“የእግዚአብሔር እጅ አጭር ሆነ?”
📖“…በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አጭር ሆነ?”
— ዘኍልቁ 11፥23
እግዚአብሔር አምላክ እንደ ተናገረው እስራኤላዊያንን ከባርነት ቀንበር አወጣቸው። ተአምራዊ በሆነ ሁኔታም መራቸው። ወደ ተስፋይቱም ምድር በሚያደርጉት ጉዞ ላይም አብሮነቱን አልነፈጋቸው። "የሚላስ የሚቀመስ" በሌለበት በደረቅ ምድረ በዳ ከሰማይ መናን መገባቸው። ከረሀብም ታደጋቸው። ነገር ግን “አሁን ግን ሰውነታችን ደረቀች፤ ዓይናችንም ከዚህ መና በቀር ምንም አታይም” የሚል ሆነ መልሳቸው። (ዘኍ 11፥6) ሙሴንም የመብል ጥያቄ ያለ መታከት በማቅረባቸው ምክንያት እረፍት ነሱት።
ሙሴም የሕዝቡን ሁኔታ ለእግዚአብሔር አቀረበ። “በፊቴ ያለቅሳሉና፦ የምንበላውን ሥጋ ስጠን ይላሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የምሰጠው ሥጋ ከወዴት እወስዳለሁ?” (ዘኍ 11፥13) የሕዝቡን የመብል ጥያቄ መመለስ የሚችል አልመሰለውም። መቼም፣ እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው። በረከቱ የማያልቅበት ሙሉ ነው። በእስራኤላዊያን ዘንድ ለተነሳው ጥያቄ እና ሙሴን እረፍት ለነሳው ጉዳይ መልስ ሰጣቸው። እንዲህም አላቸው፦ “፥ ሥጋንም ትበላላችሁ እግዚአብሔርም ሥጋን ይሰጣችኋል፥ ትበሉማላችሁ።” (ዘኍ 11፥18)
እዚጋ ነበር የሙሴ እምነት የተፈተነው። ቀይ ባህርን በድንቅ ሁኔታ ከፍሎ ያሻገራቸውን አምላክ በሙላት መታመን አቃተው። “እነርሱን የሚያጠግብ የበሬና የበግ መንጋ ይታረድን? ወይስ የባሕርን ዓሣ ሁሉ ያጠግባቸው ዘንድ ይሰበሰብላቸዋልን? ” (ዘኍ 11፥22) በማለት አለማመኑን ገለፀ። “እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አጭር ሆነ? አሁን ቃሌ ይፈጸም ወይስ አይፈጸም እንደ ሆነ አንተ ታያለህ” (ዘኍ11፥23) በማለት ሁሉን ቻይነቱን ገለጠለት። እንደተናገረውም በማድረግ በቃኝ እስኪሉ ድረስ መገባቸው።
አንዳንዴ ነገሮች እኛ ባሰብናቸው ልክ አልሄድ ሲሉን፣ ችግር ጭንቅላታችን ላይ ቤቱን ሲሰራብን፣ መፍትሔ እንደ ሰማይ ሲርቅብን፣ የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ጥያቄ ውስጥ እናስገባለን። ማንነቱንም እንረሳለን። ከዚህ በፊት በሕይወታችን የሰራልንን ድንቅ ነገሮች እንዘነጋለን። የእምነታችንም መሰረት ይናጋል። ሕይወታችን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ በሚያልፍበት ወቅት የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት እናስታውስ። የአባታችን እጅ መቼም ቢሆን እንደማያጥር እንገንዘብ። እርሱ ለጥያቄዎቻችንን መልስ፣ ለችግሮቻችን መፍትሔ፣ ለጉድለቶቻችን ሙላት የሆነ አምላክ ነው። በእርሱ ዘንድ ሁሉም ቀላል ነው። ስለዚህ አለማመናችንን አሽቀንጥረን ጥለን፣ የእምነት ካባችንን እንደርብ። በሙሉ ልባችንም “ኤልሻዳይ” ወደሆነው አምላክ እንቅረብ።
ይህ URIM የተሰኘ መንፈሳዊ Channel እንዲያድግ የምንለቃቸውን ፅሁፎች ትምህርቶች ለሌሎች ያጋሩልን።
❤️🔥@Urim7❤️🔥