ሸይኽ ረዪስን ተብዲዕ አድርጎ ይሆን?
ካላደረጋችሁ የሰውየውን ጀርሕ መቀበል ግዴታ ነው ያላችሁትን ጥላችሁታል ማለት ነው። ይሄ ደግሞ መንሀጃችሁ ላይ ጥቁር ነጥብ ይጥላል። ሚናችሁን ልዩ። ወይ ለተሞን ወይ እነዚህን መሻይኾች አንዱን መጣል ነው።
"ለተሞ ተሳስቷል" ካላችሁ ሰውየው የሱና ዑለማኦችን እያብጠለጠለ ነው ማለት ነው። የሱና ዑለማኦችን "ከመንሀጅ ውጭ ናቸው" እያለ የሚዘባነን ወፈፌ ሑክሙ ምን ነበር? ህጉ ለተሞ ጋ ሲደርስ ይቀየር ይሆን?
ለተሞ ተነካ ብላችሁ ያለ ቦታው ስትጠቅሱት የነበረውን የሰለፎች ንግግር አስታውሱ። ከሙብተዲዕ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የሱና ሰዎችን መንካት ነው። ስለዚህ እነ ሱለይማን አሩሐይሊን ከሱና እያስወጣ ያለው ለተሞ ምንድነው?

የሰውየውን ደፋርና አስቀያሚ ድምፅ ሰሙት።
=
https://t.me/IbnuMunewor


ihsan jobs 
     ኢህሳን
ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ
ይጠቅም ዘንድ ታስቦ የተከፈተ የስራ ማስታወቂያ
የምንለቅበት አዲስ ቻናል ነው

በቻናሉ ነፃ ማስታወቂያ እንለቃለን
  ከናንተ የሚጠበቀው  የትኛውም
     ማስታወቂያ በውስጥ መሥመር
ለኛ ማሳወቅ ብቻ ነው

እኛም በነፃ ከሸሪዓ የማይጋጩ ስራዎች
አጣርተን በቻናሉ እንለቃለን
@twhidfirst1
@Tolehaaaaaa
@AbuNuhibnufedlu

https://t.me/ihsan_jobs
https://t.me/ihsan_jobs


ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:- 4️⃣1️⃣
* የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ
* የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ጀምዕ የሚደረጉ ሶላቶች
~
1- ጀምዕ ማለት ሁለት ተከታታይ ሶላቶችን በአንደኛው ወቅት መስገድ ነው። ጀምዕ የሚደረጉት ሶላቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ዙህር እና ዐስርን በአንደኛው ወቅት
- መግሪብ እና ዒሻእን እንዲሁ በአንደኛው ወቅት መስገድ ይቻላል።
ከዚህ ውጭ ጀምዕ የለም። የሱብሕ ሶላት ከየትኛውም ሶላት ጋር ጀምዕ አትደረግም። እሷም ወደ ሌላ ወቅት አትውወሰድም። ሌሎችም ሶላቶች ወደሷ አይውወሰዱም። 0ስርን ከመግሪብ ጋር ጀምዕ ማድረግም አይቻልም።

2- ጀምዕ በሁለት መልኩ ሊፈፀም ይችላል።
1ኛው፦ የኋለኛውን ሶላት ወደ መጀመሪያው በማምጣት። ይሄ ጀምዑ ተቅዲም ይባላል። ዐስርን ከዙህር ጋር በዙህር ወቅት ፤ ወይም ዒሻእን ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት መስገድ ነው።
2ኛው ጀምዑ ተእኺር ይባላል። የመጀመሪያውን ሶላት ወደ ኋለኛው ወስዶ መስገድ ነው። ይህም ዙህር እና ዐስርን በዐስር ወቅት ፤ መግሪብንና ዒሻእን በዒሻእ ወቅት መስገድ ነው።

3- ጀምዕ ከሐጃ ጋር የተያያዘ ነው። መንገደኛም ይሁን በሃገሩ ኗሪ ሶላትን በወቅቱ መስገዱ የሚከብደው ከሆነ ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ሶላት ወቅት ጀምዕ ማድረግ ይችላል። ህመምተኛ፣ ነፍሰ ጡር፣ አጥቢ፣ ሌሎችም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ መስገዳቸው የሚከብዳቸው አካላት በዚህ መልኩ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ልብ በሉ! ያለ ተጨባጭ ምክንያት ልማድ እንዲያደርጉ አይደለም።

4ኛ፦ በጀምዕ ጊዜ የሶላቶቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ይገባል። ዙህር እና ዐስርን ጀምዕ የሚያደርግ ሰው ጀምዑ ተቅዲምም ይሁን ጀምዑ ተእኺር መጀመሪያ ዙህርን ያስቀድማል። ካሰላመተ በኋላ 0ስርን ይሰግዳል። መግሪብ እና ዒሻእን ጀምዕ የሚያደርግም ሰው እንዲሁ መጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ ዒሻእን ያስከትላል።

5ኛ፦ ጀምዕ እና ቀስር ተያያዥ አይደሉም። ቀስር ማለት ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ አሳጥሮ መስገድ ነው። ይሄ ጉዞ ላይ ላለ ሰው ብቻ የሚፈቀድ ነው። በሃገሩ ኗሪ የሆነ ሰው አራቱን ረከዐ ሁለት አድርጎ ማሳጠር አይፈቀድለትም። እንዲሁም ማሳጠር ሱብሕ እና መግሪብን አይመለከትም። በየትኛውም ሁኔታ የረከዐቸው ቁጥር አይቀየርም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


ትራንስፖርት ላይ ሆኖ የሶላት ወቅት እንዳያልፈው የሰጋ ሰው ምን ያድርግ?
~
1- በመጀመሪያ በወቅቱ ለመስገድ መጣር አለበት። ለምሳሌ ከመሳፈሩ በፊት መስገድ ከቻለ ይሰግዳል። ወይም ጉዞውን ቀደም ብሎ በመፈፀም ከዚያ ሶላቱን በወቅቱ ይሰግዳል። ባጭሩ እስከቻለ ድረስ ጉዞውን ከሶላቱ ወቅት ጋር በማይጋጭ መልኩ ያመቻች። ሾፌሩን አናግሮ ወርዶ የሚሰግድበት እድል ካለ የአፈፃፀም ስርአቶቹ ያልተጠበቀ ሶላት መኪና ውስጥ ሊሰግድ አይገባም። ስለዚህ ለሶላቱ ትኩረት ይስጥ።

2- በወቅቱ ለመስገድ ካልቻለስ? ጀምዕ ማድረግ የሚቻል ሶላት ከሆነ ለምሳሌ ዙህር እና ዐስር ወይም መግሪብ እና ዒሻእ ከሆኑ በማስቀደም ወይም በማዘግየት ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ወቅት በስርአት መስገድ ይችላል። ሙሳፊር ቢሆንም ባይሆንም። ወይ ወደ መጓጓዣው ከመግባቱ በፊት አስቀድሞ ወይ ደግሞ ከመጓጓዣው ሲወርድ አዘግይቶ በስርአቱ ይሰግዳል። በስርአቱ ስል በወቅቱ ለመስገድ ብሎ መኪና ውስጥ አርካኖችን ሳያሟላ እንዳይሰግድ ነው።

3- ሶላቱ ጀምዕ ለማድረግ የማይመች ከሆነስ? ለምሳሌ የሱብሕ ሶላት ወቅት ሳይገባ ተሳፈረ። ወይም ከዙህር በኋላ ቀድሞ ያልታሰበ ጉዞ ጀምሮ ትራንስፖርት ላይ እያለ የዐስር ወቅት ሊወጣበት ሆነ። መኪናው ወቅት ሳይወጣ የማይቆም ከሆነበት ምን ያድርግ? ወቅቱ ሳይወጣ መኪናው ላይ ይሰግዳል። መኪናው ላይ መቆም ከቻለ ይቆማል። ካልቻለ በተቀመጠበት ሆኖ ይሰግዳል። ሩኩዕ እና ሱጁድ ለማድረግ ካልተመቸ ጎንበስ እያለ ይፈፅማል። ለሱጁዱ ከሩኩዑ ይበልጥ ዝቅ ይላል። ውዱእ ከሌለው ተየሙም ያደርጋል።

4- ቂብላን በተመለከተ በሙሉ ሶላቱ ወደ ቂብላ መዞር ከቻለ ለግዴታ ሶላት ቂብላን መቅጣጨት ግዴታ ነው። ካልቻለ ሶላቱ ሲጀምር ወደ ቂብላ ዙሮ ይጀምራል። ከዚያ በኋላ መኪናው ቂብላውን ቢለቅም ባለበት ይሰግዳል።

(ሼር ብታደርጉት ባረከላሁ ፊኩም።)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


📌محاضرة بعنوان①:

مواعظ وعبر من حديث: "يامحمد عش ماشئت فإنك ميت "

🎙አቡ ዐኢሻ ሙሐመድ ሰዒድ

https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba


ዛሬ ጀርመን ውስጥ አንድ የሳዑዲ ዜጋ የነበረ ሰው ለገና ገበያ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ሆነ ብሎ መኪና ነድቶባቸው ብዙዎችን ጎድቷል። ታዲያ የተለያዩ የዜና አውታሮች ሰውየው ሳዑዲያዊ መሆኑን ደመቅ አድርገው እየዘገቡ ነው። አላማቸው ቀድሞም በምእራቡ ሸው.ራራ ፕሮፖጋንዳ brainwashed የሆነው ህዝባቸው በቀላሉ ከኢስላም ጋር እንዲያገናኝ አመቻችተው ማጉረሳቸው ነው። ብዙ ሞ.ኞችም በቀደዱላቸው ተከትለው ፈሰዋል።

* በመጀመሪያ የድርጊቱ ፈፃሚ ሙስሊም አይደለም። ከኢስላም ከወጣ ዘመናት ተቆጥረዋል። እምነት የለሽ ነው። እንዲያውም ለኢስላም ጫፍ የደረሰ ጥላቻ ያረገዘ፣ ይህንንም ባደባባይ የሚተፋ ነው።
* ሰውየው ፅንፈኛ የኢስ -ራኤል ደጋፊ ነው። እስራ - ኤል ከናይል እስከ ኤፍራጠስ ወንዝ ያለውን በሃይል እንድትጠቀልል የሚቀሰቅስ ነው።
* ሰውየው ከሳዑዲ እና ከባህረ ሰላጤው ሃገራት ሴቶችን በማስኮብለል ላይ የተሰማራ ወን.በዴ ነው።

በዚህ እና ሌሎችም ወንጀሎች የሚፈለግ ቢሆንም የጀርመን መንግስት ለሳዑዲ አልሰጥም ብሎ ጥገኝነት ሰጥቶ ሲንከባከበው ከቆየ በኋላ አሁን አደጋ ሲያደርስ ጊዜ ሳዑዲያዊ ነው እያሉ ይዘግባሉ። የሚገርመው ደግሞ ከባለፈው አመት ጀምሮ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል በተደጋጋሚ ለጀርመን ፖሊስ መረጃ ደርሶት ችላ ብሎ ማሳለፉ ነው። ኢስላምን ሲሳደብ ዜግነት ሰጥተው ተንከባከቡት። ደፍጥጦ ሲፈጃቸው ጊዜ ሳዑዲያዊነቱን መዘገብ ላይ ተሰማሩ። ንፍ ق ናችሁ ያመጣባችሁ ጣጣ ነው። ዋጡት!
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


የ3 አመቷ ታዳጊ ልጄን አሳክሙልኝ ይላል አባት ሙነወር አህመዲን ‼
=================================

✍ ህፃን ኢነብ ሙነወር አህመዲን ባጋጠማት የመቅኔ ችግር መቅኔዋ ደም አያመርትም እና በሰዉ ደም ነዉ ምትኖረው በየሳምንቱ ደም ይቀየርላታል አይመቻትም በአፋ እና ከተለያየ ቦታዋ ይወጣል በዛን ስዓት ለረጅም ስዓት እራሳን አታውቅም ህይወቷ እጅግ አስጊ በሆነ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን እና በመላው አለም ያላቹ ወገኖቼ የልጄን ህይወት በናንተ ተሣትፎ አድኑልኝ ይህ ጥያቄ ስጠይቅ ግን አንደበቴ ተሳስሮ ነው በርግጥ የሠው ፊት እንደማየት አስፈሪ ነገር የለም 15 ወራት ያለኝን አሟጥቼ ሥታገል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ያለችበት ሁኔታ በሽታው እየጨመረ ስለሆነ የተሻለ ሕክምና ማድረግ እንዳለባት ሐኪሞች አረዱኝ:: የተጠየኩት የህክምኛዋ ወጪ ከአቅሜ በላይ ነው ህክምናውም በፍጥነት ህንድ ሀገር ሄዳ ካልታከመች ወደ ካንሠር ይቀየራል ተባልኩ
በጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎች እንደ መጨረሻ መፍትሄ የተደረሱበት ውሳኔ፤ በሽታው ከዚህ በላይ ሳይደርስ ወደ ካንሰር ሳይለውጥ በፊት ወደ ህንድ ሀገር ሄዳ እንድትታከም የሀኪሞች ቦርድ ወስኗል።

የታዳጊዋ ህይወት እጅግ አስጊ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሀገር ሄዳ ሕክምናዋን እንድታገኝ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። ለህክምናው በአጠቃላይ ከ50,000 ዶላር (5 ሚሊዮን ብር) እንደሚያስፈልጋት ታውቋል። ይህን ለመሸፈን ደግሞ እጅግ በጣም ከአቅሜ በላይ ስለሆነብኝ ለአላህ ብላችሁ የልጄን ህይወት ታደጉልኝ ሰበብ እንድትሆኑና ወገናዊ ድጋፋችሁን እንድታደርጉልኝ ከልብ በሆነ ትህትና ጠይቀዋችኋል።
ሰዉ ለመርዳት ሰዉ መሆን ብቻ በቂ ነዉ
√ የአካውንት ቁጥሮች፦
1000665961242 ንግድ ባንክ
213116134 አቢሲኒያ ባንክ
0052261820101 ዘምዘም ባንክ

ተማም ሙዘሚል, ሳዲቅ አህመዲን እና ሙነወር አህመዲን

ስልክ፦0921339398 ሙነወር አህመዲን (አባት)

ስልክ :-0993468988 ተማም ሙዘሚል

https://t.me/+GVDu1cklUTkxYzc0




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ሌሎችም ባጠቃላይ እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ ለመስገድ የሚቸገሩበት ሁኔታ ከገጠማቸው ዙህርን እና ዐስርን በአንዱ ወቅት፤ መግሪብን እና ዒሻእንም እንዲሁ በአንደኛው በሚመቻቸው ወቅት መስገድ ይችላሉ። መንገደኞች ባይሆኑ እንኳ ማለቴ ነው። ስለዚህ ለምሳሌ አንድ ተማሪ ከመግሪብ ሶላት ቀደም ብሎ 12:00 ላይ ለፈተና እንዲቀመጥ ቢገደድና የፈተናው ጊዜ እስከ ዒሻእ ወቅት የሚረዝም ከሆነ ፈተናውን ካጠናቀቀ በኋላ በመጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ እንደገና ዒሻእን ይሰግዳል። ይሄ ሶሒሕ ሐዲሥ የመጣበት ነው። ለተጨማሪ የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን ድምፅ አያይዣለሁ።

ተጨባጭ ምክንያት ካልገጠመው ግን ሁሉንም ሶላት በወቅቱ ነው መስገድ ያለበት። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتۡ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِینَ كِتَـٰبࣰا مَّوۡقُوتࣰا }
''ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።" [አኒሳእ፡ 103]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Yusuf App
•የአፑ ይዘት በከፊል


Репост из: Yusuf App
ሪያዱ ሷሊሒን ቁጥር 3_1.0.apk
399.2Мб
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
  
    ╭──────╮
╭📲 ቁጥር ➌
│ ╰──────╯
│❏ ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

ከክፍል 129-መጨረሻው
╰────────────────╯   
╭🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
│🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

├🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼───────────────╯


Репост из: Yusuf App
ሪያዱ ሷሊሒን ቁጥር 2_1.0.apk
401.0Мб
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

    ╭──────╮
╭📲 ቁጥር ➋
│ ╰──────╯
│❏ ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

│ ከክፍል 65-128
╰────────────────╯   
╭🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
│🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

├🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼───────────────╯


Репост из: Yusuf App
ሪያዱ ሷሊሒን ቁጥር 1_1.0.apk
370.3Мб
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
  
    ╭──────╮
╭📲 ቁጥር ➊
│ ╰──────╯
│❏ ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

ከክፍል 01-64
╰────────────────  
╭🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├────⟢
│🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰──────────────
╭⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

├🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼───────────────╯


Репост из: Yusuf App
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

╭┄┈┈
ሪያዱ ሷሊሒን رياض الصالحين

│🎙የደርሱ አቅራቢ »
│⚊⚊
│» ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
╰─────────────────╯
🏷በ3 አፕሊኬሽን ተዘጋጅቶ የቀረበ
╭𑁍──────────────
│➺ቁጥር 1 ከክፍል 01-64
│🖇 https://t.me/Yusuf_App1/550
├𑁍──────────────

│➺ቁጥር 2 ከክፍል 65-128
│🖇 https://t.me/Yusuf_App1/551
├𑁍──────────────

│➺ቁጥር 3 ከክፍል 129-መጨረሻው
│🖇 https://t.me/Yusuf_App1/552
╰𑁍──────────────

  ⎙   አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!
  ↻ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
   ⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀሉን
𑁍
   http://t.me/Yusuf_App1


🔖 ዑዝር ቢል'ጀህል (ክፍል 07)

📌 ካለማወቅ ሽርክ የሰራ አካል እውን ሙስሊም ተብሎ አይጠራምን⁉️

📌 ዑዝር የሚሰጡ አኢማዎችስ ዑዝር ቢል'ጀህል ሲሰጡ የአኺራውን ቅጣት እንጅ የዱኒያዊ ፍርድና ስያሜን እውን አያስቡበትምን⁉️

እና ሌሎችም ነጥቦች የተዳሰሱበት ሙሐደራ

🎙 አቡ ዒምራን 📎 ታህሳስ 11/2017
የቴሌግራም ቻናል ⤵️
https://t.me/Abu_lmran_Alaseriy


ነጋዴው ወገኔ ሆይ!
~
የፈለገ በስራህ ላይ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩ "አልሐምዱ ሊላህ" ከአንደበትህ አይራቅ። ስታመሰግን ይጨመርልሃል። "ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ" ይላል አላህ። [አብራሂም፡ 7] የተሰጠንን እናመስግን። "አልሐምዱ ሊላህ የባሰውን ይያዝልን" እንበል። ማማረር ያጡትን አያስገኝም።
ደግሞም ከናንተ በታች ያሉትን ተመልከቱ ተብለናል። ማየት ለሚችል ከታች ብዙ ኸልቅ አለ። የባሰ ሁኔታ ላይ ያሉትን ስታስብ በተሰጠህ ላይ ጌታህን ታመሰግናለህ። ትኩረትህ ካንተ በላይ መመልከት ከሆነ ወደ ማማረር ይመራሃል። ይሄ ደግሞ የልቦና ሰላም፣ የህሊና ረፍት ያሳጣሀል። ሰላም ያለው በአልሐምዱ ሊላህ ውስጥ ነው። ተግተህ ሰበብህን አድርስ። ስለሰጠህ ኒዕማ ሁሉ ጌታህን አመስግን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


ደርስ
~
• አልዐቂደቱል ዋሲጢያህ
• ክፍል:- 0️⃣7️⃣
• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት፣ መስጂደል ዋሊደይን
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ
• የኪታቡ ሶፍት ኮፒ በpdf:-
https://t.me/IbnuMunewor/6679
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


እንደ ብሄር ተበደልን ብለው ሲያስቡ ያለ ሃይማኖት ልዩነት ሙስሊሙንም ይቀስቅሱታል። ሰላም ያገኙ ሲመስላቸው ግን ሙስሊሙን ነጥለው ሲበድሉት አብሮን ደሙን አፍስሷል፣ አጥንቱን ከስክሷል ብለው እንኳን አያፍሩትም። የኢትዮጵያ ፖለቲካና ፖለቲከኛ ሙስሊሙን መበደሉን የሚያቆመው ወይም የሚያቀዘቅዘው ሌላ ቢዚ የሚያደርገው ነገር ሲገጥመው ነው። ሰላም ሲያገኝ፣ ጉልበት ሲያወጣ የተለመደና የተደበቀ አመሉን ያመጣል። "ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ!" ከዘመን ጋር የማይለወጡ ቆሞ ቀሮች!
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

Показано 20 последних публикаций.