ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም ክረምት 84 ሺህ ለሚሆኑ የ2ኛ ደረጃ መምህራን የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ለመስጠት ዕቅድ ይዟል፡፡
ሚኒስቴሩ የመምህራንን የማስተማር አቅም ለማሻሻል በ2016 ዓ.ም ክረምት ስልጠና መስጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በመጀመሪያ ዙር 52 ሺህ የእንግሊዝኛ፣ ሒሳብ እና ሳይንስ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠናውን ተከታትለዋል፡፡
በዚህም ስልጠናውን ከወሰዱት ውስጥ፥ 63 በመቶ የሚሆኑ ሠልጣኝ መምህራን 70 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡
በዘንድሮው ክረምት ለሁሉም የ2ኛ ደረጃ መምህራን ስልጠናውን ለመስጠት ዕቅድ መያዙን በሚኒስቴሩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልማት ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡
በለፈው ክረምት ስልጠናውን ተከታትለው ምዘናውን ማለፍ ያልቻሉ መምህራን ያለባቸውን ክፍተት በመለየት በድጋሜ ምዘና የሚወስዱበት ሁኔታ እየተመቻቸ እንደሚገኝ ሥራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡
@tikvahuniversity