#ለመረጃ፡ የጉምሩክ ኮሚሽን በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሉታ) ጥሬ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ ኩባንያዎች የሚያቀርቧቸው የኤሌክትሮኒክ የማጓጓዣ ሰነዶች ተቀባይነት አግኝተው እንዲገለገሉ ፈቀደ፡፡
ሪፖርተር የተመለከተውና በጉምሩክ ኮሚሽነሩ አቶ ደበሌ ቃበታ ተፈርሞ ለሁሉም የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለሚፈጸምባቸው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች የተመራው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ሌሎች በሕግ የተገለጹ ደጋፊ ሰነዶች መሟላታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሉታ) ሥርዓት ጥሬ ዕቃ ወደ አገር የሚያስገቡ ኩባንያዎች ብቻ የሚያቀርቡት የቴሌክስ ሪሊዝ (Telex Release)፣ ሲ ዌይቢል (Sea Waybill) ሰነዶች እንደ መጓጓዣ ሰነድ ተቀባይነት አግኝተው ተገቢው አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
ቴሌክስ ሪሊዝ (Telex Release) ግዥ ለተፈጸመበት ዕቃ መርከብ ላይ መጫኑ ሲረጋገጥ አጓጓዡ ወይም የአጓጓዡ ወኪል (Agent) በየትኛውም ቅርንጫፍ ዋናውን ቅጂ በማስገባት (Surrendered)፣ ሰነዶቹን የተቀበለው አጓጓዥ ድርጅትም ሆነ የአጓጓዡ ወኪል ዋናውን ቅጂ መቀበሉን በማረጋገጥ ለመዳረሻ ወደብ (Destination Port) ዕቃው እንዲለቀቅ በኤሌክትሮኒክ መልዕክት የሚያስተላልፍበት ሥርዓት ነው፡፡
ሲ ዌይቢል (Sea Waybill) ደግሞ አጓጓዡ ድርጅት (Carrier/Shipping Line) ዕቃውን ስለመቀበሉ የሚረጋገጥበትና የመጓጓዣ ውል ማስረጃ ሆኖ የሚያገለግል ሰነድ ሲሆን፣ መዳረሻ ወደብ ደርሶ ክሊራንስ ከመጠናቀቁ በፊት ባለቤትነት ማስተላለፍ የማይቻልበት ነው፡፡
በተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጪ የሚገኙ አምራቾች ጥሬ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ ቴሌክስ ሪሊዝ (Telex Release) እንዲሁም ሲ ዌይቢል (Sea Waybill) የማጓጓዣ ሰነድ እንደሚጠቀሙ በመግለጽ፣ በእነዚህ ሰነዶች አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ታውቋል፡፡
የዕቃ ዲክላራሲዮን በኤሌክትሮኒክ ሰነድ መቅረብ እንደሚችልና ወደ አገር ለሚገቡና ለሚወጡ ዕቃዎች ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ለመፈጸም የሚቀርቡ ደጋፊ ሰነዶችን ለመወሰን ሥልጣን የተሰጠው ኮሚሽኑ፣ የተሻሻለውን የጉምሩክ አዋጅ 859/2014 መሠረት በማድረግ ኩባንያዎች ውጭ አገር ከሚገኝ ላኪ ድርጅት ጋር ባላቸው ስምምነት መሠረት የሚላኩላቸውን ጥሬ ዕቃዎች ለመቀበል የሚጠቀሙበት ሥርዓት በመሆኑ ውሳኔውን ተግባራዊ ማድረግ እንዳስፈለገ አስታውቋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን እንዳስታወቀው ቴሌክስ ሪሊዝና ሲ ዌይቢል ሥርዓት በሌሎች አገሮችም ንግድን ለማቀላጠፍ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡
ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሎጂስቲክስ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የጉምሩክ ኮሚሽን ቴሌክስ ሪሊዝና ሲ ዌይቢል እንደ ሕጋዊ የማጓጓዣ ሰነድ አድርጎ መቀበሉ፣ ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ ዕቃዎች የማጓጓዝ ስታንዳርድ ጋር የሚያስተሳስር ነው ብለዋል፡፡
ባለሙያዎቹ በተጨማሪም ኮሚሽኑ የፈቀደው ይህ ሥርዓት የሎጂስቲክስና የጭነት አስተላላፊነት አገልግሎት አሠራርን ከማስተካከል ባሻገር፣ ፍጥነትና ቅልጥፍናን እንደሚጨምር አስረድተዋል፡፡
መረጃው የሪፖርተር ነው!