💎ጉዞ ወደ ኒቃብ💎
ክፍል 6 ...
የዘንድሮው የ2ተኛ ዓመት ፕሮግራም አሪፍ እየሄደ ወደ 4……5 ወራቶችን እያስቆጠረ ነው። ግን በዚህ ዓመት ኒቃቢስትና ጂልባቢስቶች መኖራቸው ለኮሌጁ እረፍት የሠጠው አይመስለም። ለነገሩ ምኑ ይገርማል ስንት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው ሰላት ሰግደሀል/ሻል፤ሂጃብ ለብሰሻል፤ሡሪ አሳጥረሀል እየተባለ ከትምህርታቸው ሚስተጓጎሉት ስንቶቹ ናቸው!? በዚህም ኮሌጅ የምሠማው ጥሩ አነበረም። በባለፈው ክፍል የኮሌጁ ምክትል ዲን ሙስሊም እንደሆነ ገልጬ ነበር እናም ለምን እንደሚከለክል እንደ ምክንያት የሚያስቀምጠው "እኔ ሙስሊም ስለሆንኩ ስፈቅድ ሲያዩ ለራስህ እምነት አደላህ ይሉኛል" ነበር። ግን ይሄ አሳማኝ ምክንያት አይደለም ሙስሊሞች በተለያዩ ተቋማት ላይ ቦታዎችን ይዘው ሳለ ዲኑን ባላቸው አቅም ካነሰሩ ማን ሊሰራ ነው ታድያ?
በዚህ ዓመት ብዙውን የት/ት ጊዜያችን የምናሳልፈው በተግባር(practis) ነበር። አምና እኔ የገባሁበት ፊልድ ለትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ እንደመሆኑ እንዲሁም በነበረው ሁኔታ የራሡ የተግባር ማሠልጠኛ ቦታ አነበረውም ለዚያም ለተግባር ወደ ሌላ ቦታ እየሄድን ነበር የምንማረው ይህም ነበር በብዛት ከኮሌጁ አስተዳደሮች ጋ እንዳልገናኝ የረዳኝ ። አሁን ግን በአዲሡ አመት ቦታውን ከፍቶ አስመርቋል አዲስም ስለሆነ የኮሌጁ መምህራንና ዲን እየመጡ ይጎበኙታል። በዚህ መሀልም በአንዱ ቀን ዋናው ዲን ወደዚህ ቦታ ሲመጣ ያየኛል ከዚያ ከአስተማሪዬ ጋር ያስጠራኝና
"ተማሪ ነሽ?"
"አዎን"አልኩት
ስሜንም ጠየቀኝ ነገርኩት።
ወደ አስተማሪዬ በመዞር
"ስንተኛ አመት ተማሪ ናት?"
እሡም 2 አለው።
እንዴት ይህን ለብሳ ትማራለች አምና እኮ ለዲኑ (ለሙስሊሙ) ነገሬው ነበር ለምን ዝም አላት ለማንኛውም ይህን ለብሰሽ እንዳትመጪ ከፈለክሽ ( አጠገቤ ታዝባ የምታየውን ሙስሊም እህቴን እየጠቆመ) ሻርፕ አድርገሽ ነይ ብሎ ሄደ።
በነገራችን ላይ አስተማሪዎቼ እግሬ እዛ ከረገጠበት ቀን አንስቶ ምንድነው የለበሽው ለምን ይህን ለብሠሽ ተማርሽ ወላሂ አንድም ቀን ጠይቀውኝ አያውቁም አሁንም ቢሆን ምንም እነሡ አይመስላቸውም።
እኔን ግን ያልገባኝ የአስተዳደሮቹ እንዲህ መሆን ነው ዛቻቸውም በዚህ አልበቃም ጨርሠን ስወጣ ደግሞ በተራው ጥበቃው ጠራኝና"የዚህ ት/ቤት ተማሪ ነሽ አለኝ አው ስለው ከዚህ በኋላ ግን በዚህ ከመጣሽ አትገቢም አለኝ።
"ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ" አለ ያገሬ ሠው።
ዝም ብዬው ወጣው በሠዐቱ ራሡ አጠገቤ ሙስሊም ያልሆነች ልጅ ነበረች እንዴት ልታደርጊ ነው ስትል ጠየቀችኝ " ትምህርቱ እንደሆነ ጥንቅር ብሎ ይቀራታል ማውለቄ ሲያምራቸው አይታሠብም " ብያት ጉዟችንን ቀጠልን።
ይቺ ቀን እዛ ኮሌጅ ከተማርኩባቸው ቀናቶች ሁሉ የተለየች ናት እንግዲህ ዲኑ ለጥበቃው አታስገባት ብሎት መሆኑ ነው ሥል አሰብኩኝ………
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል…