"ሂጃብ በዲላ ዩኒቨርሲቲ አልተከለከለም።" - ዩኒቨርሲቲው
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች "ኢስላማዊ አለባበስ ስለለበሱ ብቻ ከጥር 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዳይማሩ እንደተከለከሉ" የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ትናንት ጥር 15/2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወቃል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥር 16/2017 ዓ.ም ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ዩኒቨርሲቲው 'ሴኩላሪዝምና ብዝሀ ኃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሠራ ተቋም' መሆኑን ገልጿል።
"አንዳንድ ሚዲያዎች ዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ከለከለ" በሚል ያወጡት መረጃ ሐሰተኛ እና ተቋሙን የማይገልጽ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
"ሂጃብ መልበስ በዩኒቨርሲቲያችን ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን እንዳልተከለከለ ለመግለጽ እንወዳለን" ብሏል ዩኒቨርሲቲው።
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስላወጣው መግለጫ ዩኒቨርሲቲው ያለው ነገር የለም።
@tikvahuniversity