ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌ ዎች
ክፍል 5️⃣
ከባለፈው የቀጠለ……
15 | P a g e
6. ዝሙተኛ ሴትን ከዝሙቷ እስክትቶብት ድረስ ማግባት አይፈቀድም ዝሙተኛ ወንድንም እንደዚሁ
ከዝሙቱ እስኪቶብት ድረስ ልታገባው አይፈቀድላትም። አላህ (سبحانه وتعالى (እንዲህ ይላል
الزَّانِي لَا يَنكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوْ مُشْرِكَةً وَالزَّانِيَةُ لَا يَنكِحُهَا إِلَّا زَانٍ أَوْ مُشْرِكٌ ۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ
[ ሱረት አል-ኑር፣ - 3 ]
{ዝሙተኛው ዝሙተኛይቱን ወይም አጋሪይቱን እንጂ አያገባም፡፡ ዝሙተኛይቱንም ዝሙተኛ ወይም አጋሪ
እንጂ አያገባትም፡፡ ይህም በምእምናን ላይ ተከልክሏል፡፡}
36
በዚህ አንቀጽ ላይ በግልጽ እንደምንመለከተው ይህ (ዝሙተኛን ማግባት) በምእመናኖች ላይ እርም
እንደተደረገ ተነግሯል
ባሪያን ስለማግባት ያለን ብይን ያላመጣሁት በዚህ ዘመን ላይ እምብዛም ባሪያዎች ስለሌሉ ጽሁፎች
እንዳይበዙ በማሰብ ነው።
እነዚህ የተዘረዘሩት ሰባቱ ደግሞ የተከለከባቸው ሰበቦች እስካልተወገዱ ድረስ ሊያገባቸው ማይችላቸው አካላት
ናቸው። እነዚህ ግን አጅነብይ ይሆናሉ ምክንያቱም የተከለከለበት ሰበብ ሲወገድ ሊያገባቸው ይፈቀዱለታልና ነው።
ለአንድ ወንድ አጅነብይ ማይሆኑት መቼም ቢሆን ሊያገባቸው ማይችላቸው ሴቶች ናቸው።በመሆኑም የሚስት እህት
አጅነብይ ናት ለእህቷ ባል ሂጃቧን መገለጥም ይሁን እሱን መጨበጥ አይፈቀድላትም። ልክ ለባሏ ወንድም
መገለጥም ይሁን እሱን መጨበጥ እንደማይፈቀድላት ሁሉ።
1.6 ክርስቲያን ና አይሁድ ሴቶችን ስለማግባት
ቁርአን አህለል ኪታብ(መጽሀፍ የተሰጡት) የሆኑ ሴቶችን ስለማግባት በሱረተል ማኢዳ ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል
الْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ الطَّيِّبَاتُ ۖ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَّهُمْ ۖ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ ۗ
{ ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ
ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች
ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን
በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡}
37
አህለል ኪታብ (መጸሀፍ የተሰጡት) የሚባሉት ደግሞ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ናቸው።
ከቁርአን አንቀጹ ጉልህ መልእክት የምንረዳው ቁም ነገር ከመኖሩ ጋር በጉዳዩ ላይ አንዳንድ መብራራት አለባቸው ብዬ
ማስባቸው ነጥቦች ስላሉ የተወሰነ ላብራራው ወደድኩ። በመሆኑም ኡለሞች በሚጠቅሷቸው ዝርዝር ነጥቦች ላይ
ተንተርሼ ለማብራራት እንዲቀለኝ በማሰብ ርእሱን ለሁለት ከፈልኩት እነሱም
1. በሙስሊም ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማግባት
2. በካፊር ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማማግባት
ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻__________________
36 አኑር 3
37 ማኢዳ 5
____.
@yenebiyattaric @yenebiyattaric