የአዶናይ ሚዲያ | YEADONAI MEDIA ™🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


_ እ ን ኳ ን ደ ህ ና መ ጡ !
ይህ ቻናል በዋናነት መንፈሳዊነት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ሲሆን መንፈሳዊ ሰው ሁለንተናዊ ልዕቀት ሊኖረው ስለሚገባ ለሁለንተናዊ ልዕቀትም አፅንኦት ሰተን እንሰራለን።
የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን🙏
(ቻናሉ ሐምሌ 30- 2011 ተጀመረ)
📧ሀሳብ አስተያየታችሁን በ @Yeshewu ላይ ላኩልን👍

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




. ኢየሱስ ይላል!!
Cover worship
ዘማሪ አቤኔዘር ታገሰ
መዝሙሩ የፓ/ር ተስፋዬ ገቢሶ ነው
!
በጣም የወደድኩት ዝማሬ ነው ተጋበዙልኝ😍


💯 share 💯
@yeadonaimedia
@yeadonaimedia




የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ከሚሊኒየም አዳራሽ ኑ የአምልኮ ኪዳናችንን እናድስ ዘማሪት ሊሊ ጥላሁን፣ ዘማሪት ቤቴሌሔም ወልዴ፣ ዘማሪት አዜብ ሐይሉ እያስመለኩ ነው የሚገኙት ከላይ ያለውን ሊንክ በመንካት ተካፋይ ሁኑ!




መልዕክቱ ይሰራጭ‼
#ScamAlert
✍ ኧረ! ይሄን የጥንቃቄ መልዕክት በአስቸኳይ ሼር አድርጉት!

ብዙ ሰው እየተሸወደ ነው።
«የቴሌግራም ፕሪሚየም በነፃ ተቀብለዋል!» የሚል የአማርኛ ጽሑፍ ከስሩ ሊንክ ያለው እየተሰራጨ ነው።
ልብ በሉ! ሊንኩን ከተጫናችሁት አካውንታችሁ 100% ተጠልፏል።

በምታውቁት ሰው አካውንት ቢላክም፤ አውቆ ሳይሆን እርሱም ተበልቶ ነው።
ሊንኩን በፍፁም እንዳትከፍቱ።
Even your phone may get banned❗❗
ሳታውቁ በስህተት የከፈታችሁ ካላችሁ በአስቸኳይ ይህን አድርጉ።

መጀመሪያ ፕሮፋይላችሁ ላይ ወዳለው Settings ላይ ግቡ Devices የሚለውን ንኩት። በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other Sessions የሚለውን ተጫኑና ከሁሉም አካውንታችሁ ሎግኢን ከተባለባቸው ዲቫይሶች ውጡ።  Ok በማለት 24 ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት። 24 ሰዓት ከቆዬ ይህን ማድረግ ላትችሉ ትችላላችሁ። ምክንያቱም እነርሱ ይህን ስቴፕ ተከትለው እንደ ዋና ባለቤት ሆነው እናንተን ያባርሯችኋል። 

ብዙ ሰው እየተበላ ስለሆነ ሼር it.
አሁን ማነው የ 5000 ብር የቴሌግራም ፕሪሚየም በነፃ የሚሰጣችሁ?
በአቋራጭ ለመበልፀግ አትጣደፉ።
አዩዘሀበሻ

@yeadonaimedia
@yeadonaimedia






ድንቅ አዲስ መዝሙር ነው አድምጣቹ ተባረኩበት እንዲሁም ለወዳጆቻቹ share አድርጉ ሌሎች አዲስ መዝሙሮችን ስትለቅ እንዲደርሳቹ እና በጸጋዋ ትባረኩ ዘንድ ቻናሏን subscribe አድርጉ! ብሩካን ናቹ!😍
https://youtu.be/M_eojCYRsoQ?si=7ZZhrdWgp3ll5J8n




ሶስቱ ቀደምት እና ተወዳጅ ዘማሪዎች በአንድ መድረክ በሚሊኒየም አዳራሽ በአንድ ላይ ሊያገለግሉ ቀን ተቆርጧል!

ዘማሪት ሊሊ ፣ ዘማሪት ቤተልሔም ወልዴ፣ዘማሪት አዜብ ሐይሉ በሚሊኒየም አዳራሽ በተወደዱ ዝማሬዎቻቸው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ጌታን ለማምለክ ቀን ተቆርጦ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

ይህንን ድንቅ የአምልኮ ድግስ ያዘጋጀቸው የክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን (CM Tv) ናት ስለ ዝግጅቱ በ ክርስቶስ ተልዕኮ ቤተከርስቲያን ዋና መጋቢ ተስፋሁን ሙላለም የተሰጠው ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊንኩን ከላይ ስላያያዝን መመልክት ትችላላችሁ።

መልካም ቀን!

@yeadonaimedia
@yeadonaimedia




ከ65 ዓመታት በኋላ ታሪክ ሊደገም ነው !!

አንጋፋው ወንጌላዊ #ቢሊ ግራሃም በንጉሱ ጊዜ ነው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመጀሪያ ጊዜ የጀማ ወንጌል የሰበኩት። ለዚህ ስራቸውም ከንጉሱ ዘንድ ምስጋና ተችሯቸው ነበረ።

ዛሬ በሳቸው እግር የተተካው ልጃቸው ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም፣ ታላቅ የወንጌል ድግስ አዘጋጅቷል።

“መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል፣ የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ታላቅ የወንጌል ድግስ ይካሄዳል። ከሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር በሚኖረው የአደባባይ ድግስ፣ የጸሎት፣ የወንጌል ስብከት እና የዝማሬ ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል።

ፕሮግራሙን የቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከካውንስሉ ጋር በጋራ በመሆን ነው ያዘጋጀው። በፕሮግራሙ ከሃአር ውስጥ ዘማሪዎች፣ መጋቢና ዘማሪ አገኘሁ ይደግ፣ዘማሪ አቤኔዘር፣ ዘማሪ ጉቱ እና ከውጪ ሃገራት የተጋበዙ ዘማሪዎች በመድረኩ ያገለግላሉ።

ድግሱን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያዋ የሚገኙ ክርስቲያኖች የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዚህ የጸሎት፣ የወንጌል እና የምስጋና ድግስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሬቨረንድ ፍራንክሊን የሰማሪታን ፐርስ ፕሬዝደንት ሲሆኑ፣ ተቋሙ ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተራድኦ ስራን ሲሰራ ቆይቷል።
Christian post

@yeadonaimedia
@yeadonaimedia


. እታመንሃለሁ
Meron Alemu (judy)
✅New song
💯 share 💯
@yeadonaimedia
@yeadonaimedia




#የአዶናይ_ሚዲያ_መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ አሕዛብ የሚለው ስያሜ የተሰጠው ለነ ማነው?
Опрос
  •   በክርስቶስ አምነው ላልዳኑ
  •   አይሁዳዊ ላልሆኑ ሁሉ
  •   ጣኦት ለሚያመልኩ
  •   ለሐጥያተኞች
4 голосов


እግዚአብሔርን መውደዳችን የሚታወቀው በመታዘዛችን ነው።

እሱ ያዘዘን ደግሞ እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ነው። 2ኛ የዮሐንስ መልእክት 1፥ 6 እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነውከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።

እሱን ከወደድነው እሱን ለማስደሰት ትዕዛዙን እንፈጽማለን። አጠገባችን ያለውን ወንድማችንን እየጠላን ግን እግዚአብሔርን እንወደዋለን ብንል እንዋሻለን።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፥4 አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም። 11 ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና። ሁልጊዜ በፍቅር እንድንመላለስ ጸጋው ያግዘን!

መልካም ቀን!🌄

💯 share 💯
@yeadonaimedia
@yeadonaimedia


4 ቀናት ቀሩ!
ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሽ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚል ርዕስ ከዘማሪት ሀና ተክሌ ጋር አምላካችንን ለማክበር እንገናኝ!
ይህን የአምልኮ ድግስ ያዘጋጀው ኤፔክስ ኢቨንትስ ሲሆን ብቸኛ አጋር ኤልሀዳር ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነው።
#መሥዋዕት #hannatekle #apexevent #apexventures #worship #protestant #christian #jesus #millenniumhall #christiantiktok

@yeadonaimedia


ቀን 4

የክርስቶስ መወለድ ውጤት

የክርስቶስ ልደት ደስታን፣ ድነትን እና የእግዚአብሔርን መገኘት ወደ ዓለም አመጣ።

ሉቃስ 2:10-11:- መልአኩ ለእረኞቹ የላከው መልእክት የኢየሱስን መወለድ “ለሰዎች ሁሉ የሚሆን ታላቅ የምሥራች” እንደሆነ ገልጿል።

ዮሐንስ 1፡14፡ እግዚአብሔር ሥጋ ሆነ በሰውም መካከል አደረ ክብሩንም ገልጦ ጸጋንና እውነትን አመጣ።

ገላትያ 4፡4-5
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።

የኢየሱስ መወለድ የእግዚአብሔርን እቅድ ጊዜ ፈጽሟል፣ የሰው ልጆችን ዋጅቶ የእግዚአብሔር ልጆች አድርጎናል።

👉ሉቃስ የኢየሱስ መወለድ ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ማለቂያ የሌለው የደስታ ምንጭ እንደሆነ ያነግረናል።

👉ዮሐንስ ጥልቅ ፍቅሩን እና ቁርጠኝነትን በማሳየት እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ እንዲኖር የመረጠውን አስደናቂ እውነት አጉልቶ ያሳያል።

👉የገላትያ መልዕክት በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብ እንደሆንን ፥ ባሪያዎች ሳንሆን ተወዳጅ ልጆቹ እንደሆንን አጽንዖት ሰጥቶ ይነግረናል።

👉እንደ እግዚአብሔር ልጅ ፍቅሩን ለሌሎች በማካፈል የክርስቶስን ልደት ደስታ አክብሩ። በቃል፣በድርጊት ወይም በደግነት ፍቅሩን ለአለም እናካፍል

የክርስቶስ ልደት ተስፋ፣ ፍጻሜ እና ውጤት ማጠቃለያ

ከብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ወደ አዲስ ኪዳን የክርስቶስ ልደት ፍጻሜ የተደረገውን ጉዞ ስናሰላስል፣ የእግዚአብሔር ታማኝ የመቤዠት እቅድ ወጥነት ያለው እንደሆነ እናያለን።  ገና ከመጀመሪያው፣ እግዚአብሔር ለተሰበረው ዓለም ብርሃንን፣ ሰላምን፣ ፍትህን፣ እና ድነትን የሚያመጣ አዳኝ እንደሚልክ ቃል ገባ።  እነዚህ ተስፋዎች የሚናገሩት ኢየሱስ ልደት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ባህሪውን እና ተልዕኮውንም ጭምር ነው።  በትንቢት እንደተነገረው ወደ ቤተልሔም መምጣቱ የእግዚአብሔርን ፍጹም ጊዜ እና ሉዓላዊ ፈቃድ አሳይቷል።

የክርስቶስ ልደት ደስታን፣ ድነትን እና የእግዚአብሔርን መገኘት ወደ ዓለም አምጥቷል። ከሁሉም ሁኔታዎች በላይ የሆነውን ተስፋ (ተመልሶ መምጣቱን) አብስሮናል።  ይህንን ወቅት ስናከብር፣ ኢየሱስ ለአንዳንዶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው አዳኝ መሆኑን በመገንዘብ ለፍጥረት ሁሉ ወንጌልን ለማድረስ ልንተጋ ይገባናል። ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህልእንደሆነ ከመታወቅ የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለመረዳት እና በፍቅሩ ፀንተን ለመኖር የበለጠ ህብረታችንን ከእርሱ ጋር ልናጠናክር ይገባል።

በእርሱ በኩል በፍቅሩ እና በጸጋው የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን በማወቅ በዚህ ወቅት በእግዚአብሔር ተስፋዎች እንድንታመን፣ ታማኝነቱን እንድንገነዘብ እና የክርስቶስን ልደት እውነት በህይወታችን እንድንኖር ፀጋው ይርዳን።

✍በአቢጊያ

💯 share 💯
@yeadonaimedia
@yeadonaimedia


ቀን 3

በክርስቶስ ልደት እና የተነገሩ ትንቢቶች ፍጻሜ

የኢየሱስ መወለድ የእግዚአብሔርን ተስፋዎች ፈጽሟል እናም ይመጣል የተባለው መሲሑ መሆኑን አረጋግጧል።

ማቴዎስ 1:22-23፡ የኢየሱስ በድንግልና መወለዱ የኢሳይያስ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘ ሲሆን ይህም ተስፋ የተደረገበት መሲሕ መሆኑን ያረጋግጣል።

ሉቃስ 2:4-7:- ኢየሱስ በቤተልሔም መወለዱ የሚክያስ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው ከንጉሥ ዳዊት የዘር ሐረግ ጋር የተያያዘ መሆኑን ሉቃስ ገልጿል።

ማቴዎስ 2፡1-12፡ ሰብአ ሰገል ኮከብን ተከትለው ዘኍልቍ 24፡17ን ፈፅመው ኢየሱስን ለአሕዛብ ሁሉ አዳኝ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል።

👉የእነዚህ ፍጻሜዎች ትክክለኛነት የኢየሱስ መወለድ የእግዚአብሔር መለኮታዊ እቅድ አካል መሆኑን ያረጋግጣል።

👉 በድንግልና መወለድ ኢየሱስ ፍፁም አምላክ እና ፍፁም ሰው መሆኑን፣ ልዩ በሆነ መልኩ በሰው ልጆች እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ክፍተት ለማስተካከል ብቁ መሆኑን ያሳያል።

👉 ሰብአ ሰገል ያደረጉት ጉዞ ኢየሱስ የሰዎች ዘር ወይም አስተዳደግ ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ሰዎች መዳንን እንደሚሰጥ ያሳያል።

👉እግዚአብሔር በሕይወታችሁ ውስጥ የገባቸው ተስፋዎች እንዴት ወዲያውኑ በማታዩአቸው መንገዶችም ይፈፀማሉ። እግዚአብሔር ለሰጠው ነተስፋ ቃል የታመነነ ነውና።

የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤”
  — ዕብራውያን 10፥23

👉እኛም ከእኛ የተለዩ ለሆኑት ፍቅር እና ደግነት በማሳየት የክርስቶስን ልደት ዓለም አቀፋዊ መልእክት ለአለም እናዳርስ።

✍በአቢጊያ

💯 share 💯
@yeadonaimedia
@yeadonaimedia

Показано 20 последних публикаций.