ከ65 ዓመታት በኋላ ታሪክ ሊደገም ነው !!
አንጋፋው ወንጌላዊ #ቢሊ ግራሃም በንጉሱ ጊዜ ነው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመጀሪያ ጊዜ የጀማ ወንጌል የሰበኩት። ለዚህ ስራቸውም ከንጉሱ ዘንድ ምስጋና ተችሯቸው ነበረ።
ዛሬ በሳቸው እግር የተተካው ልጃቸው ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም፣ ታላቅ የወንጌል ድግስ አዘጋጅቷል።
“መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል፣ የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ታላቅ የወንጌል ድግስ ይካሄዳል። ከሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር በሚኖረው የአደባባይ ድግስ፣ የጸሎት፣ የወንጌል ስብከት እና የዝማሬ ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል።
ፕሮግራሙን የቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከካውንስሉ ጋር በጋራ በመሆን ነው ያዘጋጀው። በፕሮግራሙ ከሃአር ውስጥ ዘማሪዎች፣ መጋቢና ዘማሪ አገኘሁ ይደግ፣ዘማሪ አቤኔዘር፣ ዘማሪ ጉቱ እና ከውጪ ሃገራት የተጋበዙ ዘማሪዎች በመድረኩ ያገለግላሉ።
ድግሱን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያዋ የሚገኙ ክርስቲያኖች የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዚህ የጸሎት፣ የወንጌል እና የምስጋና ድግስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሬቨረንድ ፍራንክሊን የሰማሪታን ፐርስ ፕሬዝደንት ሲሆኑ፣ ተቋሙ ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተራድኦ ስራን ሲሰራ ቆይቷል።
Christian post
✨ @yeadonaimedia ✨