URIM🔥


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የዚህ ዘመን ቅሬታዎች፣የሀገራችን መድሀኒቶች፣እውነተኛ ክርስቲያኖች፣እግዚአብሄር በሚሰራበት ቀን ገንዘቦቹ ነን።
ክርስቲያን ለሆነ ሁሉ የተከፈተ
URIM
ሁሉን ለወንጌል ብቻ😍
Subscribe Our YouTube Channel
👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@URIMAGAPE?si=JnGurbjzh0clS2B_
@Urim7

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


💐ወድዶኛልና አዳነኝ


📖“ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።”

         መዝሙር 18፥19


አንዱ አካል ከሌላው አካል ጋር ግንኙነት የሚፈጥርበት መንገድ ይለያያል። በሰውኛ መነፅር ሲታይ እነዚህን ሰዎች በአንድ ሕብረት ውስጥ የጨመራቸው የጋራ ፍላጎታቸው ነው። ምን አልባት የግንኙነታቸው መሰረት ገንዘብ፣ ስራ፣ ስልጣን፣ ቁንጅና፣ የትምሕርት ደረጃ ወዘተ ... ሊሆን ይችላል። እነዚህ ከላይ ለመዘርዘር የሞከርናቸው ነገሮች ምን አልባት በፊት እንደነበሩበት ባይቀጥሉና ቢበላሹ፣ ሰዎቹ በፊት የነበራቸውን ሕብረት ይዘው የመቀጠላቸው ነገር ጥያቄ ውስጥ ይገባል።


እግዚአብሔር አምላክ ከሰው ልጆች ጋር ግንኙነትን ሲፈጥር መሰረቱ ፍቅር ነበር። ይህንን ሕብረት ያቋቋመው በሁኔታዎች ላይ ተመርኩዞና ለሰው ልጆች ቅድመ ሁኔታን በማስቀመጥ አልነበረም። ይልቁን ራሱን ተማምኖ ይህንን ስርዓት ዘረጋ። ምክንያቱም “እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።” (1ኛ ዮሐ 4፥8) የመንግስቱም መሰረት ከእርሱ ዘንድ የመነጨውን ይህ ፍቅር ሆነ። ይህም ብቻ አይደለም። ፍቅርን የማወቃችን አንፃራችን ሆነ። “እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤” (1ኛ ዮሐ 3፥16)


የሰው ልጅ ከነበረበት የከፍታ ስፍራ በኃጢአት ምክንያት ቁልቁል ተፈጠፈጠ። ኃጢአትም ይዘርረው ዘንድ በፈቃዱ ነጎደ። ነገር ግን ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኛውን የማይጠላው አምላክ ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ የሰው ልጆችን ለማዳን ሲል ሰው ሆኖ ወደዚች ምድር መጣ። የዕዳ ፅፈታችንን በሙሉ ከእኛ ላይ አስወገደልን። “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤” (ቆላ 2፥14) ኃጢአታችንን ወስዶ በመስቀል ላይ በመንጠልጠል ዳግም ሕይወትን ሰጠን። “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” (1ኛ ጴጥ 2፥24) ይህ ስለ እኔና እናንተ የተከፈለ ድንቅ መስዋዕትነት ነው። ፍቅር ማለት ይህ ነው! ታዲያ ይህን ቤዛነት በመረዳት ፈቃዳችንን በፈቃዱ ውስጥ በመሰወር ልንመላለስ ይገባል። “ወድዶኛልና አዳነኝ” (መዝ 18፥19) የሚለውም ዝማሬ ዘውትር ትዝታችን ይሁንልን።

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


💐በፊትህ


📖“አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።”

          — መዝሙር 19፥14


ዳዊት የፀሎት መዝሙሩን እንደቀጠለ ነው። በዚህ ክፍል ላይ ደግሞ እንዲህ በማለት በአምላኩ ፊት ፀሎቱን ይዞ ይቀርባል፦ “አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።” (መዝ 19፥14)


ከዚህ ከዳዊት የፀሎት መዝሙር በመነሳት በምድር ላይ ያሉ ሰብዓዊያንን በአምስት ክፍሎች መመደብ እንችላለን። አንደኛው ምድብ፣ ከአንደበታቸው የሚያወጡት ቃላቶች ውሸት የሞላባቸውና ልባቸው በትዕቢት የተወጠረ ነው። በሁለተኛው ምድብ የሚገኙ ሰዎች ደግሞ በምላሳቸው ውሃን የሚጠብሱ ደላዬች ከመሆናቸው በተጨማሪ ልባቸው በክፋት የሰከረ መሰሪዎች ናቸው። ለአፋቸው ቃል ለከት የማያበጁ፣ ነገር ግን ልባቸው ንፁህ የሆኑ ሰዎች በሶስተኛው ምድብ ሲመደቡ የአፋቸው ቃልና የልባቸው ሀሳብ "በሰዎች" ዘንድ ያማረ የሆኑት ሰዎች ደግሞ አራተኛውን ምድብ ይይዛሉ። በመጨረሻው ምድብ የሚገኙት ሰብዓዊያን የአፋቸው ቃልና የልባቸው ሀሳብ "በእግዚአብሔር ፊት" ያማረ የሆነ ነው። ምን አልባት "ለምን በእግዚአብሔር ፊት ብቻ? በሰዎችስ ፊት መልካም መሆን የለበትም?" ብለን ጥያቄን ልናነሳ እንችል ይሆናል። በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ቃልና የሰመረ የልብ ሀሳብ በሰዎች ዘንድ ክፉ ሊሆን ከቶ አይችልም።


ምድቤ ከመጨረሻው ይሆን ዘንድ ናፍቆቴና መሻቴ ነው። እናንተስ? የዳዊት መሻት ራሱን ከመጨረሻው ክፍል ማግኘት ነበር። ወገኖቼ፣ የአፋችን ቃል በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ይሆን ዘንድ ያስፈልጋል። ያዕቆብ ይህንን ሀሳብ እንዲህ በማለት ያፀናዋል፦ “አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።” (ያዕ 3፥6) ለዚህ ነው አንደበቶቻችንን ልንገራ የሚያስፈልገው። ነብዩ ኤርምያስ ደግሞ የሰው ልጅ ልብ የአመፅ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?” (ኤርም 17፥9)


ወገኖቼ፣ ዛሬ የለውጥ እርምጃን ልንራመድ ያስፈልጋል። ምን አልባት እስካሁን አንደበታችንን ባለመግራት ብዙ ጥፋቶችን ሰርተን፣ ሰዎችንም አሳዝነን ሊሆን ይችላል። የልባችንም ሀሳብ ከፍቶ እግዚአብሔርንና ሰዎችን በድለን ይሆናል። እንመለስ! ከሁሉ ይልቅ የበደልነው እግዚአብሔርን ነውና አስቀድመን በንሰሃ ፊቱ እንቅረብ። በመቀጠል ደግሞ የበደልናቸውን ሰዎች በመፈለግ ይቅርታን እንጠይቃቸው። ይህን ስናደርግ ሰማይ በታላቅ ደስታ ይሞላል።

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


.   #ፀጋ_ነፃ_እንጂ_ርካሽ_አይደለም!!!

⚡️ ፀጋ ለማይገባው ሰው የሚሰጥ ነፃ ስጦታ ነው።
⚡️ ፀጋ ተቀባዩን የማይመጥን እና የሰጪውን ለጋሽነት የሚያሳይ ድንቅ ነገር ነው።
⚡️ ፀጋ ዋና ዓላማው የአምላክን ህይወት ምድር ላይ እንድንገልጠው የሚያስችል የእግዚአብሔር አቅም ነው።
⚡️ ፀጋ ሰው እድሜ ልኩን ቢለፋ በደሞዝ ወይም በሽልማት ሊያገኘው የማይችል ነፃ እና የእግዚአብሔር የፍቅር ስጦታ ነው።
⚡️ እግዚአብሔር ልጁን እና ከልጁ ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ በፀጋ ሰቶናል። ከእግዚአብሔር ያገኘነው ስጦታ በፀጋ እንጂ እግዚአብሔር እኛ ጋር እዳ ስላለበት አይደለም።
“ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?”
    ሮሜ 8፥32

* የተመረጥነው በፀጋ ነው።
ኤፌሶን 1
⁴ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።⁵ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።⁶ በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።⁷ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።⁸ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።⁹ በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤

* የተጠራነው በፀጋ ነው።
“ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥”
  — 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥9

* የዳነው በፀጋ ነው።
ቲቶ 2
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤

* የምንኖረው በፀጋ ነው።
“ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤”
  — ቲቶ 2፥12-13

* የምናገለግለው በፀጋ ነው።
1ኛ ቆሮንቶስ 15
¹⁰ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።¹¹ እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ።

#የሆነውን_ሁሉ_የምንሆነው_ሁሉ_የምንሆነው_በፀጋ_ነው!!!

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


በረከት የጸጋ፣ የሞገስ፣ የበጎነት ችሮታ ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን ባርኳል፤ እንዲባረኩም ደንግጓል። የአሮን ባርኮት አንዱ ባርኮት ነው፤ ካህናት ሕዝቡን እንዲባርኩ የተሰጣቸው የባርኮት ትእዛዝ። ትእዛዙም "ስሙን በእስራኤል ላይ ስለሚያደርግ" የእግዘብሔርን ባርኮት በሕዝቡ ላይ ያመጣል። የመጀመሪያው አንጓም እንዲህ ይላል፤ "እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ይጠብቅህም" (ዘኁ 6፥24)። እግዚአብሔር ባራኪ ነው፤ ጠባቂም ነው። የርሱ ባርኮት ያገኛቸው ምሕረቱ የደረሳቸው፣ ሞገሱን የተላበሱ፣ በጎነቱ የከበባቸውና ሰላሙ ያገኛቸው ናቸው። እርሱ የሚባርካቸውንም ይጠብቃል፤ ፍጹም በጎነት ከጥበቃ ጋራ ከእግዚአብሔር ብቻ ነው የሚገኘው።

Numbers 6:24
The Lord bless you and keep you;



Join Our Channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


እግዚአብሔር የምህረትና የይቅርታ አምላክ ነው። አንተ አጥፍተህም፣ ርቀህም፣ ደክመህም፣ በብዙ የኅጢዓት ጥልቀት ውስጥ ሆነህም እግዚአብሔር ይታገስሀል። የታገሰህ እንድትቆም፣ እንድትበረታ ብሎ እንጂ ለጥፋትህ እውቅና እየሰጠ አይደለም። የምትታገሰው የምትወደውን ነው። ትወደዋለህ ማለት ትፈልገዋለህ ነው። ወዶክ የታገሰህን ኢየሱስ ማወቅ ትፈልጋለህን? ያሉብህን የትኛውንም አይነት ጥያቄ ልንመልስልህ በዚ አለን!

2 ጴጥሮስ 3:9፤
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
#ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል
#tesfa #hope

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


“በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፤
— ምሳሌ 10፥6

🔥@Urim7🔥


💐ብጠፋም እጠፋለሁ!


📖“ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፤ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ብጠፋም እጠፋለሁ።”

             አስቴር 4፥16


ፍቅር የራሱን የማይፈልግ ንፁህ ስሜት ነው። አንድ ሰው በእንደዚህ አይነት ፍቅር ሲጎበኝ ራሱ እንኳን እያጣ ሌላው ሲያገኝ ከመቅናት ይልቅ ይደሰታል። የእርሱን ማግኘት እንደ ራሱ አድርጎ ይቆጥረዋል። ሀዘኑ ያሳዝነዋል፣ ደስታው ያስቦርቀዋል፣ ችግሩ ያሳስበዋል፣ ጭንቀቱ ይገባዋል።


አስቴር ወገኖቿ ሊጠፉ መሆኑ አሳስቧታል። ምንም እንኳን እርሷ ሁሉ የሞላላት ንግስት ብትሆንም ውጪ ያለው የሕዝቦቿ እሮሮ ግን ጎልቶ ታያት። ታዲያ እንዲሁ ዝም ብላ መቀመጥን አልወደደችም። ይልቁን በንጉሱ የወጣውን ትዕዛዝ ሽራ ወደ እርሱ ለመግባት ወሰነች። ለአክራትዮስም እንዲህ አለችው፦ “ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፤ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፤ ብጠፋም እጠፋለሁ።” (አስ 4፥16)


በአስቴር ዘንድ የተንፀባረቀው ንፁህ ፍቅር የሚያስደንቅ ነው። "ብጠፋም እጠፋለሁ!" በማለት ለወገኖቿ መስዋዕትነትን ለመክፈል ቆርጣ ተነሳች።


ፍቅር እርስ በእርስ በሚኖረን ግንኙነት ውስጥ ጎልቶና ደምቆ ሊታይ ይገባል። የሌሎች ቁስል የእኛም እንደ ሆነ በማሰብ ሸክሞቻችንን እንሸካከም ዘንድ ተጠርተናል። በዓለም ላይ ያለው ሁሉም ነገር ኖሮን ፍቅር ግን ከሌለን ከሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ምስኪኖች ነን። ስለዚህ አንዳችን ለሌሎቻችን "ብጠፋም እንኳን ልጥፋ" እስክንል ድረስ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የፍቅር ሰዎች ያደርገን ዘንድ ልንቃትት ይገባል። እርሱም ፍፁም በሆነ ፍቅር ይባርከናል።

Join Our Channel⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


💐ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና


📖“ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።”

           መዝሙር 62፥5


ሕይወትን ጣፋጭና ተወዳጅ ከሚያደርጓት ነገሮች አንዱ ተስፋ ነው።  ተስፋ የሌለው ሕይወት ካለመኖር ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ይህ ተስፋ አሁናዊ ጨለማችን ነገ ላይ በታላቅ ብርሃን እንደሚለወጥ ለውስጣችን ይነግረዋል። ከዛሬ ነገ የተሻለ እንደሚሆንም ያረጋግጥልናል።


ብዙዎች በተለያዩ ነገሮች ላይ ልባቸውን በመጣል ተስፋ ያደርጋሉ። አንዳንዶች ተስፋቸውን ቁሳዊ ነገር ላይ ይተክሉትና ተስፋ ያደረኩት ነገር አልሆን ሲል ለታላቅ የልብ ስብራት ይዳረጋሉ። ሌሎች ደግሞ "ለእኔ ያለሁት እኔው ራሴ ነኝ" በማለት ራሳቸውን ብቻ ታምነው ተስፋ ያደርጋሉ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉን ቻይ አይደለምና ያሰቡት ነገር በሙሉ ከመሬት ላይደርስ ይችላል። ታዲያ በዚህን ጊዜ "እኔ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም በቃ" በማለት ራሳቸውን ከባድ ጭንቀት ውስጥ ይከትቱታል።


ዳዊት ለነፍሱ እንዲህ ይላታል፦ “ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።” (መዝ 62፥5) እውነተኛውና ዘላቂነት ያለው ተስፋ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው። ማን ነው እርሱን ተስፋ አድርጎ አውላላ ሜዳ ላይ የቀረው? ማንስ ነው በሀዘን ዓይኖቹ የፈዘዘው? ማንም! ስለዚህ ተስፋችንን ከእግዚአብሔር ጋር እናቆራኘው። እርሱ ለተስፋ ቃሉ ታማኝ ነውና።

ይህን ህያው ቃል ለሌሎች አጋሩት🦋

Join Our Channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


“ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።”

         — መዝሙር 72፥18


በዚህች ጥቂት ዕድሜዬ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አይቼ አውቃለሁ። ለአፍታ እንኳን ይሆናሉ ብዬ ያላሰብኳቸው ነገሮች ዕውን ሆነው ሳይ መደነቄን ይጨምረዋል። የትምሕርትና የምርምር ልህቀቱ ከዚህ በኃላ እጅን በአፍ የሚያሲዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መወለዳቸው አይቀሬ መሆኑን ያሳያሉ።


ጊዜ ጊዜን ሲወልድ እንዲህ የተገረምንባቸው ነገሮች እየቀለሉብን ይመጣሉ። እንደዛ ያስደነቀን ፈጠራ ተራ ይሆንብናል። መደነቃችን ይቀርና ሌላ ከዚያ የተሻለ ነገርን በመፈለግ እንጠመዳለን።


እግዚአብሔር ብቻውን ድንቅ የሚያደርግ አምላክ ነው። ለስራው አጋዥ የማያሻው ኃያል ነው። ለአደራረጉ ልክ የሌለው ኤልሻዳይ ነው። እርሱ ዘውትር የማይለመድ ገናና ነው። ዳዊት ይህንን በመገንዘብ ነበር እንደዚህ ያለው፦ “ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።” (መዝ 72፥18) ዛሬም ይህ አምላክ ከእኛ ጋር ነው። በከበደን ነገር ላይ እረፍትን ሊሰጠን እነሆ በደጅ ነው።

Join Our Channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


📖“የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።”

           — መዝሙር 51፥12


ጭው ባለ የበረሃ መንገድ ላይ አንድ ሰውዬ መኪናውን ያሽከረክራል። በጉዞ ላይ እያለ ድንገት አንድ በእድሜ የገፉ ሰውዬ እቃ ተሸክመው ሲሄዱ ያያቸዋል። እርሱም ይሔን እያየ እንዲሁ ጥሎ መሄድ ስላልሆነለት መኪናውን ጥግ አሲዞ ያቆመውና ሰውዬውን በመጥራት ሊሸኛቸው እንደሚፈልግ ይነግራቸዋል። ይሄ ዕድል ደስታን የፈጠረላቸው አባት ሰውዬውን እያመሰገኑ ዕቃቸውን በመያዝ ከኃለኛው የመኪና ክፍል ይቀመጣሉ። ከዛም ጉዣቸውን በወሬ እየተጨዋወቱ ይቀጥላሉ። ድንገት ሹፌሩ የመኪና መስታውቱን ሲያየው ሰውዬው ዕቃውን አሁንም ድረስ እንደተሸከሙት ናቸው። ታሪኩ ሲቋጭ፣ "መሸከምዎ ካልቀረማ በቃ በእግር ይምጡ አላቸው" ይባላል። 


እግዚአብሔር አምላክ ከኃጢአታችን እረፍት ይሰጠን ዘንድ ወደ እኛ ሲመጣ ሸክማችንን ሊያራግፍልን ነው። በማዳኑ ሲጎበኝን ያጎበጠንን የኃጢአት ሸክም ከእኛ ላይ በማራቅ ደስታን ይሰጠን ዘንድ ነው። ታዲያ ጭው ባለ ምድረ በዳ ላይ ሆነን ይህንን የከበረ ዕድል ሲሰጠን በእሽታ መንፈስ ውስጥ ሆነን የበረከቱ ተቋዳሽ ልንሆን ይገባል።


ዳዊት ኃጢአቱ አጉብጦትና ከብዶት ሳለ እግዚአብሔር አምላክ ይምረውና ያሳርፈው ዘንድ ከተፍ ባለለት ጊዜ ይህንን ልመና በአምላኩ ፊት በፍፁም ልቡ አቀረበ፦ “የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።” (መዝ 51፥12)


አዎ፣ እግዚአብሔር ከተበተበን ኃጢአት ማዳን ይቻለዋል። የልምምድ ኃጢአት ገዝፎብን መውጫው በጠፋን ሰዖት መንገዱን ያሳየናል። ኃጢአት ካመጣብን መዘዝ የተነሳ ዘውትር ሀዘንተኞች ብንሆን እርሱ በፀጋው ደስታን ማጥገብ ልማዱ ነው። ታዲያ እውነተኛ የሆነውን ድነትና ደስታ የምንፈልግ ከሆነ ወደዚህ የምሕረት አምላክ በእምነት እንቅረብ። እርሱም በፀጋው አድኖን ፍፁም በሆነው ደስታ ውስጣችንን ይሞላዋል።

Join Our Channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


📖“እንደ ልብህ ይስጥህ፤ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።”

           መዝሙር 20፥4


ዳዊት ምርቃቱን ማዝነቡን እንደቀጠለ ነው። “እንደ ልብህ ይስጥህ፤ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።” (መዝ 20፥4) የሚለውን ምርቃት "አሜን! ይሁንልኝ!" እንላለን።


የልባችን ፈቃድ በፈቃዱ ይተካልን። የእርሱ ሀሳብ ሀሳባችንን ይተካው። ውስጣችን "በጎ፣ ደስ በሚያሰኝና ፍፁም በሆነው" ፈቃዱ ይሞላ። ከሚታየው ይልቅ የማይታየውን ማየት ይሁንልን። ከጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ዘላለማዊ ሀሴትን እግዚአብሔር ያጎናፅፈን። ኃጢአት የሞላበትን የድንጋዩን ልብ አውጥቶ በፅድቅ የተሞላ የስጋን ልብ ይስጠን።


አሜን! አሜን! አሜን!...


የልባችንን ምኞት እንደ መልካም ፈቃዱ ይስጠን። እንዲህ ቢሆንልኝ ብለን የምናስበው ነገር ሁሉ ይሳካልን። ፈቃዳችንን ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ይፈፅምልን። የሸለቆው ሕይወታችን ያብቃልን። ወደ ከፍታ መውጣታችን ይፍጠንልን። ካለንበት ስፍራ መስፈንጠር ይሁንልን። የውድቀት ዘመናችን ያብቃልን። የከፍታችን ዘመን ይምጣልን። የእሮሮው ጊዜ አክትሞ እልልታችን ይምጣ።


አሜን! አሜን! አሜን!...

Join Our channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


💧የሕይወት ውሃ💧

📖"ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ። ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 7:37)

😭በዚህ ምድር ላይ ያለ የትኛውም ነገር የነፍስን ጥማት ማርካት አይችልም። ነፍሳችን ዙሪያችን ባሉ ሰዎች ወይም ባከማቸነው ገንዘብ እርካታን አታገኝም።

🚰ነፍስ እውነተኛ እርካታን ምታገኘው ከፈጠራት ከእግዚአብሔር ነው።

✅ከእግዚአብሔር የተቀበልነው የሕይወት ውሃ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ግን የነፍሳችንን ጥማት ለዘላለም ማርካት ይችላል።

Join Our Channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


ታመኑ!

#በማንም አትታመኑ ብቸኛ መደግፊያ እየሱስ ነው።

ሰው መሽሽጊያ ቢያጣ አባቱ ጋ ወይ እናቱ፣እህት፣ጓደኞቹ ዘመድጋር ይሸሸጋል እነኚህ ባይኖሩትም ሌላ የት ይኬዳል ጴጥሮስ እንዳለው ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤” ዮሐንስ 6፥6

እኛ ግን ሁሉ ቢኖረን እንኳ እንተ ከሌለህበት ሙት ባህር ውስጥ እንደተጣለች ኳስ እንሆናለን ወዴት እንደምትሄድ እንደማታውቅ ንፋስ መጥቶ ወደ ፈለገበት የሚወስዳት ምስኪን ነበርን እኛ ግን ስለምንታመንብህ መድረሻችን ሳንጀምረው አውቀናል።

እግዚአብሔር ማመን ማለት 50%፣ 60% ራስን ለእግዚአብሔር ማስገዛት አይደለም❌❌
100% ራስን ለመንፈስ ቅዱስ ማስገዛትና✅ መስጠት ነው።

ከሰማሁት ሳይሆን ካለፍኩት ህይወት እንዴ እሱማ እሷማ በችግሬ ይደርሳል ብላቹ በሙሉ ልባቹ ያመናቹት ሰው እንኳ ቢኖር ልብን 💔 ከላይ ወደ ታች ያወርዳል

የተናገረው 💯 ያደርገዋል ደግሞም እግዚአብሔር በጨለማ ይተወን ዘንድ ክፉ አይደለም ብቻ ታመኑት!


“እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።”
  — ሐዋርያት 16፥31

Join Our channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


ካነበብኩት😇

የወርቅ መንገድ👣

መፅሀፍ ቅዱስ ክርስቲያን በሞት ጥላ መካከል አያልፍም አይልም: ነገር ግን "በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔጋር ነህና ክፉን አልፈራም" (መዝ 23:4) ይላል እንጂ።  ይህ መንገድ ፣ ለባለራዕይዮች የእምነት ፤ የትምህርት ፤ የመዝሙር መንገድ ነው። የእግዚአብሔር መንገድ በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ፤ በአንድ ጊዜ አንድ ቀን ነው። ጥያቄው በዚህ መንገድ ውስጥ ምን እና ማን አለ ነው ። ለመለኮታዊ አናጺ፣ ምድረበዳው ፤ ጨለማው፤ ብቸኝነቱ፤ ጥሩ የስራ ቦታው ነው ።

እኛ ክርስቲያኖች በዚህ መንገድ ፤ ተሰርተን ስናበቃ አይኖቻችን የከበረን ነገር የሚያዩበት ፤ የምንከብርበት ፤ የምንማርበት፤ ልዩነት የምንፈጥርበት፤ የምንሰማበት፤ ከሀይል ወደ ሀይል ከክብር ወደ ክብር የምንለወጥበት ይሆንልናል።

Join Our channel⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


ክርስቶስን ከተውከው ከቀንህ ላይ ፀሀይን እንደማውጣት፤ከለሊትህም ላይ ጨረቃን እንደማንሳት፤ከባህር ውስጥ ውሃን እንደማጥፋት፤ከወንዝ ውስጥም ጓርፍን እንደመተው፤ከእርሻህ ላይ ሰብልን እንዳለመሰብሰብ፤ከስጋ ውስጥ ነፍስን እንደማውጣት፤ከመንግስተ ሰማያት ውስጥ ሃሴትን እንደማጣት፤ሁሉን ተዘርፎ እንደማጣት ነው።

   ቻርለስ ስፐርጅ

Join Our Channel ⭐

 🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


💧የሕይወት ውሃ💧

📖"ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ። ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 7:37)

😭በዚህ ምድር ላይ ያለ የትኛውም ነገር የነፍስን ጥማት ማርካት አይችልም። ነፍሳችን ዙሪያችን ባሉ ሰዎች ወይም ባከማቸነው ገንዘብ እርካታን አታገኝም።

🚰ነፍስ እውነተኛ እርካታን ምታገኘው ከፈጠራት ከእግዚአብሔር ነው።

✅ከእግዚአብሔር የተቀበልነው የሕይወት ውሃ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ግን የነፍሳችንን ጥማት ለዘላለም ማርካት ይችላል።

Join Our Channel ⭐

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


⚜️ ማርታን መሆን አያዋጣም


👉🏻 ወዳጆቼ ጌታን ከሩቅ እያያቹት ስራቹ ላይ ብቻ ተፍ ተፍ  ማለታቹ አያዋጣቹም   የግድ ደግሞ ስኬታማና የተሳካለት ሰው ለመሆን ሁሉንም ነገር ማግበስበስ አይጠበቅባቹም

✅ የሚያዋጣው ማርታን መምሰል ሳይሆን ማሪያምን መሆን ነው ጌታም ለዚህ ነው የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው ማርያምም መልካሙን መርጣለችና እርሱም ከእርሷ አይወሰድባትም ብሎ የተናገረው እውነት ነው የሚያስፈልገው አንድ ነገር ነው እርሱም ለጌታ መሆን ፤ ይሄን ስል ደግሞ ቁጭ ብላቹ ተቀመጡ ማለቴ እንዳልሆነ መቼም ትረዱኛላቹ

❗️ ገንዘቡም ፣ ድግሱም ፣ ስራውም ፣ ቡናውም ፣ ጫወታውም ፣ ሶሻል ሚዲያውም ፣ ጓደኞቻቹም ከጌታ በኃላ መድረስ ስለሚችሉ ቅድሚያቹን ሁሉ ለጌታ ስጡት።

Join Our Channel🌟

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


ሕግህ ደስታዬ ባይሆን ኖሮ፣
በመከራዬ ወቅት በጠፋሁ ነበር።
በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና፣
ትእዛዝህን ከቶ አልረሳም።
መዝሙር 119:92-93

🔥@Urim7🔥


አማኞች ለእግዚአብሔር ጥልቅ ፍቅር ሲኖራቸው፣ ለሀጢያት ፍጹም ጥላቻ ሲሰማቸው፣ አለምን ሲጠሉ፣ የክርስቶስን መምጣት በናፍቆት ሲጠባበቁ፣ ሌሎች ክርስቲያኖችን ሲወዱ፣ የጸሎታቸውን መልስ ሲያገኙ፣ እውነትና ስህተትን ሲለዩ እና ክርስቶስን መምሰል ሲናፍቁ በእነርሱ ላይ ያለውን የመንፈስ ቅዱስን ስራ ይመሰክራል።

      __ጆን ማክአርተር

🔥@Urim7🔥
🔥@Urim7🔥


🔤🔤🔤🔤

ፍቅርን ፍቅር ያዘው

*ኤሮስ የሚባል የፍቅር አይነት አለ ይሄ ፍቅር እርስ በእርስ በሚፈላለጉ ሰዎች መካከል የሚፈጠር ነው ።
* ስቶርጌ ረጅም ጊዜ በማሳለፍ አብሮ በመቆየት የሚፈጠር የፍቅር አይነት ነው።

* ሜኒያ  የሚያውቁትን ሰው የማፍቀር የመውደድ አይነት ነው።  ለምሳሌ ታዋቂ ሰዎችን ....

👉አጋፔ ይሄ የፍቅር አይነት ከሁሉም ይለያል ምክንያቱም ይሄ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው።
ሆሴዕ 1_3
* ጎሜር በሆሴዕ ለመወደድ ምንም አይነትና ብቃት የላትም ምክንያቱም እሷን ሴተኛ አዳሪ/ ጋለሙታ ሴት ስለሆነች ።
1ቆሮ 1:18_19
ሆሴዕ_3

👉 የኢየሱስ ደም እንዲፈስልን ምንም አይነት ብቃት ችሎታ የለንም  የምንወደድበት አቅም የለንም እንዲሁ እሱ ግን ያለ ምክንያት ወዶናል።

👉ኢየሱስ እኛን ሲወድ የዘለአለም ህይወት ሰጥቶናል
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።”
  — ቲቶ 3፥3


“ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።”
  — ዮሐንስ 15፥13

👉በዘለአለም ፍቅር ወዶናል
ሮሜ5:7_8
👉ያለምክንያት ገና ሀጥያተኞች ሳለን ወዶናል

" በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።”
  — ዮሐንስ 13፥1
ዮሐ 17
ዮሐ ።3:16



ፍቅርን ፍቅር ሲይዘው

👉 የወደደውን ሆነ
👉 ስለ ሀጥያተኞች በመሞት ፍቅሩን ገለጠ ሮሜ 5:18
👉ያለምክንያት ወደደን
👉በማይለወጥና በይናወጥ ፍቅር ወደደን


የነሀሱ እባብ vs   ኢየሱስ
_ ለእስራኤላዊያን  👉ለዓለም ሁሉ
_ ለስጋ በሽታ      👉ለሀጥያት
_ከጊዜያዊ ሞት 👉ከዘለአለም ሞት
_ በመመልከት 👉 በማመን

👉ሆሴዕ ጎሜርን በብርና በወርቅ እንደገዛት ኢየሱስ እኛን በገዛ ደሙ ዋጅቶናል /ገዝቶናል ።


አገልጋይ _ ዘለአለም (zed)

🔥@Urim7🔥

Показано 20 последних публикаций.