#የጂላኒ_ረቡዕ
ሸይኽ ዑመር አብዱል ባዝ (ረዲየላሁ አንህ) እንዲህ ይላሉ፡- “አንድ ጁምዓ ከሰይዲ ሸይኽ አብዱልቃድር ጂላኒ (ረዲየላሁ አንህ) ጋር ወደ መስጂድ ጉዞ ወጣን። ሰዎች ቢያዬቸውም ማንም ሰላምታ የሰጣቸው አልነበረም። በልቤ አሰብኩ፡- “ዘውትር ጁምዓ ወደ መስጂድ ለመድረስ በሼክ አካባቢ ይሰበሰቡ የነበሩት ሰዎች ዛሬ ምን እየሆኑ ነው?” ወዲያው ሰዎች ሼክን ለመዘየር ሲጣደፉ አየሁ። ሰይዲም በፈገግታ አዩኝና “ዑመር ሆይ፣ የፈለከው ይህንኑ ነው! የሕዝቡ ልብ በእጄ እንዳለ አላስተዋላችሁምን? ከፈለግኩ ከኔ አርቃቸዋለሁ፣ ከፈለግኩ ወደ እኔ እስባቸዋለሁ።
በአንድ ወቅት አብዱልቃድር (ረዲየላሁ አንህ) ንግግር ሲያደርጉ አቡል ሙዓሊ የሚባል ሰው በዚህ ስብሰባ ላይ ተገኝቷል። እሱ በቀጥታ በታላቁ ቅዱሳን ፊት ተቀመጠ። በትምህርቱ ወቅት አቡል ሙዓሊ የሑዙር ጂላኒ (ረዲየላሁ አንህ) መሰባሰብን መልቀቅ ክብር የጎደለው ሆኖ ስላገኘው ይህንን ፍላጎት ለመግታት ሞክሯል። ከዚህ በኋላ አቅቶት ለመሄድ ወሰነ። ይህ ሲሆን አቡል ሙዓሊ በስብሰባ ላይ ሳይሆን ውብ ለምለም ባለው ሸለቆ ውስጥ እንዳለ አወቀ። በወንዙ ውስጥ በሚፈስ ጅረት የበለጠ ተውቧል። ወዲያው የተፈጥሮን ጥሪ ተቀብሎ ዉዱእ አደረገ ከዚያም ሁለት ረከዓ ሰላት ሰገደ። ሶላትን እንደጨረሰ አሁንም በታላቁ ቅዱሳን ስብስብ ውስጥ መመለሱን ተገነዘበ። ነገር ግን ብዙ ቆይቶ አቡል ሙዓሊ የሱ ቁልፎች ከእሱ ጋር እንዳልነበሩ አወቀ። ከዚያም በሁዙር ጋውስ-አእዛም (ረዲየሏሁ ዐንህ) ጋር ወደ ሸለቆው ሲጓጓዝ ከወንዙ አጠገብ ባለው የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ የቁልፍ ቀለበቱን ሰቅሎ እንደነበር አስታውሰ። አቡል ሙዓሊ ከዚህ ክስተት በኋላ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለንግድ ጉዞ የመሄድ እድል አገኘ። በዚህ ጉዞ ውስጥ አንድ ሸለቆ ደረሰ እና እዚያ አረፈ ከዚያም ሸለቆው በትምህርቱ ወቅት የተጓጓዘበት ቦታ መሆኑን አስተዋለ ከዛፉ አጠገብ ሲሄድ ቁልፎቹ አሁንም በዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ተንጠልጥለው አገኘው። ሱብሃነላህ!
የሑዙር ጓውስ-አእዛም ተማሪዎች እንደተለመደው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በድንገት የሼኻቸው የተባረከ ፊት ሲቀላ እና ላብ የተባረከውን ፊታቸውን ሸፍኖ እንደነበር ይገልጻሉ። ከዚያም እጃቸውን ካባው ውስጥ አስገብተው ለጥቂት ጊዜ ዝም አሉ። እጃቸውን ከካባው ውስጥ ካወጡ በኋላ፣ ከእጅጌቸው ውስጥ የውሃ ጠብታዎች ይንጠባጠቡ ጀመር። ከመንፈሳዊ ሁኔታቸው የተነሣ ተማሪዎቹ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረቡም ይልቁንም ይህን አስደናቂ ክስተት ቀን፣እና ሰዓቱን መዝግበውታል። ይህ ክስተት ከተፈጸመ ከሁለት ወራት በኋላ በባህር ወደ ባግዳድ የመጡ ነጋዴዎች ደርሰው ለሑዙር የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተዋል። እነዚህን ነጋዴዎች በባግዳድ ከዚህ በፊት ታይተው ስለማያውቁ ተማሪዎቹ በዚህ ግራ ተጋብተው ነበር። ስጦታውን ያመጡበትን ምክንያት ነጋዴዎቹን ሲጠይቋቸው ከሁለት ወራት በፊት ወደ ባግዳድ በመርከብ ላይ እያሉ መርከባቸው በኃይለኛ ማዕበል ተያዘች። የመስጠም አደጋ እንዳለ ሲገባን ወደ ሸይኽ አብዱልቃድር ጂላኒ ተጣራን። ወደርሱም በተጣራን ጊዜ ከሩቅ አንዲት እጅ መርከቦቻችንን ወደ ላይ አነስታ ስጋት ከሌለበት የባህር ክፍል አሳረፈች። ተማሪዎቹ ይህንን ዘገባ በመድረሳ ውስጥ ከተፈጠረው ክስተት ጋር ሲያነፃፅሩ ታላቁ ቅዱሳን እጃቸውን ወደ ካባው ያደረጉበት፣ ቀንና ሰዓት እንደሆነ ተረጋግጧል። ሼክ አብዱልቃድር ጂላኒ እጃቸውን ወደ ካባው ውስጥ የሚያስገቡ ቢመስልም በተጨባጭ ግን ለእርሳቸው እርዳታ የጠየቁትን ለመርዳት እጃቸውን ወደ ባህር እየዘረጉ ነበር። ሱብሃነላህ!
በሑዙር ዝና በጣም የተደነቀች የባግዳድ እናት ልጇን በእጃቸው ለመተው ወሰነች እና “ይህን ልጅ እንደራስህ ውሰደው፣ እንዳንተ እንዲሆን አሳድገው” አለች። ሼክም ልጁን ተቀብለው አምልኮትን፣ መንፈሳዊነትን ወዘተ ያስተምሩት ጀመር።ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እናትየዋ ልጇን ለማየት መጣች እና ቀጥኖ እና ገርጥቶ አንድ ቁራሽ እንጀራ ሲበላ አየችው። ተናደደች እና ሼኩን እንድታይ ጠየቀች። እሷም በመጣች ጊዜ ሁዙር በደንብ ለብሰው፣ ደስ የሚል ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ዶሮ ሲበሉ አገኘቻቸው። እሷም “ዶሮህን እየበላህ ላንተ የተውኩት ምስኪን ልጄ ከደረቅ እንጀራ በቀር ምንም የለውም!” ብላ ጮኸች። ሼኩ እጃቸውን በዶሮው አጥንት ላይ አስቀምጠው "አጥንቶችን ከአፈር በሚያነቃቃው በአላህ ስም ተነሳ!" ሲሉ ተናገሩ ዶሮዋ ወዲያው በህይወት ጉብ አለችና “ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መልእክተኛው ናቸው ሼክ አብዱልቃድር የአላህና የመልእክተኛው ወዳጅ ናቸው!” ብላ በጠረጴዛው ዙሪያ ሮጠች። ሁዙር ጂላኒ ወደ ሴቲቱ ዞር ብለው “ልጅሽ ይህን ማድረግ ሲችል የፈለገውን መብላት ይችላል” አሎት። አላሁአክበር
አንድ ጊዜ ጂላኒ ንግግር ሲያቀርቡ ሸይኽ አሊ ቢን ሄይቲ (ረዲየላሁ አንህ) ከፊታቸው ተቀምጠዋል። በትምህርቱ ወቅት ሸይኽ አሊ ቢን ሄይቲ (ረዲየላሁ አንህ) እንቅልፍ ወሰዳቸው። ሁዙር ጓውስ-አእዛም (ረዲየላሁ አንህ) ይህንን አይተው ከሚንበር ወርደው በእንቅልፍ ላይ ካሉት ሸይኽ አሊ ቢን ሄይቲ ፊት ለፊት ሁለት እጆቻቸውን በአክብሮት አጣጥፈው ቆሙ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሼክ አሊ ቢን ሄይቲ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሁዙር ከፊታቸው ቆመው አገኞቸው። ወዲያው በአክብሮት ከተቀመጡበት ተነሱ። ሁዙር ፈገግ ብለው እንዲህ አሉ፡- በአክብሮት ፊትህ የቆምኩበት ምክንያት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ ) በሥጋዊ ዓይኖቼ ከአጠገብህ መመልከቴ ነበር።
ሼክ አዲ ኢብኑ ሙሳፈር (ረዲየላሁ አንህ) እንዲህ ይላሉ፡- “በአንድ ወቅት ሁዙር ንግግር ሲያደርጉ ዝናብ ከሰማይ ወረደ። ይህም አንዳንድ ታዳሚዎች እንዲበታተኑ አደረጋቸው ሼኽ አንገታቸውን ወደ ወደ ሰማይ አንሥተው፡- “እነሆ እኔ ለአንተ ስል ሰዎችን እየሰበሰብኩ እንዲህ ከኔ ትበትናቸዋለህ” አሉ። ዝናቡ ወዲያው ትምህርቱ በሚካሄድበት ግቢ ላይ መዝነቡን አቆመ፣ ምንም እንኳን ዝናቡ ሳይቀዘቅዝ ከትምህርት ቤቱ አከባቢ አልፎ ቢቀጥልም በስብሰባው ላይ አንዲት ጠብታ ዝናብ አልዘነበችም። ሱብሃነላህ!
ሸይኽ አህመድ ጃም (ረዲየሏሁ ዐንህ) የሚባሉ ታላቅ ቅዱሳን ነበሩ በየሄዱበት አንበሳ ላይ ይጓዙ ነበር። በጎበኙበት ከተማ ሁሉ የከተማዋን ህዝብ አንድ ላም ለአንበሳው ምግብ እንዲልክላቸው መጠየቅ ልማዳቸው ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ወደ ባግዳድ ሄዱ ከደቀ መዛሙርቱ አንደኛውን ወደ ሁዙር ላኩ ለአንበሳው ማዕድ ላም አንዲላክለት አዘዘ። ታላቁ ጋውስ መምጣቱን አስቀድሞ ያውቁ ነበር ለአንበሳው አስቀድመው ላም አዘጋጅተው ነበር። ደረሳው ላሙን ይዞ ሲሄድ ከሁዙር ቤት አካበቢ ላይ ተቀምጦ የነበረ ያረጀ ውሻ ተከተለው። ለሼኽ አህመድ ጃም ላሙን ሰጣቸው ሼኹም ለአንበሳው ላሟን እንዲበላ ነገሩት። አንበሳው ወደ ላሟ ሲሮጥ ደካማው ውሻ አንበሳውን ወረወረ ጉሮሮውና ሆዱን በመቅደድም ገደለው። እየጎተተም ከሁዙር ፊት አቀረበው። ይህን ሲመለከቱ ሼህ አህመድ በታላቁ ገውስ ፊት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ለትእቢታቸው ይቅርታ ጠየቁ።
*አላሁ ተአላ ለሁዙር እውነተኛ ፍቅር ይስጠን! እንደ ደካማው ውሻ በሱልጣን አውሊያ አብዱልቃድር ጂላኒ አገልግሎት ስር ያድርገን! አሚን!
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM