ሰው አምላክ ሆነ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
5፥17 እነዚያ "አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አል መሢሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ
ዐበይት አበው "አምላክ ሰው ሆነ" ብቻ ሳይሆን "ሰው አምላክ ሆነ" ብለው ያምናሉ፥ በጣም ሥመ ጥር እና ገናና የቤተክርስቲያን አባት ዮሐንስ አፈ ወርቅ"John Chrysostom" እንዲህ ይለናል፦
"አምላክ ሰው ሆነ ሰውም አምላክ ሆነ"።
St.John Chrysostom homily 11 on first Timothy 1 Timothy Chapter 3 Number 16
ድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረው ሰው "አምላክ ሆነ" የሚለው ትምህርት በሰፊው በአበው የሚነገር ነው፥ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ"Gregory of Nazianzus" እራሱ "ሰብእ ዘኮነ አምላክ" በማለት "ሰው አምላክ ሆነ" ይለናል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 61 ቁጥር 23
"ሰው አምላክ ሆነ"
አንድምታ ላይም "አምላክ ሰው ሆነ" የሚሉ ምንባባት በሰፊው አሉ፦
ዮሐንስ 2፥14 አንድምታ፦ "አምላክ ሰው ሆነ፥ ሰው አምላክ ሆነ" እያሉ ርደቱን እና ዕርገቱን ለመንገር።
ሉቃስ 2፥14 አንድምታ፦ "አምላክ ለሆነ ሥጋ ከሥላሴ ጋር በአንድነት ምስጋና ይገባዋል፥ ወሰላም በምድር "ሰው አምላክ ሆነ" እያሉ።
የሚገርመው ቄርሎስ ዘእስክንንድርያ"Cyril of Alexandria" በድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረው ሥጋ "አምላክ ነው" በማለት ተናግሯል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 78 ቁጥር 31
"ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ሥጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን"።
ከፍጡር የሚገኝ ሥጋ ፍጡር ሆኖ ሳለ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ"Athanasius of Alexandria" ሳያቅማማ "የባሕርይ አምላክ ነው" በማለት ይናገራል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 29 ቁጥር 19
"ከእመቤታችን ከቅድስት ከድንግል ማርያም የነሳው ይህ ሥጋም እውነተኛ የባሕርይ አምላክ ነው"።
ከአምላክ ያልተገኘ ሥጋ እና ከፍጡር የተገኘን ሥጋ "የባሕርይ አምላክ ነው" ማለት የጤና ነውን? ፈጣሪ ድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ የፈጠረውን ፍጡር አምላክነት ከሰጠ እራሱ የራሱን ባሕርይ እያጋራ ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 31 ቁጥር 18
"ሥጋ አምላክነትን የማይመረመር ጌትነትን አገኘ"
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 66፥ ቁጥር 15
"ሥጋ የፈጣሪ አካል ባሕርይ በሆነ ጊዜ ፍጹም አምላክነትን አገኘ"
ሰውን ወደ አምላክነት ከፍ ማድረግ እና እግዚአብሔር ወደ መሆን ከፍ ማድረግ ጣዖት ማስመለክ ነው፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 21 ቁጥር 14
"ሰውነት በመለኮት አምላክ ሆነ"
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 29 ቁጥር 53
"እግዚአብሔር ሰው ሆነ ሰውን ወደ አምላክነት ከፍ አደረገው"
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 11 ቁጥር 10
"ከዳዊት ሴት ልጅ የነሳውን ሥጋ ግን በአንድ አካል ከሆነው ከመለኮት ጋር አዋሐደው፥ እንዳይለይ እግዚአብሔር ወደ መሆን ከፍ አደረገው"
ሰው አምላክ ሆነ ማለት ሁሉን ዐላዋቂ ሁሉን ዐዋቂ ሆነ፣ ሁሉን የማይችል ሁሉን ቻይ ሆነ፣ የሚሞት የማይሞት ሆነ፣ የሚተኛ የማይተኛ ሆነ፣ ግዙፍ ረቂቅ ሆነ፣ ስሉጥ ምጡቅ ሆነ እያላችሁን ነው። ሥጋን እግዚአብሔር ማድረግ እና ማስመለክ ባዕድ አምልኮ ነው፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 17 ቁጥር 12
"መለኮት ትስብእትን ባማረ "አምልኮ" ባሕሪያዊ ምስጋና አሳተፈው"
ፍጡሩ ትስብእት አምልኮን ሲሳተፍ አይታያችሁምን? ፍጡሩ ትስብእት አምላክነት እና አምልኮ ያገኘው፦
፨ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ "ከአምላክ ጋር በመዋሐድ ነው" ሲሉ፣
፨ ኦርቶዶክስ ቅብዓት "በአብ ቀቢነት በመቀባት ነው" ሲሉ፣
፨ ኦርቶዶክስ ጸጋ ደግሞ "በአብ ጸጋ ነው" ሲሉ፣
፨ ኦርቶዶክስ ካራ "ሦስተኛ ልደት እና በራሱ ቀቢነት በመቀባት ነው" ይላሉ።
ምን አለፋችሁ ድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ የተፈጠረው ፍጡር "ከሦስቱ የሥላሴ አካላት አንዱ ሆነ" እያሉን ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 77 ቁጥር 2
"በኃለ የተገኘን ሥጋ ሊዋሐደው ከዳዊት ባሕርይ እርሱ ፈጠረ እንደ ተጻፈ ከሦስቱ አካላት አንዱን አደረገው"።
"ኮሊሪዲያን"Collyridian" የሚባሉት ማርያማውያን "ማርያም አምላክ ሆነች" ብለው ማርያምን ማምለክ የጀመሩበት ምክንያት "የማርያምን ሥጋ እና ደም አምላክ ሆነ" በሚል ትምህርት ነው፥ "የሰው እናት ሰው ናት፥ የአምላክ እናት አምላክ ናት" በሚል ብሒል ማርያምን ያመልኳት ነበር።