👇④ ✍✍✍ …አዳምን የሚያጠቃልል ነው። ከዚህ ተነሥተን ስናየው ድንግል ማርያም የመላእክትም ቤዛቸው ናት!ምነው እነርሱማ ምን በድለው ተቤዠቻቸው? የሚል ቢኖር መልሱን እስክንነግረው ይታገሥ።
"…ከወደቁት በቀር እውነት ነው መላእክት ምንም ነውር የለባቸውም። ነገር ግን ቤዛነት ለበደል ብቻ ሳይሆን ለአንድ አካል ያልተቻለውን ነገር በዚያ ተገብቶ ሲፈጽምለት ቤዛነት ይባላል። ስለዚህ ኃይላተ ሰማያት እግዚአብሔርን አብረውት እየኖሩ ድምጹን እየሰሙ አያዩትም። እንዲያውም ስንኳንስ ሊያዩት ምኞታቸው እርሱን ማሰባቸው ራሱ የማይሻገሩት ሞገድ ይሆንባቸዋል። በሁከት መንፈሳዊ እየዋኙ በኅሊና ርቀት እየመጠቁ ሲያስቡት ከመታሰብ በላይ ይሆንባቸዋል። በመሠረተ ዓለም ይመረምሩታል ይጠልቅባቸዋል፤ በጠፈረ ሰማይ ይሹታል ይመጥቅባቸዋል፤ በክበበ ዓለም ይፈልጉታል ይሰፋባቸዋል፤ በውሳጤ ዓለም ይመኙታል ይሰወርባቸዋል፤ በኅሊና መንፈሳዊት ያስቡታል ይረቅባቸዋል። ስለዚህ ይህን ሁሉ አለመመርመሩን ፊታቸውን፣ እግራቸውን በመሸፈን ረበው በመታየት ይገልጡታል።(ሕዝ ፮፥፩-፰)
"…እንዲህ ሆነው መታየቱ ስንኳንስ መታየቱ መታሰቡ ግሩም ነውና ሲሉ ነው። አሳባቸውንስ እንኳን ባለመመርመር ያሸንፈዋልና "አኀዜ ኪሩቤል-ኪሩቤልን የያዘ" ብሎታል ቅዱስ ሄሬኔዎስ ሐዋርያዊ፡፡ ኪሩቤልን የሚይዝ ማለት ምሉዓነ አዕምሮ የሆኑትን እንኳ መዋዕየ ሕሊና ነው ሲል ነው። አባ ሕርያቆስም" ኀበ ኢይበጽሖ ሕሊና ሰብእ ወኢዘመላእክት አዕምሮ-መለኮትስ የሰዎች ሕሊና የመላእክት እውቀት የማይደርስበት በልዕልና ያለ ግሩም ድንቅ ነው" ሲል አመስጥሮታል። ማየት ቢሳናቸውም ማየት መፈለጋቸውን ግን አላቆሙም። ስንኳንስ የማይበሉት የማይጠጡት መላእክት የሚበሉት የሚጠጡት የሰው ልጆችም የሚጠግቡት እግዚአብሔርን በማየት ነውና። መዝ 11፥11 ይህን ግን አነርሱ ማድረግ አልቻሉም። ስለዚህ ይህን ያሚያደርግላቸው አካል የማያዩትን ጌታ እንዲያዩት የሚያበቃቸው ቤዛቸው ነው ማለት ነው። እንግዲያውስ ይህን ያደረገችው ድንግል ማርያም ብቻ ናትና ለእነርሱ ቤዛቸው ናት ማለት ነው። የእነርሱ ዐይን ሊያየው ያልደፈረውን የእርስዋ ሕዋሳት ግን ታቅፈው አጥብተው አሳድገውታልና። ይህንን ቅዱስ ጳውሎስ "ወአስተርአየ ለመላእክት-ለመላእክት የታየ" ሲል ገልጦታል። (፩ ጢሞ ፫፥፲፮) የታየ ማለት ቀድሞ አይታይም ነበር ማለት ነው።
"…ቅዱስ ያሬድም ምስጢሩን በዜማ" ዘመላእክት ይትሜነዩ ርእዮቶ፣ በላዕለ ማይ ዘጠፈረ ቤቶ፣ተወልደ እምድንግል ያርኢ ኂሩቶ፣ ለዘከመዝ ንጉሥ ነአምን ልደቶ- መላእክት ያዩት ዘንድ የሚመኙት ፥አዳራሹን በውኃ የሠራ፥ቸርነቱን ይገልጥ ዘንድ ከድንግል ተወለደ፥ እንዲህ ያለውን የዘለዓለም ንጉሥ የክርስቶስን ልደት እናምናለን" ሲል አንቆርቁሮታል።( ድጓ ዘአስተርእዮ ዘእግዝእትነ) ይህር ርኀብ ያጠገበቻቸው ይህንን ጥም ያረካቻቸው ድንግል ማርያም በእውነት የመላእክትም ቤዛቸው ናት!
"…ለእኛስ? አብሶ ለእኛማ እንዴታ! የመጀመሪያው ቤዛነቷ ንጽሕናዋ ነው። አሁን ልብ እንበል ክቡር እንግዳ ሲመጣ ክቡር ቤት ያሻዋል። ትልቁ እንግድነት ደግሞ ክርስቶስ ወደ እኛ ባሕርይ የመጣበት ሥጋዌ ነው። ሰማይን ለዘረጋው ምን ዓይነት አዳራሽ ሠርተን እናስተናግደዋለን? ዓለምን በእጁ ለያዘ በምን ጎጆ እንወስነወለን? ብርሃንን ለተጎናጸፈው ምን ዓይነት መጋረጃ እንጋርድለታለን? ምድርን በውኃ ላጸና ምን ዓይነት ምንጣፍ ጉዝጓዝ እናደርግለታለን? ምዑዘ ባሕርይውን ምን አይነት ሽቱ እናጣፍጥለታለን? ትንኝን በምግብ ለማይዘነጋት ምን እንደግስለታለን? ምንም!
እንግዲያው በምን ተቀበልነው? ነውር ነቀፋ የሌለባት ቅድስናን የተጎዘጎዘች፥ ንጽሕና የተደራረባት፥ ምዕዝተ ምግባር ወአሚን፥ ጥዕምተ ስም ወቃል፥ ከከዋክብት የደመቀች፥ ከፀሐይ ያበራች፥ ከሰንፔር የጠራች፥ እንደ ጨረቃ ብርሃኗ ያልጎደለች ይልቁንም ጸጋን የተመላች፥ ጽርሕ ንጽሕት ድንግል ማርያም ተገኘችልን።
"…እግዚአብሔርን ያስተናገድንባት ንጽሕት አዳራሽ ድንግል ማርያም! የሁላችን ቤት ጉድፍ ነበርና ጽድልት በሆነችው አዳራሽ ተቀበልነው። የሁላችን ቤት መርገም መልቶት ነበርና ቡርክት ቤት እርሷን አገኘን፥ የሁላችን ቤት ምንም አልነበረውምና ጸጋን በተመላችው ቤት አሳደርነው። ሁላችን ደካሞች ነበርንና ቤታችን አቅም አልነበረውም፥ ስለዚህም ኃይለ ልዑል ባጸናት ጽንዕት ቤት ኀይል እርሱን ተቀበልነው። ይህንን ነው ሊቁ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ "በፈቃደ አቡሁ ወረደ፥ ኀበ ማርያም ተአንገደ፥ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ- በአባቱ ፈቃድ ወረደ፥ በድንግል ማርያም ተስተናገደ፥ በንጹሕ ድንግልናዋ እግዚአብሔር ተወለደ" ሲል የዘመረው።
"…እግዚአብሔር ያዳነን ሰው ሁኖ ነው። ሰው ለመሆን ደግሞ ከአውሬ ወይም ከእንስሳ ወይም ከመላእክት ሥጋ አላመጣም። ምክንያቱም የፈለገው ሰው መሆን ነውና፡፡(ዕብ፪፥፲፬-፲፯) ሰው ማለት ደግሞ ቀድሞ ዓርብ የተፈጠረው ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈበት በአርአያ ሥላሴ የከበረው ፍጥረት መጠሪያ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ሰው ለመባል የሚበቃው አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረውን የተስማማ ባሕርይ ሲይዝ ነው ማለት ነው። ጌታ ሰው ይሆን ዘንድ በመጣበት ወራት ደግሞ ሁላችንም ሙሉ ሰው መሆናችን ቀርቶ "ሰውስ ክቡር ሲሆን አላወቀም ልብ እንደሌላቸው እንስሳት ሆነ "የተባልንበት አርአያ ሥላሴ ተሰጥቶን የነበርነው ደብዝዘን በእንስሳት የተመሰልንበት፤ ውሉደ ብርሃን የነበርን"በጨለማ የሚኖር ሕዝብ "የተባልንበት የእዳ ዘመን ነው። በዚህ ጊዜ ከአብራከ አዳም ከማኅፀነ ሔዋን ስታበራ የነበረች ነጭ ዕንቁ ድንግል ማርያም ተገኘችልን። የቀድሞውን ንጹሕ ጠባይዐ ፍጥረቱ ለአዳም የተስማማ የቀድሞውን የአዳምን ንጹሕ ባሕርይ ይዛ ተገኘች። እግዚአብሔርም ሰውን ለማዳን ሲያስብ ሰው መሆን ሽቷልና ሰው ስለተገኘችለት ወደ እርስዋ መጣ። ድንቅ በሚያሰኝ በማይመሰመር ተዋሕዶም ሰው ሆነ።" ፈቂዶ ይፈውስ ትዝምደ ሰብእ ተገምረ በማኅፀነ ድንግል ተኀቢኦ ለኩሉ ኀይል እለ በሰማያት ማኅደር-ባሕርየ ሰብእን ነገደ ሰብእን ሊያድን ሽቶ ከሰማይ ሠራዊት ተሰውሮ በድንግል ማኀፀን ተወሰነ" እንዳለ መጽሐፈ ኪዳን። ስለዚህ የሰው ወገንን ሁሉ ወክላ እግዚአብሔርን ሰው ያደረገችው ናትና በእውነት ቤዛዊተ ዓለም በእውነት ሰው የመሆናችን መመኪያ የሰው ዘር ወላዲተ አምላክ!
"…ሔዋን ላፈረሰችው ድንግልና በድንግልናዋ ካሰችልን። አጋንንትን ለሰማችበት ጆሮዋ ስብሐተ መላእክትን ሰምታ ካሰችልን። በሲኦል እንኖር ዘንድ የነበርነውን በመቅደስ ኑራ ወደ መቅደስ መለሰችን። ስደተኞች የነበርነውን በስደቷ ወደ ርስት መለሰችን፥ ረኀብተኞች የነበርነውን በረሃብ በጭንቅ ተሰዳ ልጇን መገበችን፤ በጨለማ የነበርነውን በሌሊት ቁር ከአውሬ ጋር በስደት ኑራ በልጇ ብርሃን አበራችልን። በሐሩረ ጌጋይ እንቃጠል የነበርነውን በሐሩር እየጠወለገች ተሰዳ ጠለ ምሕረት ልጇን ሰጠችን። ሁከተ አጋንንትን እንሰማ የነበርን የአይሁድን ጩኸት ስትስማ ኑራ የስብሐተ መላእክት እድምተኞች አደረገችን። በሞት ፍርሐት በርደተ ገሃነም እንርድ የነበርን በልጇ ሞት ስትደነግጥ ኑራ ሠላምን ሰጠችን፣ የአለቀሰችው እንባ የደረሰባት ባሕረ ኀዘን መስጠሜ አበሳ ሆነን። አይይ! ዘመኔም እውቀቴም ያጠረ እኔ የእርስዋን ስቃይ እዘረዝር ዘንድ ወዴት ተችሎኝ!
"…ዛሬ ደግሞ በገነት ያሉትን ነፍሳት ልጇ በመላእክት ካስጎበኛት በኋላ በዚህ ስትደሰት ደግሞ ሲዖል ውስጥ የሚጋዩትን አሳያት። ጌታም ይህን ማሳየቱ…👇④✍✍✍