𝐎𝐅𝐅𝐈𝐂𝐈𝐀𝐋: (ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሚገኘው ፖቶማክ ወንዝ 64 ሰዎችን የጫነ ንብረትነቱ የአሜሪካ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን እና 3 ወታደሮችን የጫነ የጦር ሂሊኮፕተር መጋጨታቸውን ተከትሎ በተፈጠረው አደጋ ዙሪያ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለአደጋው ሙሉ በሙሉ ገለጻ እንደተደረገላቸው ምሽቱን በሰጡት መግለጫ ገለጹ። "እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር" ሲሉ የጀመሩት ትራምፕ "በመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎቻችን እየሰሩት ላለው አስደናቂ ስራ እናመሰግናለን፣ ሁኔታውን እየተከታተልኩ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እሰጣለሁ" ብለዋል።
ትራምፕ የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነም ጥያቄ አንስተው "ይህ መፈጠር ያልነበረበት መጥፎ ሁኔታ ነው... ጥሩ አይደለም!!!" ብለዋል።
የአደጋው መንስኤ በትክክል ምን እንደሆነ ተጣርቶ በሚመለከታቸው ባለስልጣናት ይነገራል። እስካሁን ነፍስ ለማዳን እየተደረገ ባለው ጥረትም የ18 ሰዎች አስከሬን እንደተገኘ ከዚህ ቀደም ባቀረብነው መረጃ ላይ መግለጻችን ይታወሳል።