በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
በ2016 በጀት ዓመት ከማኅበረሰቡ በተገኘ ድጋፍ በ"ትምህርት ለትውልድ" መርሐግብር 22 ሺህ የሚደርሱ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ጥገና መከናወኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
በክረምት ወራት 62 ሺህ መምህራንን በሚያስተምሩት ትምህርትና የማስተማር ሥነ-ዘዴ ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁንም ሚኒስቱሩ ገልፀዋል። ከስልጠናው ማጠቃለያ በኋላ ምዘናውን በብቃት ላለፉ መምህራን የማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት ከያዛቸው ሥራዎች መካከል የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሳት ሥራ አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመጪው ዓመት ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ #ኢዜአ
@tikvahuniversity