Zemedkun Bekele (ዘመዴ)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ሐሙስ፦ አዳም ሐሙስ ይባላል፦

"…ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በአምስተኛው ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን ከትንሣኤው ጋር ተያይዞ ታስበው ይውሉ ዘንድ አዳም ወር በገባ በ6 ከኢየሱስ እና ከእነ ቅድስት አርሴማ ጋር አብሮ የሚከበር የወርሀዊ በዓል ሥርዓት የተሠራለት ቢሆንም የዛሬው ግን አባታችን አዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በሜዳህ ድኼ፣ በእንጨት ላይ ተሰቅዬ ከ5 ቀን ተኩል በኋላ አድንህሃለሁ ተብሎ የተሰጠው ተስፋና የተገባለት ቃል ኪዳን ተፈጽሞ አዳምና ልጆቹ ነጻ የወጣበትን አስበን የምንውልበት ዕለት ነው።

"…አባታችን አዳም በሦስት ነገር ወደቀ። በተዋሕዶ፣ በመብልና በእጽ ምክንያት ወደቀ። ሰይጣን ከቆንጆዋ እባብ ተዋሕዶ፣ እባብን መስሎ፣ እባብንም አሕሎ አዳምና ሔዋንን ሰብኮ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዳትበሉት፣ የበላችሁ ቀን የሞት ሞትን ትሞታላችሁ ብሎ የከለከላቸውን ዕጽ በልተው ሞቱ። በዚህ ምክንያት የሞቱትን አዳምና ሔዋንን ለማዳን እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ምድር መጣ።

"…ሰይጣን በእባብ ገላ ተዋሕዶ እንዳዋረደው፣ ጌታም ከአዳም የልጅ ልጅ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጦ አዳነው። አዳም በዕፅ ምክንያት እንደ ሞተ የሚያውቅ ጌታም በዕለተ አርብ በ17 ክንድ ዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ አዳነው። በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳም "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ… ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐ፥ 6፥ 54-56 በማለት በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳምን የራሱን ሥጋና ደም መብልና መጠት አድርጎ አደነው።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።

3.5k 0 6 147 169

መልካም…

"…አሁን ደግሞ 12ሺ ሰው አንብቦት 3 ፍሬ ሰዎች ብቻ ጓ 😡 ብው ወዳሉበት ወደዛሬው ርእሰ አንቀጻችን በእናንተ ወደማስተቸቱ እንገባለን። ከድሮው አንጻር ሲታይ አሁን አሁን ጓ😡 ብው የሚልብኝም ሰው እየቀነሰ መጥቶ በጣም ስጋት ላይ ወድቄአለሁ። ብዙዎች የተነፈሱ ይመስለኛል። ሃቅን መጋፈጥ አልቻሉም። እናም ጓ 😡 ብው የምትሉ ሰዎች ከፔጄ ባትጠፉ ዴየስስ ይለኛል።

"…ሌላው በአባ ደጀኔ ቶላ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል አጀንዳ እንድታጠር የፈለጉ ቅባቴና መኔዎችንም አይቻለሁ። "አንተ የሚያምርብህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው። እነ ሄኖክ ኃይሌ እንኳን ኃይለቃል መናገር ጀመሩ እኮ። መምህር ዘበነም ጓ ብሏል። ሲኖዶሱም ውይይት ጀምሯል እናም ዘመዴ እሱላይ ብትሠራ ያሉኝ አዛኝ ቅቤ አንጓቾችም ገጥመውኛል። እኔ ግን አልኳቸው እንኳን ይሄ ሁሉ ሊቅ ታክሎበት ለእመቤታችን ራሷ አታንስም። እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻዬን የምጮህበት ዘመን አልፏል። ሞኝህን ፈልግ ብያአቸዋለሁ። አሁን የእኔ ትኩረት ጎጃም ነው። ጮቄ ተራራ።

"…እኔ ዘመዴ ከጎጃም አልወጣም። ከጮቄም አልወርድም። የነገውን ርእሰ አንቀጽ እስክጽፍላችሁ ድረስ የዛሬውን እንዴት አያችሁት? ደፈር ብላችሁ ምከሩ፣ ተነጋገሩ፣ ተከራከሩ።

• ተንፒሱ…ጻፉ…✍✍✍

30.1k 1 14 310 1k

👆③✍✍✍ …የዘር ማጥፋት የሚጠቅማትን ፕሮፓጋንዳ ሠራላቸው። ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ቴሌቭዥኑ ሁሉ አሥረስ መዓረይ ሆነ። የጀግና ዐማራ ፋኖ በጎጃም ጀግኖችም በድሮንና በስናይፐር መርገፍ፣ መውደቃቸውን ቀጠሉ።

"…ይሄን ጊዜ ነው እኔ ጎጃም መግባቴን ያወጅኩት። ጎጃም መግባቴን እንደሰማ በመጀመሪያ ከተደጋጋሚ የስልክ ቅጥቀጣ በኋላ አላነሣውም ያልኩትን የአስረስ መዓረይን የሥልክ ጥሪ አንሥቼ ማነጋገር ጀመርኩ። እሱ ጠበቃ ስለሆነ አመጣጡ እኔን ቅርጽ ሊያሲዘኝ ነበር። በፍርድ ቤት የለመደውን እኔ ላይ ለመተግበር ነበር አመጣጡ። አስረስ ብልህ ነው። ሲጀምር እንኳ ያለኝ "ዘመዴ አንተ ግን ዋጋህን ታውቀዋለህ? አንዳንድ ሰዎች ዋጋቸውን አያውቁም። አንተ ማለት ቀላል ሰው አይደለህም። መሬት ላይ እኮ ገበሬው ሳይቀር ዘመዴ ምን አለ ነው የሚለው። እናም ዋጋህ ውድ ነው ነበር ያለኝ። አሁንም ደጋግሜ ስሰማው ይገርመኛል። አላልኩም ካለ አስረስ ይናገርና እኔ ልፈርበት። ሌሎቻችሁ በማታውቁት አትዘባርቁ። ውሸት ማለት ያለበት ባለቤቱ ነው። የመጀመሪያው ቀን የስልክ ውይይታችን በመግባባት ነበር የተቋጨው።

• አስረስ፦ ሃሎ መምህር ዘመድኩን እንደምን አለህ። እንኳን ወደ ጎጃም ምድር ለጉብኝት መጣህ። እንደው በጾሙ ባይሆን መልካም ነበር…

~ዘመድኩን፦ ሃሎ ጠበቃ አስረስ እንዴት ነህ?

• አስረስ፦ እንዴ እንዴት ስልኬን ልታውቅ ቻልክ? ተደዋውለን እኮ አናውቅም።

~ ዘመድኩን፦ አዎ እርግጥ ነው ተደዋውለን አናውቅም። ነገር ግን እኮ ከአለቃህ መልእክት እየተቀበልክ የምታደርሰኝ በዚሁ ስልክ ነበር። እኔ ለአንተ አልመልስልህ እንጂ ስልክህንማ ሴቭ አድርጌ እኮ ይዤዋለሁ።

• አስረስ፦ በፍጹም እኔ ጽፌልህ ዐላውቅም።

~ ዘመድኩን፦ ቆይ ጠብቀኝማ። ስክሪንኮፒ አድርጌ ላኩለት።

• አስረስ፦ ኦ ያያ ልክ ነህ፣ ይሄኛው ያኛው ስልኬ ነው። ረስቼው ነው። ይቅርታ።

~ ዘመድኩን፦ ምንም አይደል።

"…እንዲህ ነው የተጀመረው የእኔና የአስረስ ግኑኝነት። እኔም ከመጣህማ ማርያም ታምጣህ ለመጠየቅ፣ ለመመርመር ፈቃደኛ ነህ? አልኩት። አዎ አለኝ። አስረስን በፈቃዱ መረመርኩት፣ ጠየቅኩት። ቃሉን ተቀበልኩት። 9 ጥያቄ ሲቀረኝ ደንብሮ፣ ደንግጦ ጠፋ። አላስተረፍኩትም። በውስጤ ያለውን ሁላ ነው የጠየቅኩት። ሴራውን ሁላ ነው ያስለፈለፍኩት። አንድነቱ በጎጃሞች እንደዘገየ የነገረኝ፣ ያመነልኝ ራሱ አስረስ መዓረይ ነው። እነ ዝናቡ ናቸው ወታደራዊ አዛዥነቱም ለጎጃም መሰጠት አለበት ብለው ትንሽ ያስቸገሩን እንጂ ሠራዊቱ ራሱ መውጫ መግቢያ ነው ያሳጣን ያለኝ ራሱ አስረስ መዓረይ ነው። እኔ ዘመነ ካሤ እስከተመረጠ ድረስ ዘመነ ስለማይተወኝ፣ ስለማይከዳኝ ችግር የለብኝም ብሎ በቃሉ የነገረኝ ራሱ አስረስ ነው። ውይይታችንን ደጋግሜ ሳዳምጠው አሁንም ድረስ እገረምበታለሁ። እኔ ከሰው ሰምቼ አይደለም። በይሆናልም አይደለም የምጽፈው። እኔ ከፈረሱ አፍ የሰማሁትን፣ በመረጃና በማስረጃ የያዝኩትን ነው የማወራው። ግርማ አየለንና አልማዝ ባለጭራዋን "እነሱን ሰው አድርገህ፣ ከሰው ቆጥረህ" ያለኝ አስረስ ራሱ ነው። የእኔን የዘመዴን ዋጋም ውድነት በአፉ የገለጸልኝ አስረስ መዓረይ ነው። መጀመሪያ ክዶኝ ኋላ ላይ የነገረኝ ማርሸት ነው ስለው ትንፋሽ አጥሮት ሲንተባተብ ብትሰሙት ትደነቃላችሁ። የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ባወቀ አስረስን ከቤቴ አምጥቶ በቤቴ ያስለፈለፈውም ራሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው ብዬ ነው የማምነው።

"…አሁን የተያዘው ሴራ አክራሪ የዐማራ ብሔርተኛ እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፍጹም አማኝ የሆኑ የጎጃም ጀግኖችን ማስወገድ ነው በጎጃም የተያያዙት። ለምሳሌ በቀደም በድሮን ገደብ ላይ የተፈጁትና ያለቁት በሙሉ ምርጥ ምርጥ የዐማራ ታጋይ የጎጃም ፋኖዎች ናቸው። በየትኛውም የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የማይጠፉት እነ አስረስ መዓረይ፣ እነ እሸቱ፣ እነ ማርሸት በዚያ የኮማንዶ ምረቃ ላይ አልተገኙም። ሠልጣኞቹም ከመዋቅር ውጪ ነው የሠለጠኑት። የሥልጠናውም በጀት ከዐማራ ፋኖ በጎጃም የፋይናንስ ቋት የተገኘም አይደለም። አንድ ባለሀብት ነው ገንዘቡን የሰጠው። የብርጌዱ መሪ እና ኋላ እሱም ከጀርባ እንደተመታ የሚነገረለት ሻለቃ መንበሩ ጌታዬም ይሄን አካሄድ በጽኑ መቃወሙን ነው አሁን ጮቄ ላይ ሆኜ እየሰማሁ ያለሁት። በድሮን የተጨፈጨፉትን ከጭፍጨፋው በፊት በአካባቢው ድሮን እየታየች ነውና ልጆቹ ይበተኑ እያሉ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የቴሌግራም አክቲቪስቶች አብዝተው ቢጮሁም ምላሽ አላገኙም። ኋላ ላይ ግን ልጆቹ ጭዳ ከሆኑ በኋላ የአዞ እንባ "ጅግና ይሞታል፣ ትግል ይቀጥላል" ብላ ብላ ዲስኩር ከጫካ ውስጥ ተሁኖ ተለፈፈ። ይሄ ልክ አይደለም።

"…አሁን በጎጃም የዐማራ ፋኖ በጎጃም ትልቅ ፈተና ውስጥ ነው ያሚገኘው። የዐማራ ፋኖ አንድነት ይመጣል ተብሎ የሚለፈፈውም በእነዚሁ የዐማራ ፋኖ በጎጃምን እግር ተወርች አስረው ቀፍድደው በያዙት አካላት አማካኝነት ነው። ማርሸት ፀሐዩ በቃል አቀባይነቱ ዕድል አግኝቶ በቅርቡ የምሥራች ጠብቁ የሚለውም ፍጹም ውሸት ነው። እነ አስረስ እያሉ የዐማራ ፋኖ አንድነት የማይታሰብ ነው። ሞጣ እንኳ በአንድ ቪድዮው ላይ አስረስን ሲያስቀር ዘመነን ጨምሮ በሙሉ ፋኖዎችን ባንዳ የሚል ማዕረግ ሰጥቶ ሲያከናንብ ነበር የሰማሁት። ሞጣ የምሥራቅ ጎጃም ፀረ ኦርቶዶክስ መናፍቅ ቅባቴ ነው። በሴራው በምሥራቅ ጎጃም የሚገኙ የተዋሕዶ ጀግኖችንም እየተቀረጠፉ ነው። ማርሸት ፀሐዩ ከግንባሩ ገንዘብ ያዥ ከወሮ ሕይወት ጋር በስልክ ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ በግልጽ የነገራት "ዐማራ ጄኖሳይድ ተፈጸመበት የሚባለው ውሸት ነው። ጭፍጨፋው የዓለም አቀፍ የጄኖሳይድ መመዘኛን አያሟላም" ብሎ የተሟገተ የዐማራ ነፃ አውጪ ፋኖ ቃልአቀባይ ነው። ድሮኗ እነሱን አትነካም። የጎጃም ዐማራ ጀግኖች ግን ተራ በተራ እየተለቀሙ ነው። ጎጃም ጥቁር ከል እየለበሰች ነው። የጀግና መፍለቂያ ሀገር በአመራር ቅሽምና እመቀእመቃት እየወረዱ ነው። ፉከራ፣ ቀረርቶ፣ ሽለላ ብቻውን ለጎጃም ዐማራ ረብ አያመጣለትም። በጎጃም ዶክተሮች በተጠና መልኩ አየተረሸኑ ነው። እየተሰደዱም ነው። መምሕራን እየተጨፈጨፉም፣ እየተሰደዱም ነው። ደንቆሮ፣ ማይም፣ ያልተማረ ትውልድ ጎጃም ላይእንዲበቅል እየተደረገ ነው። ነጋዴና ንግድ ቀዝቅዟል። ያልተማረ ማይም ትውልድ ደግሞ ባርያ ከመሆን የዘለለ ስፍራ አያገኝም። ይሄ ሲነገር ለመፍትሄው ከመራወጥ ይልቅ ለምን ተተቸን እያለ የሚያለቃቅሰው፣ የሚነስረው፣ የሚያንዘረዝረውን መንጋ ማየቱም ያሳቅቃል። ያሳቅቃልም። በጣም ነው የሚያሳፍረው። ቤተሰብህ፣ ትውልድህ በሴራ እያለቀ ነውና መፍትሄ ፈልግ ስትለው ለምን በአደባባይ ተነገረኝ ብሎ ኮሬንቲ ካልጨበጥኩ ብሎ የሚፎገላውን ሳስብ እደመማለሁ። ኩራት እራት አይሆንም እኮ።

"…እና ዘመዴ አሁን የዐማራ ፋኖ አንድነት በቅርቡ የለም ነው የምትለን? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም። እኔም ምላሼን ይዤ በነገው ርእሰ አንቀጼ ከች እላለሁ። እስከዚያው በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ዙሪያ እየተወያየን እንቆያለን።

• ዘመዴ ሚዲያ መጥቷል። አየር ላይም ውሏል።

• የባንዳና የሾተላይ መርዝ ይሽራል።
• የባንዳና የሾተላይ እሾህም ይነቀላል።
• የዐማራ ፋኖ በጎጃምም ከሕመሙ ይፈወሳል።
• ዐማራም እንደ ሕዝብ ድል ያደርጋል።

~ይደፈርሳል…ግን ደግሞ ይጠራል…✊

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሚያዝያ 15/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።


👆②✍✍✍ …ቡድን ነው። የጎጃሙ ግን ይለያል። ከዶክተር ሙሴ ጀምሮ አሁንም ከጎጃም ውጪ ወደ ውጪ የሚሉ አካላት ትግሉን ተቆጣጥረው ይዘውታል። ፋይናንስ ደግሞ ዘጭ ነው። እናም የጎጃሙ ከበድ የሚለው ለዚህ ነው።

"…ለዚህ ፕሮጀክት ሲባል ከ30 ዓመት በላይ ከታች ከ1ኛ ደረጃ ጀምሮ ተመልምለው እየተረዱ፣ እየተደገፉ አድገው ዩኒቨርሲቲም ሲገቡ ወጪ ተችሎላቸው ተመርቀው ሥራ ተመድበው ተኮትኩተው ያደጉ ልጆች አሁን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን ወታደራዊና ቦለጢቃዊ የአመራር ቦታውን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ተቆጣጥረውት ይገኛሉ። የጎጃሙ ቋጠሮ በቶሎ የማይፈታው ለዚህ ነው። ከባድ ነው። እንደ ጎንደርና እንደ ወሎ አጀንዳ አራማጆቹ ከዐማራ ፋኖ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራር ውጪ አይደሉም። ራሳቸው አመራር ናቸው። የጎጃሙ ሴራ አደገኛነቱ ለራሳቸው ለጎጃም ዐማራ ፋኖዎች ጭምር ነው። ሴራውን የማያውቁ፣ በምልመላው ውስጥ ያልነበሩ። ነገር ግን ጎጃም መወለዳቸው፣ ዐማራ መሆናቸው፣ መከራው ገፍቶ ወደ ትግሉ የቀላቀላቸው። በንፁሕ ዐማራነት መንፈስ የሚታገሉቱ በተለይ ኦርቶዶክሳውያኑ ምሁር ጀግና ፋኖዎችም፣ ከሕዝብም መካከል እየተለቀሙ በሙሉ እየተወገዱም ነው። ከተሰመረው ቀይ መስመር የሚያልፍ የጎጃም ዐማራ ፋኖ ጀግና ከጀርባ በመቺ ኃይል ይመታና ይወገዳል አልያም በድሮን በጥቆማ በጅምላ ይጨፈጨፋል። አለቀ።

"…የጎጃሙ ኃይል የሚዲያ የበላይነት አለው። የአክቲቪስቶችም የበላይነት አለው። የጋዜጠኞችም የበላይነት አለው። የቴሌግራም ገጽ ላይ የተከፈቱ አብዛኛው ፔጆች የጎጃም ልጆች ፔጅ ነው። ቴሌግራም ላይ በየቤቱ ድምጻቸው ጎላ ብሎ የሚሰማውም የእነሱ ድምፅ ነው። ነገሩ የገባቸውም ያልገባቸውም አክቲቭ ሆነው ነው የሚንቀሳቀሱት። ሚዲያውን በሰበር ዜና የሚያጨናንቁትም እነዚሁ አካላት ናቸው። ግንብ አያፈርሱም እንጂ እንደ ኢያሪኮው ሠራዊተ እስራኤል በጩኸት የሚተካከላቸው የለም። እናም ይሄን አስኳል ሰብሮ ገብቶ ነገርየውን ለመጋፈጥ የፈጣሪ ጥበቃና ርዳታ ከሌለህ ከባድ ነው። አደገኛም ነው። አብዛኛው ሰው ነገርየው አልገባውም። ነገርየው እጅግ ረቂቅ፣ ውስብስብና የተጠላለፈ ነው። በጎጃም ጉዳይ ትንታኔ የሚሰጡ ጋዜጠኛ በለው ወላ ቦለጢቀኛ የነገሩን 1% እንኳ ዐውቆ አይደለም የሚንቀሳቀሰው። አልገባቸውም ባይ ነኝ። በጎጃም ሀብቱ አለ። ገንዘቡ አለ። መሣሪያው አለ። የሰው ኃይሉ በሽ ነው። ግን ትግሉ ከላይ ተጠልፏል። ተጠልፏል ሲባል እንዲህ በዋዛ በፈዛዛ የሚነገርና የሚታለፍ ተጠልፏል አይደለም። ከባድ ጥልፍ ነው። እሱን መጋፈጥና ማስተካከል ካልተቻለ ዓይናችሁ እያየ ጎጃም ዱቄት ይሆናል። አንድ ዐማራ ብቻ ነው የሁሉም መዳኛ። እኛ ብቻ ብሎ ተገንጣይ፣ ጠቅላይ ሓሳብ ማራመድ አደገኛ ነው። አጥፊ አውዳሚም ነው።

"…አሁን በጎጃም ያለው የዐማራ ፋኖ በጎጃም 95% ቱ አመራር አጠቃላይ የዐማራ አንድነት እንዲፈጠር አይፈልግም። 5% ቱ ብቻ ነው አንድነት ፈላጊው። የሚበልጠው ስግብግብ፣ ተረኛ ገዢ ለመሆን የቋመጠና ካልተሳካ ጎጃምን ክልል ወይም ሀገር ማድረግ የሚፈልግ ጎጠኛ ነው። መስከረም ላይ አንድነቱ ሊመጣ ሲል ጎንደር የሚገኘው የዐማራ ፋኖ በጎንደር የእነ አርበኛ ባዬ ቡድን በእስክንድር ነጋ ተጠልፎ ከነበረው የእነ አርበኛ ኃብቴ ቡድን ጋር ንግግር ላይ ስለነበረ አንደነቱ ሳይበሰር ተራዘመ። በመሃል ግን በእኛ ምክንያት አንድ ባለመሆናችን የዐማራን ሕዝብ መከራ ከሚያራዝም ብለው ጎንደሮች በቃ አንድነቱ ይፍጠን፣ የእኛና የእነ ሀብቴም ንግግር ከሰመረ እና ከተሳካ ከአንድነቱ በኋላ አስፈላጊውንና ተገቢውን ሥፍራ እንሰጣለን በመላት ከሸዋም፣ ከወሎና ከጎጃም ጋር መክረው ወሰኑ። በውሳኔውም መሠረት ከብዙ ክርክርና ውይይት በኋላ የአንድ ዐማራ ፋኖ መሪዎች፣ የሥልጣን ድልድሉም ተወስኖ አለቀ። ሁላቸውም በተስማሙበት መሠረት አርበኛ ዘመነ ካሤ የዐማራ ፋኖ አንድነቱ ጊዜያዊ መሪ እንዲሆንም ወሰኑ። ወሰኑና ወደ አፈጻጸሙ፣ ወደ ማወጁ ሊሄዱ ሲሉ የጎጃሞቹ ተወካይ ጠበቃ አስረስ መዓረይ ሳንካ መፍጠር ጀመረ። ጭራሽ ከውይይቱ ስፍራ ጠፋ። እልም ብሎም ጠፋ። እንደ ድንገት ሲገኝም ሳንኳ እየፈጠረ ያለቀ የደቀቀውን ጉዳይ እንደገና እያመሰው ይረብሽ ጀመር።

"…አስረስ መዓረ የዘመነ ካሤን መሪነትን በተለይ ጎንደሮች ተቀብለናል ማለቱ አስደነገጠው። ተሸበረም። ቋሚ ትርክት፣ እንደ ፍልስጤምና እስራኤል፣ እንደ ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ፣ እንደ ሕንድና ፓኪስታን ይተያይ ዘንድ ሰኔ 15 የተባለ መርዛማ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎን መከፋፈያ ገዳይ ትርክት ደምስሶ የሚያስቀር ውሳኔ ነበር በጎንደሮች በኩል በወሎም የተወሰነው። ይሄ ነገር ለእነ አስረስ መዓረይ ቡድን አልተዋጠም። የዚያን ሰሞን አስረስ መዓረይ ጠፍቶ ሳለ በጎጃም የድሮን ጥቃቱ የትየለሌ ሆነ። በተለይ የአርበኛ ዘመነ ካሤ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉት የጎጃም ዐማራ ጀግኖች በሙሉ እየተለቀሙ ተደመሰሱ። ተበሉም። በጎን ደግሞ እነ ይሄነው የሸበሉ፣ እነ አማኑኤል አብነት፣ እነ በላይነህ ሰጣርጌ ግሩፕ፣ እነ አልማዝ ባለጭራዋ፣ እነ ሞጣ ቀራንዮ የተባሉ የምሥራቁ ጎጃም የእነ አስረስ መዓረይ የሳይበር ሠራዊት አርበኛ ዘመነ ካሤን በጥበብ በስውርም፣ በግልጽ በገሀድም፣ በቅኔ፣ በአግቦ፣ በአሽሙርም በማዋረድ፣ በማንቋሸሽ ቀጣዩ የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ የሚሆነው ሰው ጠበቃ አስረስ መዓረይ መሆኑን ማወጅ ጀመሩ። መጻፍም ጀመሩ። "ዘመነ አስረስን የሚበልጠው ብረት በመጨበጥ እንጂ ሁለቱም በንባብ እኩል ናቸው።" ብለው በድፍረት መጻፍ ሁላ ጀመሩ። ድሮኗ ዘመነ ካሤ ላይ አነጣጥራ መቆም ጀመረች። ያኔ ነው እኔ ዘልዬ ነገር ሳይበላሽ ወደ ጎጃም የገባሁት።

"…የዐማራ ፋኖ በጎጃም የታችኛው አመራሮች ጥያቄ ማንሣት ጀመሩ። ለምንድነው አንድነቱ የሚዘገየው? ምንድነው ችግሩ በማለት እነ አስረስ እና እነ ዘመነ ላይ ጥያቄ ያዥጎደግዱ ጀመር። ሕዝባችን እያለቀ ነው። ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞቻችን ጋር በቶሎ አንድ ካልሆንና ጎንደር ችግር ሲገጥመው እኛ ሄደን፣ እኛ ችግር ሲገጥመን ሌላው ጋር ሄደን ካልተዋጋን እንዴት ማሸነፍ እንችላለን። አንድ ካልሆን ማሸነፍ አንችልም። በየሰፈራችን ሆነን በየተራ እያለቅን ነው። ምንድነው ችግሩ? ከእናንተ ነው ወይስ ከጎንደሮች፣ ከወሎና ከሸዋ? በማለት መጠየቅ ጀመሩ። ወተወቱም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ጎንደር፣ ሸዋ፣ ወሎም እየደወሉ ምንድነው ችግሩ በማለት ይጠይቁ ያዙ። ተጠያቂዎቹም ለጠያቂዎቹ ምላሽ ይሰጡ ጀመር። "እኛ ሁሉንም ጨርሰን የምንጠብቀው የጎጃምን ውሳኔ ነው። መሪውንም ከጎጃም መርጠናል። የጠፋው የእናንተ ተወካይ አስረስ ማረ ነው" በማለት ይመልሱላቸው ጀመር። በዚህ የተበሳጩት ምስኪን ነገሩም ያልገባቸው የጎጃም ዐማራ ፋኖዎች እነ አስረስን ወጥረው መያዝ ጀመሩ። ዘመነ ካሤም ኧረ ይሄ ነገር እንዴት ነው በማለት በለሆሳስ መጠየቅ ጀመረ።

"…ቀደም ብሎ በዲፕሎማሲው፣ በፖለቲካው ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት የራሱን የፖለቲካ ካፒታል የገነባው አስረስ መዓረይም የእኔ መዓት እንደሚዘንብበት ሳያውቅ፣ ሳይረዳ ለብቻው ይዳክር፣ ይፈነጥዝ ያዘ። የበፊት የኢሣት ጋዜጠኞች እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ወንድምአገኝ፣ አነ ደረጄ ሁላ የአስረስ መዓረይ ልሣኑ ሆኑ። አፍቃሬ ወያኔዎቹ ኢትዮ ፎረሞችና እነ በቃሉ አላምረው ሁሉ፣ እነ ኦሮምቲቲው ተብታቤ ሞገስ ዘውዱም ሁሉ ቤተኛው ሆኑ። ትሪፕል ኤዎችም ፈረንጅ ጋዜጠኛ ሁላ ላኩለት። ከጋዜጠኛው ጋር በነበረው ቃለ መጠይቅ ላይም ትግሬዋ ወያኔ በወልቃይት በማይካድራ ለጨፈጨፈችው…👇②✍✍✍


"ርእሰ አንቀጽ"

"…ዘንድሮ በ2017 ዓም ከጎንደር መልስ ነበር ከገና ከበዓለ ልደት በፊት ወደ ጎጃም የገባሁት። መጀመሪያ አገባቤ እስከ በዓለ ጥምቀት በዚያ ለመቆየት ነበር አስቤ፣ አልሜ፣ አቅጄ ወደ ጎጃም የሄድኩት። ጎጃም ገብቼ ነገርየውን ሳየው ግን ሓሳቤን ቀይሬ አይደለም በጥምቀት በልደት ልመለስ ዐቢይ ጾምን በዚያው በጎጃም አሳልፌ እስከ ትንሣኤ ድረስ ለመቆየት ወሰንኩ። በዚህ የውሳኔ ሓሳቤም ልጸና አልቻልኩም። በጎጃም ያለው የደነደነ ነገር አይደለም እስከ ትንሣኤ ፋሲካ እስከ ነሐሴ ጾመ ፍልሰታ ድረስም ብቆይ የማይቀረፍ መሆኑ ገባኝ። እሱንም አራዝሜ እስከ መስከረም 1/2018 ዓም እስከ ቅዱስ ዮሐንስ በዓል አስከ እንቁጣጣሽ ድረስ እንደምቆይ ገለጥሁ። መጀመሪያ መርጡለ ማርያም፣ ከዚያ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰነበትኩ በኋላ ነው አሁን በዓቴን ወዳጸናሁበት ጎጃም ጮቄ ተራራ ላይ ከትሜ የቀረሁት። ከመረጃ ቴቪ ጋር ስንነጋገር እሺ ጎጃምስ መግባቱን ግባ፣ እስከመቼ ነው የምትቆየው? ነበር የተቋሙ ጥያቄ። እስከ መስከረም ድረስ ነው የምቆየው የሚለው የእኔ መልስ አስደንጋጭ ነበረ። አሁን ላይ ሳየው መስከረምም ከጎጃም የምወጣ አይመስለኝም። ማርያምን በጣም አስፈሪ፣ በጣምም ከባድ ነው የጎጃም ነገር። እንደሚወራው አይደለም። ጀግንነት፣ ወንድነት ሳያንሳቸው ነገር ግን ተተብትበዋል አይገልጻቸውም።

"…ከመረጃ ቲቪ እንደለቀቅኩ ለዘመድ ቴቪ ምሥረታ ወደ ራየን ወንዝ ማዶ በዓቴ ለጥቂት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያልኩ ከመመለሴ በቀር ከወርሀ ታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ አብዛኛውን ጊዜዬን እያሳለፍ የምገኘው በዚያው በጎጃም ነው። እኔ ጎጃም በመግባቴ መጠነኛም ቢሆን ሚጢጢዬ ለውጥ መምጣቱ በሁሉም ዘንድ የሚታመን ነው። ለውጡ መሠረታዊ ለውጥ ግን አይደለም። የጎጃም ጉዳይ በጣም ውስብስብ ነው። የጎጃም ጉዳይን ከባድ የሚያደርገው የገንዘብ ጉዳይም ስላለበት ነው። የውጭ ኃይሎች የፖለቲካ ኢንቨስትመንት አለበት። የጎጃም ጉዳይ የማንነት ጥያቄና እጅግ አደገኛው የሃይማኖት ጉዳይም አለበት። ጎጃም የታላቁ ወንዝ የዓባይ ውኃ መገኛም ስለሆነ የብዙዎች ዓለም አቀፍ ኃይሎች ትኩረት ሰጥተው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚፋተጉበት ስፍራ ነው። የፖለቲካ ምእመናን እንደሚያስቡት ጎጃም በአርበኛ ዘመነ ካሤና በጠበቃ አስረስ መዓረይ ምናምን ተብሎ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። እጅግ እጅግ አደገኛና ከባድ ነገር ነው በጎጃም ያለው። መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ከሌለ በቀር ጎጃም ብቻ ሳይሆን ዐማራ በጎጃም ጉዳይ ከባድ ዋጋ ይከፍላል። ከባድ ኪሳራንም ያስተናግዳል።

"…እኔ ዘመዴ ጎጃም ከገባሁ ወዲህ ተለቅመው በሴራ ከተገደሉት ከአርበኛ ዮሐንስና ከአርበኛ ሃይማኖት በቀር በጎጃም ጋብ ብሎ የነበረው የድሮን ጭፍጨፋ እና ጀግናን ከጀርባ ነጥሎ የመምታቱ ነገር ጋብ ብሎ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ሰሞኑን ግን በጊዜ የለንም መንፈስ ይመስላል ሴረኞቹ የሴራ ሰንዱቃቸውን ከፍተው እንደገና በድጋሚ አገርሽተው ጎጃምን በተለየ መልኩ ማስጨፍጨፋቸውን ጀምረው ታይተዋል። ጎጃምን ወያኔ ትፈልገዋለች። ሻአቢያም ይፈልገዋል። ኦህዴድ ኦነግም እንዲሁ ሴል አስገብቶ ተቀምጧል። በጎጃም የጎንደር ስኳድም እጁን ነክሯል። የጦር መሪ ሁላ አለው በጎጃም። በጎጃም አገው ሸንጎ ወታደራዊ ቁመናው ከፍ ያለነው። በጎጃም የቅባትና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ፉክቻም ይንፀባረቃል። ብአዴን በሁሉም የዐማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ገብቶ ቢታይም እንደ ጎጃም ዐማራ ፋኖ የተቆጣጠረው ግን አለ ማለት አይቻልም። አሕፋድ እስክንድር ነጋ እንኳ የአባቴ ሀገር ነው ብሎ የራሱ ሴል አለው ጎጃም ላይ።

"…ነገርየውን ስጽፈውም፣ ስናገረውም ይመርራል። ያንገሸግሻልም። ነገር ግን ደፍሮ፣ ጨክኖ ለመፍትሄው ካልተንቀሳቀሱ በቀር የጎጃም ኪሳራ በትውልድ እንኳ በቶሎ አይመለስም። ማርያምን እንደቀላል አትዩት። ሰሞኑን ጮቄ ከመግባቴ በፊት በጎጃም ጉዳይ ራሳቸው ጎጃሜ የሆኑ የጎጃም ዐማሮችን ለማግኘትና ለመወያየት ሞክሬ ነበር። ሁላቸውም የሚነግሩኝ ነገር እጅግ ከባድ ነው። በጣም ከባድ ነው። አገዛዙ ራሱ ዐማራን እያደቀቀ ያለው ሁለቱን ጎጎ ዎችን ግራና ቀኝ ገዝቶ ይዞ ነው። ጎጃምና ጎንደርን። የወያኔም የኘሆነ የኦሮሙማው ኃይላት አብዛኛው የብአዴን ባለ ሥልጣናት የሚመረጡት ከጎጃምና ከጎንደር ነው። አሁንም በፋኖ አንድነት ላይ ውዝግብ እየፈጠሩ የሚገኙት ሁለቱ ጎጎ ዎች ናቸው። ከዚያ አካባቢ ባለው እርስ በእርስ መናናቅ፣ መገፋፋት ምክንያት ዐማራ ከባድ ዋጋ እየከፈለ ነው። ሰኔ 15ን እንደ ቤንዚን እየተጠቀሙበት ሁለቱ ዝሆኖች ሲራገጡ ምስኪን ሳር ዐማራው እየተጨፈለቀ፣ እየተደፈጠጠም ነው። ይሄን ማስተካከል በቀላሉ የሚቻል አይመስለኝም። አገዛዙም ይሄን በሚገባ ስለሚያውቅ ነው ደረቱን ነፍቶ እያላገጠባቸው የሚገኘው።

"…የታመመ ሰው መድኃኒት ነው የሚታዘዝለት። መድኃኒት ደግሞ በባህሪው መራር ነው። ይጎመዝዛል። ያንገሸግሻልም። የኮሶ መድኃኒት የሚጠጣ ሰው ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ እየተባለ ከመድኃኒቱ በኋላ ሲፈወስ የዶሮ ፍትፍት እንደሚጠብቀው እየተነገረው ነው ያን ሆምጣጤ፣ ሬት የተጨቀጨቀ የሚመር የኮሶ ፍሬ እየተንዘፈዘፈ፣ እየተንገሸገሸ የሚጠጣው። የሚጋተው። ያለበለዚያ የኮሶን ትል አይስክሬምና የፍራፍሬ ጭማቂ ጁስ አይፈውሰውም። የዐማራም ትግል ለደረሰበት በሽታ መፍትሄው ዶሮ ማታ ዶሮ ማታ እያለ ጥርሱን ነክሶ ጎምዛዛውን መድኃኒት መርጦ ጨክኖ መዋጥ ብቻ ነው። የዐማራ ትግል እንዲፈወስ መፍትሄው እንዲያ ማድረግ ነው። አሁን የሚታየው የትግሉ አያያዝ ግን ለዐማራም፣ ለራሳቸው ለታጋዮቹም ምንም አይጠቅማቸውም። ጠብ የሚል ነገርም አያመጣላቸውም። ትግሉም ፈቀቅ አይልም። አንዳንድ የፋኖ መሪዎች፣ በእገታ፣ በኮንትሮባንድ፣ በቀረጥና ታክስ ስብሰባ፣ በመሳሪያ ሽያጭ፣ በግብርና ሥራ ላይ እየተሳተፉ ስለሆነ ትግሉ እንዲቋጭ ፈጽሞ አይፈልጉም። ሴረኞችና ሴራ ራሱ የሚመራው የዐማራ ትግል ትርፉ መጪው ትውልድ ራሱ ቀና የማይልበትን ስብራት ጥሎ ማለፍ ብቻ ነው የሚሆነው። እናም ከወዲሁ በፍጥነት የዐማራ ፋኖን ትግል ፍቱን መድኃኒት በመስጠት ከደረሰበት ስብራት መፈውስ ያስፈልጋል። ማርያምን ጊዜ የለም። እኔ ይሄን እየጻፍኩ የዐማራ ፔጆችን ዞር ብላችሁ ስታነቡ በብርጌድ ሰበር ዜና ድብልቅልቁ ወጥቶ ስለምታዩ ግራ መጋባታችሁ አይቀሬ ነው። ግን ጨክናችሁ መድኃኒቱን ዋጡት። የሚሻለው የእኔ የዘመዴ ምክር ነው።

"…እንደነገርኳችሁ ነው። አሁን የዐማራ ዋነኛው የችግሩ ቋጠሮ የሚገኘው ጎጃም ውስጥ ነው። ሰንኮፉ የሚገኘው ጎጃም ውስጥ ነው። ችግር ሸዋም አለ። ጎንደርም ወሎም አለ። የሚፀንነው ችግር ያለው ግን ጎጃም ነው። የጎጃም ዐማራ ችግር ደግሞ አሁን ዝም ብዬ ሳየው በምክክር፣ በውይይት፣ በንግግር የሚፈታም አይመስለኝም። ሥር የሰደደ፣ ቀድመው የተዘጋጁበት ኃይሎች የላይኛውን ወሳኝ ስፍራ የተቆጣጠሩት ስለሚመስለኝ ነገርየውን ከባድ ያደርገዋል። ለምሳሌ ከሸዋ በቀር ጎንደርን፣ ወሎን ክልል የማድረግ እንቅስቃሴ በሰፊው ነው ያለው። ሁሌም ሲናገሩ ነው የምትሰሟቸው። ነገር ግን በአፍ ይነገር፣ ይመከር፣ ፕሮፓጋንዳም ይሠራበት እንጂ በወሎም፣ በጎንደርም አፍቃሬ መንግሥት የሆነ አካል የሚያወራው እንጂ ነገርየው በሠራዊቱ ውስጥ ሰርጾ የገባ አይደለም። የነገርየው የክልልነት አራማጆቹም ከሠራዊተ ፋኖ ውጪ ያሉ አካላት ናቸው። በጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ስኳዶች እና የዐብን ብአዴን አባላት ሲሆኑ፣ በወሎ ደግሞ አፍቃሬ ኦሮሙማው እዚህ ግባ የማይባል የወሃቢይ እስላም…👇①✍✍✍


መልካም…

"…እኔ ዘመዴም በአዲስ አበባ የነበረኝን ቆይታ አጠናቅቄ በሰላም ጎጃም ጮቄ ተራራዬ ላይ ደርሻለሁ። በአዲስ አበባ የጎጃሙንና የሸዋውን የድሮን ጭፍጨፋ አጀንዳ ለማስቀየር በአባ ደጀኔ ቶላ ወይም በአቡነ ገብርኤል አማካኝነት በፀጋዬ ሮቶ የሠራተኛ ማኅበር አዳራሽ በእመቤታችን ላይ የተዘራውን የምንፍቅና ትምህርት መስመር ያስያዙ ሊቃውንት ትምህርት ስኮመኩም ውዬ ነው እነሱ ወደማይነኩት አጀንዳ ወደ ጮቄ ተራራ ተጋድሎዬ የተመለስኩት። ጮቄ እኮ ነፍስ ነች።

"…ወደ ጮቄ ተራራ ስሄድ በቦሌ አየር መንገድ በኩል ነበር ያለፍኩት። በዚያም ሳልፍ የቀድሞው ግራኝ አሕመድ ረዳት፣ የአሁን ዳግማዊ ግራኝ አሕመድ አጋዥ ቱርክ በቦሌ አየር መንገድ በሦስት ግዙፍ አውሮጵላኖች የተጫኑ የዐማራ መጨፍጨፊያ ቦንብና ጥይት እያራገፉ ነበር የተመለከትኩት። ይሄን የቱርክን ጭካኔ ያየው የተመለከተው የዐማራ አምላክ ደግሞ ቱርክ በዛሬው ዕለት በመሬት መንቀጥቀጥ እያራገፋት መሆኑን ከአልጀዚራ ዜና እያየሁ ስደነቅ ነበር። ባለፈውም እንዲሁ በኢትዮጵያ ጉዳይ እጇን ስታነሣ ዱቄት አድርጓት ነበር። አሁንም ገና ምን ዓይተው።

"…አሁን ጮቄ ተራራ በአቴ ደርሻለሁ። የተከመረ የቤት ሥራ ነው የጠበቀኝ። እንደ አዲስ የሚነሣብኝ የተለየ አዋራ ባይኖርም ነገር ግን ከበፊቱ የከፋ ሴራ አለና እሱን ሴራ ወደማፍረሱ እገባለሁ። በድፍረት እናገራለሁ ጎጃም አደጋ ውስጥ ነው። ባለድርሻ አካላትና ይመለከተናል የምትሉ በሙሉ በጊዜ መፍትሄው ላይ ካልተረባረባችሁ መጪው ጊዜ ከባድ ነው። የአንድነት ዘመቻ ብላብላ ፉገራውን ለጊዜው አቁማችሁ የምር አንድ ካልሆናችሁ እመኑኝ ደም እንባ ብታለቅሱ የማትወጡት አዘቅት ውስጥ ነው የምትዘፈቁት። መዝግቡልኝ። ተናግሬ የቀረ የለም አይደል? እደግመዋለሁ መዝግቡልኝ።

• እናሳ ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?

31k 0 6 149 1.3k

ረቡዕ፦ አልዓዛር ይባላል።

"…የማርታና የማርያም ወንድማቸው አልአዛር መሞቱን ተከትሎ ከተቀበረ ከ4 ቀን በኋላ ጌታ በሕዝቡ ሁሉ ፊት መግነዝ ፍቱለት መቃብሩንም ክፈቱለት ሳያስብል እንዳስነሣው እያስበን የምናከብርበት ዕለት ነው። “…ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” ዮሐ 11፥25 የሚለውን ወርቃማ የትንሣኤ ትምህርት ያስተማረንም በዚሁ በአልአዛር መቃብር ላይ ቆሞ ነበር።

"…በእርግጥ አልአዛር የሞተው በዚህ ዕለት አልነበረም። አልአዛር የሞተው ከበዓለ ሆሣዕና በፊት በነበረው ረቡዕ ሲሆን አራተኛ ቀኑ የሚሆነው ቅዳሜ የሆሣዕና ዋዜማ ላይ ነበር። ጌታም ያስነሣው በዚሁ በዕለተ ቅዳሜ መጋቢት 17 ቀን ነበር። በዚሁ ቀን መታሰቢያ እንዳያደርጉለት የግርግር ወራት ሆነ። በ22 ሆሳዕና ሆነ። በ23ም ርግመተ በለስ አንጽሖ ቤተ መቅደስ ሆነ፣ ደግማሞ የአልዓዛር ትንሣኤ ከሞት ወደ ሞት እንጂ ለሕይወት ያልሆነ፣ ከጊዜም በኋላ ተመልሶ የሚሞት ትንሣኤንም ጠባቂ ስለነበር በዚህ ምክንያት የትንሣኤው በኩር የክርስቶስ ትንሣኤ ካለፈ በኋላ በዛሬው ዕለት እንዲከበር ሥርዓት ሠርተውልናል።

"…ለምሳሌ ጌታ የወይን ጠጁን ወደ ውኃ የቀየረው የካቲት 23 ነበር። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ግን ሥርዓት ሲሠሩልን የካቲት 23 በዐብይ ጾም የሚውል ሆነው ቢያገኙት በዚህ ዕለት ሀሴት፣ ደስታ ማድረግን ከልክለው የየካቲት 23ን የቃና ዘገሊላ በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተው ከበዓለ ጥምቀት በኋላ የውኃ በዓል ከውኃ ጋር ይከበር ይውል ዘንድ እንደወሰኑት ሁሉ የአልአዛርንም ትንሣኤ ከትንሣኤ ጋራ እንዲውል ነገር ግን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በዛሬው ዕለት እንዲከበር አደረጉልን።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።

36.1k 0 31 802 1.3k

"…የምርኮኛ አያያዝ በምሥራቅ ጎጃም…

"…እነኝህ ወጣቶች ሃይማኖት በቀለ፣ መሰረት አሳዬ እና ድንበሩ ሽታ ይባላሉ። ከሰሞኑ ከወራሪው ሠራዊት ካምፕ በመውጣት የወገንን ኃይል የተቀላቀሉ የ33ኛ ዙር አድማ መከላከል የብርሸለቆ ምሩቃን ናቸው። የአረጋ ከበደን "ሙሴዎች" እየተቀበልን ነው። በነገራችን ላይ ብርሸለቆ ከተመረቀው 5,500 የአድማ መከላከል አባላት መካከል ግማሽ ያህሉ ከነ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል ይላል የአስረስ የፌስቡክ ልጥፍ።

"…በጦርነት ሕግ ምርኮኛ ከነ ሙሉ ዝናሩ፣ ካርታ ሙሉ ጥይቱ ክላሹን ሞልቶ በአንድ ጊዜ ዋነኛውን የጦር መሪ እንደ አጃቢው አክት እየደረገ አጠገቡ ተደርድሮ ፎቶ ሲነሣ የማየው እዚያው ምሥራቅ ጎጃም አስረስ መዓረይ ጋር ብቻ ነው።

"…እኔ በየትኛውም ዓለም እንዲህ ዓይቼ አላውቅም። ምርኮኛ ጫማ ያወልቃል፣ ትጥቅ ያስረክባል። ከዚያ ወደማረፊያ ቦታ ሄዶ የሥነ ልቦና አገልግሎት ያገኛል። ጎጃም እነ አስረስ መዓረይ ጋር ግን ይሄ የለም። ከፋኖ ይልቅ ምርኮኛ ነው ክብር ያለው። እንዴት ሰው ለራሱ አይሰጋም? ምርኮኞቹ የተለየ ተልእኮ ይዘውስ ከሆነ የመጡት? ወይስ አገዛዙ ነው ጠባቂ ብሎ የሚልክለት? ቀሽም።

"…ይሄን ዓይነቱ ዝርክርክ ነገር ወሎ ላይ አላይም። ጎንደር ላይም አልመለከትም። ሸዋም ላይ እነ መከታው ጋር እንጂ እነ ደሳለኝ ጋር አላይም። የሚያልቀው፣ የሚጨፈጨፈውም የጎጃም ፋኖና የጎጃም ሕዝብ ነው። የምርኮኛ እንክብካቤም ያለው ደግሞ እዚያው ጎጃም በተለይም ምሥራቅ ጎጃም እነ አስረስ መዓረይ ጋር ነው። አልገብቶኝም።

"…አሁን እኮ ይሄን የመሰለ ጮማ ምርጥ ምክሬንም በክፉ የሚያይ ሰው አይጠፋም። ወዳጄ አትቀልዱ። የፎቶ ቦለጢቃው ምንም ጠብ የሚል ነገር የለውም። ወሬም፣ ፕሮፓጋንዳም ቢሆን የሚያሳምንና የሚመስል በልክም ሲሆን ነው የሚያምረው።

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ

40.7k 1 12 194 1.6k

መልካም…

"…6 ፍሬ ሰዎች የተበሳጩበት ርእሰ አንቀጻችን ተነብቧል። አሁን ደግሞ የእናንተ ሓሳብ የሚደመጥበት መርሀ ግብር ይከተላል። ጻፉ። አስተያየታችሁን ጻፉ።

"…በነገራችን ላይ ካልቀደምናቸው በቀር ሲኖዶሱ ራሱ የተጠለፈ ነው የሚመስለኝ። አባ ደጀኔ ቶላ፣ አቡነ ገብርኤል የመነፈቀ ቃል የዘሩት ብቻቸውን ተደብቀው መስለውኝ ነበር። ለካስ አባ ወልደ ትንሣኤ ከጉባኤው በደስታ ጮቤ ረግጠው ተቀምጠዋል። አህያ ብሉ፣ እየሱስ አማላጅ ነው፣ ታቦት ላይ ያፌዙት ሊቀጳጳስ በዚያ አሉ።

"…በተሃድሶነት ተከስሶ በስንት አማላጅ ተንበርክኮ እግር ላይ ወድቆ ይቅርታ ጠይቆ የነበረው አቶ ፀጋዬ ሮቶም በዚያው በጉባኤ ላይ ይታያል። ደጀኔ ቶላ አባ ገብርኤል እመቤታችንን አዋርዶ በተሳደበ ጊዜም እጁ እስኪላጥ ሲያጨበጭብ ይታያል። አደጋ ደርሶባቸው አንጎላቸው ተከፍቶ ከተሰፋ በኋላ አፍቃሬ መናፍቅ የሆኑት አባ ወልደተንሣኤም በድል አድራጊነት ስሜት ተኮፍሰው ይታያሉ።

"…በዚያው ጉባኤ ላይ "አትደንግጡ፣ አትፍሩ" የተባሉት የአቶ ፀጋዬ ሮቶ ሠራተኞችም ሲያጨበጭቡ ይታያሉ። ማኅበረ ቅዱሳን ስቱዲዮው የተገነባው በፀጋዬ ሮቶ ብር ነው። የቤተ ክህነቱም የቴሌቭዥን ጣቢያ ስቱዲዮም የተገነባው በዚህ ባለፀጋ ገንዘብ ነው። ፓትርያርኩን ጨምሮ ባለሀብቱ ቤቱ ጠርቶ እጅ መንሻ ያልተሰጠው ሰው የለም። የገንዘቡ ምንጭ ሮዳስ ቀለምና ሮቶው ብቻ አይመስልም። የሆነ የታቀደ ነገር እንዳለ ይሸተኛል።

"…እደግመዋለሁ ከውጭ ማፍረስ ያልቻሏትን ቤተ ክርስቲያን ከውስጥ ለማፍረስ ግርርር ብለው የገቡ ይመስለኛል። ሰዶማውያን መብት እንዲኖራቸው በስሱ የሚሞግቱ፣ ለመናፍቃን ተቆርቁረው የሚሞግቱ ጉዶችን እያየን ነው። ይላላጣሉ እንጂ ምንም አያመጡም።

• በነገራችን ላይ ደጀኔም ብፁዕ አይባልም። የአረቄያም ሁሉ መጫወቻ ሆነን እንቅር በማርያም።

41.2k 1 27 177 1.3k

👆⑤ ✍✍✍ …ሕዝቡን ሊምር ሲሻ ለሙሴ ላጠፋ ነኝ እንዳለው አሁንም የእናቱን ርኅርኂትነት ያውቃልና ማርልኝ እንድትለው በሲኦል ያሉትን ነፍሳት አሳያት። ስለዚህም  እርስዋ መሪር እንባን አለቀሰችና "ቅትለኒ በእንተ ቤዛሆሙ- እኔ ስለ እነርሱ ልሙትና ማርልኝ ስትል ለምነዋለች፣ ጌታም ቅዱሳኑ ሁሉ ሰብስቦ ወርዶ ነፍሷን ታቅፎ ታይቷልና አስተርእዮ ተብሏል። ሥጋዋን አቃጥላለሁ ያለውን ታውፋንያን እጆቹን ቆርጦ የእናቱን ሥልጣን የገለጠበት ቀን ነው።ሥጋዋን ያቃጥል ዘንድ በድፍረት የመጣውን ይቀጠልለት ብላ ቤዛ ሁናው ተቀጥሎለታል።  ስንዴ መሬት ላይ ስትወድቅ ብዙ ታፈራለች። ካልወደቀች ግን ብቻዋን ትኖራለች(ዮሐ፲፪፥፳፬) የድንግል ማርያም መሞት ብዙ ሰማዕታትና መናንያን ሊቃውንት ይፈሉ ዘንድ የቤተክርስቲያን ቤዛ ነው! ያለ ድንግል ማርያም ድኅነት የለም መባሉም መሬት ላይ ካልወደቀች ፍሬ የለም ብቸዋን ትኖራለች እንጅ እንዳለው ነው። የድንግል ማርያም፦ ልደቷ ጥቅም፣ ልኅቀቷ ጥቅም፥  መፅነሷ ድኅነት፥መውለዷ ድኅነት፥ መሰደዷ ድኅነት ፥መመለሷ ድኅነት፥ ማሳደጓ ድኅነት፥ መሪር እንባዋ ድኅነት፥ ድንጋጼዋ ድኅነት፥ ጸሎቷ ድኅነት፥  መሞቷ ድኅነት፥ ማረጓ ድኅነት ነው፡፡ ፷፬ቱ እድሜዋ ሁሉ የደረሰባት እያንዳንዱ መከራዋ ለሰው ድኅነት ስለሆነ እድሜዋ ራሱ ቤዛችን ነው። ፷፬ መቁጠሪያ የምንጸልየው ፥ ፷፬ሰላም ለኪ የምንማጸነው ስለዚህ ነው።

"…ነገሬን በወዳጇ በአባ ጊዮርጊስ ሰዓታት ልጠቅልል" ንትፈሣሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም፤ ወበደመ አስካልኪ መዓድም፥ ቅድስት ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም- ድንግል ማርያም ሆይ በሚጣፍጠው ስምሽ ደስ ይለናል፥ ጥዑም በሆነው በማኅፀንሽ ፍሬ በክርስቶስ ደምም ሐሴትን እናደርጋለን፥ ዕንዕት ክብርት ንጽሕት ልዩ እመቤታችን ሆይ አንቺ ቤዛዊተ ዓለም ነሽ!" ሁላችን እንዲህ እንል ዘንድ የልቡናችንን አውታረ መሰንቆ መንፈስ ቅዱስ ይቃኝልን! አሜን።
    
"…መዝግቡ። አሁን የአገዛዙ ካድሬ ሰባኪያነ ወንጌል ተብዬዎች ስለዚህ ነገር አይተነፍሱም። ስለ ዶሮ ብልት 12 ሁለት መሆን የሚያመሰጥሩት በሙሉ አሁን የሉም። እንዲህ ዓይነቱ ኑፋቄ ሲዘራ ድምጻቸው አይሰማም። ብዕራቸው አይነበብም። አንዴ ቴዲ አፍሮ ሚስት ጋር፣ አንዴ ሌላ ቦታ፣ በየዩቲዩቡ ራሳቸውን የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂ ሊቅ አድርገው የሾሙ፣ አፈ ጮሌ ሸቃጭ ነጋዴ ሰባክያን አሁን የሉም። ትንፍሽ አይሉም። ወዳጄ ሆድና እምነት ይለያያል። በአንጻሩ እንዳልኩት ነው። የመናፍቃን በኃይለኛው በውስጥም በውጭም ማፍላት ሊቃወንተ ቤተ ክርስቲያንን ያበዛል፣ ያስነሣል። የአሕዛብ ሰይፍ ቅዱሳን ሰማእታትን ያበዛል፣ ያስነሣል። ሳይማሩ፣ ሳይጠነቅቁ በብር፣ በጉቦ፣ በፓርቲ ፍላጎትና በደብዳቤ በብሔር ኮታ መሾም፣ አባ፣ ብፁዕነትዎ መባል ብቻውን ከማስከበሩ ይልቅ በሥጋም ያዋርዳል፣ መሳቂያ፣ መሳለቂያ ያደርጋል ያስቀስፋልም። በነፍስም ያስቀስፋል። ዕድሜ ነው የሚያሳጥረው። የእነ አባ ደጀኔም መነሣት እንዲሁ ነው። ለዛሬ አበቃሁ።

ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ በዛዊት ዓለም
የአማኑኤል እናት የመድኃኔዓለም

• ዘመዴ ነኝ ከቤዛዊት ማርያም


👇④ ✍✍✍ …አዳምን የሚያጠቃልል ነው። ከዚህ ተነሥተን ስናየው ድንግል ማርያም የመላእክትም ቤዛቸው ናት!ምነው እነርሱማ ምን በድለው ተቤዠቻቸው? የሚል ቢኖር መልሱን እስክንነግረው ይታገሥ።

"…ከወደቁት በቀር እውነት ነው መላእክት ምንም ነውር የለባቸውም። ነገር ግን ቤዛነት ለበደል ብቻ ሳይሆን ለአንድ አካል ያልተቻለውን ነገር በዚያ ተገብቶ ሲፈጽምለት ቤዛነት ይባላል። ስለዚህ ኃይላተ ሰማያት እግዚአብሔርን አብረውት እየኖሩ ድምጹን እየሰሙ አያዩትም። እንዲያውም ስንኳንስ ሊያዩት ምኞታቸው እርሱን ማሰባቸው ራሱ የማይሻገሩት ሞገድ ይሆንባቸዋል። በሁከት መንፈሳዊ እየዋኙ በኅሊና ርቀት እየመጠቁ ሲያስቡት ከመታሰብ በላይ ይሆንባቸዋል። በመሠረተ ዓለም ይመረምሩታል ይጠልቅባቸዋል፤ በጠፈረ ሰማይ ይሹታል ይመጥቅባቸዋል፤ በክበበ ዓለም ይፈልጉታል ይሰፋባቸዋል፤ በውሳጤ ዓለም ይመኙታል ይሰወርባቸዋል፤ በኅሊና መንፈሳዊት ያስቡታል ይረቅባቸዋል። ስለዚህ ይህን ሁሉ አለመመርመሩን ፊታቸውን፣ እግራቸውን በመሸፈን ረበው በመታየት ይገልጡታል።(ሕዝ ፮፥፩-፰)

"…እንዲህ ሆነው መታየቱ ስንኳንስ መታየቱ መታሰቡ ግሩም ነውና ሲሉ ነው። አሳባቸውንስ እንኳን ባለመመርመር ያሸንፈዋልና "አኀዜ ኪሩቤል-ኪሩቤልን የያዘ" ብሎታል ቅዱስ ሄሬኔዎስ ሐዋርያዊ፡፡ ኪሩቤልን የሚይዝ ማለት ምሉዓነ አዕምሮ የሆኑትን እንኳ መዋዕየ ሕሊና ነው ሲል ነው። አባ ሕርያቆስም" ኀበ ኢይበጽሖ ሕሊና ሰብእ ወኢዘመላእክት አዕምሮ-መለኮትስ የሰዎች ሕሊና የመላእክት እውቀት የማይደርስበት በልዕልና ያለ ግሩም ድንቅ ነው" ሲል አመስጥሮታል። ማየት ቢሳናቸውም ማየት መፈለጋቸውን ግን አላቆሙም። ስንኳንስ የማይበሉት የማይጠጡት መላእክት የሚበሉት የሚጠጡት የሰው ልጆችም  የሚጠግቡት እግዚአብሔርን በማየት ነውና። መዝ 11፥11 ይህን ግን አነርሱ ማድረግ አልቻሉም። ስለዚህ ይህን ያሚያደርግላቸው አካል የማያዩትን ጌታ እንዲያዩት የሚያበቃቸው ቤዛቸው ነው ማለት ነው። እንግዲያውስ ይህን ያደረገችው ድንግል ማርያም ብቻ ናትና ለእነርሱ ቤዛቸው ናት ማለት ነው። የእነርሱ ዐይን ሊያየው ያልደፈረውን የእርስዋ  ሕዋሳት ግን ታቅፈው አጥብተው አሳድገውታልና። ይህንን ቅዱስ ጳውሎስ "ወአስተርአየ ለመላእክት-ለመላእክት የታየ" ሲል ገልጦታል። (፩ ጢሞ ፫፥፲፮) የታየ ማለት ቀድሞ አይታይም ነበር ማለት ነው።

"…ቅዱስ ያሬድም ምስጢሩን በዜማ" ዘመላእክት ይትሜነዩ ርእዮቶ፣ በላዕለ ማይ ዘጠፈረ ቤቶ፣ተወልደ እምድንግል ያርኢ ኂሩቶ፣ ለዘከመዝ ንጉሥ ነአምን ልደቶ-  መላእክት ያዩት ዘንድ የሚመኙት ፥አዳራሹን በውኃ የሠራ፥ቸርነቱን ይገልጥ ዘንድ ከድንግል ተወለደ፥ እንዲህ ያለውን የዘለዓለም ንጉሥ የክርስቶስን ልደት እናምናለን" ሲል አንቆርቁሮታል።( ድጓ ዘአስተርእዮ ዘእግዝእትነ) ይህር ርኀብ ያጠገበቻቸው ይህንን ጥም ያረካቻቸው ድንግል ማርያም በእውነት የመላእክትም ቤዛቸው ናት!

"…ለእኛስ? አብሶ ለእኛማ እንዴታ! የመጀመሪያው ቤዛነቷ ንጽሕናዋ ነው። አሁን ልብ እንበል ክቡር እንግዳ ሲመጣ ክቡር ቤት ያሻዋል። ትልቁ እንግድነት ደግሞ ክርስቶስ ወደ እኛ ባሕርይ የመጣበት ሥጋዌ ነው። ሰማይን ለዘረጋው ምን ዓይነት አዳራሽ ሠርተን እናስተናግደዋለን? ዓለምን በእጁ ለያዘ በምን ጎጆ እንወስነወለን? ብርሃንን ለተጎናጸፈው ምን ዓይነት መጋረጃ እንጋርድለታለን? ምድርን በውኃ ላጸና ምን ዓይነት ምንጣፍ ጉዝጓዝ እናደርግለታለን? ምዑዘ ባሕርይውን ምን አይነት ሽቱ እናጣፍጥለታለን? ትንኝን በምግብ ለማይዘነጋት ምን እንደግስለታለን? ምንም!
እንግዲያው በምን ተቀበልነው? ነውር ነቀፋ የሌለባት ቅድስናን የተጎዘጎዘች፥ ንጽሕና የተደራረባት፥ ምዕዝተ ምግባር ወአሚን፥ ጥዕምተ ስም ወቃል፥ ከከዋክብት የደመቀች፥ ከፀሐይ ያበራች፥ ከሰንፔር የጠራች፥ እንደ ጨረቃ ብርሃኗ ያልጎደለች ይልቁንም ጸጋን የተመላች፥ ጽርሕ ንጽሕት ድንግል ማርያም ተገኘችልን።

"…እግዚአብሔርን ያስተናገድንባት ንጽሕት አዳራሽ ድንግል ማርያም! የሁላችን ቤት ጉድፍ ነበርና ጽድልት በሆነችው  አዳራሽ ተቀበልነው። የሁላችን ቤት መርገም  መልቶት ነበርና ቡርክት ቤት እርሷን አገኘን፥ የሁላችን ቤት ምንም  አልነበረውምና ጸጋን በተመላችው ቤት አሳደርነው። ሁላችን ደካሞች ነበርንና ቤታችን አቅም አልነበረውም፥ ስለዚህም ኃይለ ልዑል ባጸናት ጽንዕት ቤት ኀይል እርሱን ተቀበልነው። ይህንን ነው ሊቁ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ "በፈቃደ አቡሁ ወረደ፥ ኀበ ማርያም ተአንገደ፥ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ- በአባቱ ፈቃድ ወረደ፥ በድንግል ማርያም ተስተናገደ፥ በንጹሕ ድንግልናዋ እግዚአብሔር ተወለደ" ሲል የዘመረው።

"…እግዚአብሔር ያዳነን ሰው ሁኖ ነው። ሰው ለመሆን ደግሞ ከአውሬ ወይም ከእንስሳ ወይም ከመላእክት ሥጋ አላመጣም። ምክንያቱም የፈለገው ሰው መሆን ነውና፡፡(ዕብ፪፥፲፬-፲፯) ሰው ማለት ደግሞ  ቀድሞ ዓርብ የተፈጠረው ንጽሐ ጠባይዕ ያላደፈበት በአርአያ ሥላሴ የከበረው  ፍጥረት መጠሪያ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው ሰው ለመባል የሚበቃው አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረውን የተስማማ ባሕርይ ሲይዝ ነው ማለት ነው። ጌታ ሰው ይሆን ዘንድ በመጣበት ወራት ደግሞ ሁላችንም ሙሉ ሰው መሆናችን ቀርቶ "ሰውስ ክቡር ሲሆን አላወቀም ልብ እንደሌላቸው እንስሳት ሆነ "የተባልንበት አርአያ ሥላሴ ተሰጥቶን የነበርነው ደብዝዘን በእንስሳት የተመሰልንበት፤ ውሉደ ብርሃን የነበርን"በጨለማ የሚኖር ሕዝብ "የተባልንበት የእዳ ዘመን ነው። በዚህ  ጊዜ ከአብራከ አዳም ከማኅፀነ ሔዋን ስታበራ የነበረች ነጭ ዕንቁ ድንግል ማርያም ተገኘችልን። የቀድሞውን ንጹሕ ጠባይዐ ፍጥረቱ ለአዳም የተስማማ የቀድሞውን የአዳምን ንጹሕ ባሕርይ ይዛ ተገኘች። እግዚአብሔርም ሰውን ለማዳን ሲያስብ ሰው መሆን ሽቷልና ሰው ስለተገኘችለት ወደ እርስዋ መጣ። ድንቅ በሚያሰኝ በማይመሰመር ተዋሕዶም ሰው ሆነ።" ፈቂዶ ይፈውስ ትዝምደ ሰብእ ተገምረ በማኅፀነ ድንግል ተኀቢኦ ለኩሉ ኀይል እለ በሰማያት ማኅደር-ባሕርየ ሰብእን ነገደ ሰብእን ሊያድን ሽቶ  ከሰማይ ሠራዊት ተሰውሮ በድንግል ማኀፀን ተወሰነ" እንዳለ መጽሐፈ ኪዳን። ስለዚህ የሰው ወገንን ሁሉ ወክላ እግዚአብሔርን ሰው ያደረገችው ናትና በእውነት ቤዛዊተ ዓለም በእውነት ሰው የመሆናችን መመኪያ የሰው ዘር ወላዲተ አምላክ!

"…ሔዋን ላፈረሰችው ድንግልና በድንግልናዋ ካሰችልን። አጋንንትን ለሰማችበት ጆሮዋ ስብሐተ መላእክትን ሰምታ ካሰችልን። በሲኦል እንኖር ዘንድ የነበርነውን በመቅደስ ኑራ ወደ መቅደስ መለሰችን። ስደተኞች የነበርነውን በስደቷ ወደ ርስት መለሰችን፥ ረኀብተኞች  የነበርነውን በረሃብ በጭንቅ ተሰዳ ልጇን መገበችን፤ በጨለማ የነበርነውን በሌሊት ቁር ከአውሬ ጋር በስደት ኑራ በልጇ ብርሃን አበራችልን። በሐሩረ ጌጋይ እንቃጠል የነበርነውን  በሐሩር እየጠወለገች ተሰዳ  ጠለ ምሕረት ልጇን ሰጠችን። ሁከተ አጋንንትን እንሰማ የነበርን የአይሁድን ጩኸት ስትስማ ኑራ የስብሐተ መላእክት እድምተኞች አደረገችን። በሞት ፍርሐት በርደተ ገሃነም እንርድ የነበርን በልጇ ሞት ስትደነግጥ ኑራ ሠላምን ሰጠችን፣ የአለቀሰችው እንባ የደረሰባት ባሕረ ኀዘን መስጠሜ አበሳ ሆነን። አይይ! ዘመኔም እውቀቴም ያጠረ እኔ የእርስዋን ስቃይ እዘረዝር ዘንድ ወዴት ተችሎኝ!

"…ዛሬ ደግሞ በገነት ያሉትን ነፍሳት ልጇ በመላእክት ካስጎበኛት በኋላ በዚህ ስትደሰት ደግሞ ሲዖል ውስጥ የሚጋዩትን አሳያት። ጌታም ይህን ማሳየቱ…👇④✍✍✍


👆③✍✍✍ …ጠባቂ ለመሆንም ቨርጅንያ ያሉ ደጋፊዎቻቸው ሩጫ ላይ ናቸው፡፡ ዓላማችውና ግባቸው ፓትርያርክ ለመሆንም ነው፡፡ ለመናፍቁ አገዛዝ የሚመች የኦሮሞ ፓትርያርክ ለመሆንነው የሚወራጩት። ዳንኤል ክብረት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማፍረስ የሚመች ሰው በሚፈልግበት በዚህ ዘመን እኔ አለሁ ለማለት ነው ጳጳሱ እንዲህ የሚሆኑት። ያውም በአምላክ እናት በእመቤታችን ላይ።

"…አባ ገብርኤል እንደ ፍንዳታ ነው የሚሰብኩት። የዐውደ ምህረት አያያዛቸው የሊቃውንቱ ዓይደለም። የባሕታውያን ነው። ሲወራጩ፣ ሲውረገረጉ ለሚያያቸው ከበረሀ ሳይሆን ከከተማ ተልኬ ነው ብሎ የሚውረገረግ የከተማ ባሕታዊ ነው የሚመስሉት። ኮርጀዋል። ቀላውጠዋል። ከፓስተሮች የኮረጁትም የመድረክ አያያዝ አለ። ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ጎንበስ ነው የሚለው። ነፋስም አይወዘውዘውም። ረጋ ነው የሚለው። ፍሬ የሌለው ዛፍ ግን ቅጠል ብቻ ስለሆነ ይግለበለባል። እሱን ነገር ነው አሁን አሁን የማየው። የቀደሙት ሊቃነ ጳጳሳት በሁሉም መስክ የተሟሉ ነበሩ። በጾም በጸሎት ምጥጥ ያለ ወዛም ፊት። ግርማ ሞገሳቸው ራሱ አስፈሪ። ሌሊት በሰዓታት በማኅሌቱ፣ በጸሎተ ኪዳኑ፣ በቅዳሴው፣ በሰርክ ጉባኤው ተገኝተው በተገኙበት ሁላ መድረኩን የሚሞሉ ነበሩ። ንግግራቸው በጨው የተቀመመ፣ አንደበት ለዛቸው የሚበላ የሚጠጣ፣ ሲናገሩ ውለው ቢያድሩ የማይሰለቹ ነበሩ። አሁን ግን ይትፍርሂ እም ነው። ኢዩ ጩፋ፣ እስራኤል ዳንሳን የሚያስንቁ ነው የሆኑት። ልብ ብላችሁ እዩአቸው።

"…በመጨረሻም ደስታዬ የሊቃውነተ ቤተ ክርስቲያን ለአባ ደጀኔ ቶላ መልስ ለመስጠት ከእስራታቸው ተፈትተው ግርር ብለው መውጣት ነው። ይሄ አንድ ነገር ነው። ነገር ግን አገዛዙ ይሄን የሊቃውንቱን መነሣት ለጥናት ነው የሚጠቀምበት። ለምሳሌ አቢይ አሕመድ እንደመጣ የሚዲያ ነፃነት ብሎ ሚዲያውን ልቅ አደረገው። እስላምና ጴንጤ ጋዜጠኞችን ቃለመጠይቅ ጠያቂ አድርጎ በተናቸው። እነ ቤተልሄም ታፈሰ ወዘተ አሳድደው ጠያቂ ሆኑ። ሕዝቤም አገኘሁ ብሎ ሰፍ ብሎ በነፃነት ይበረጠቅ ጀመር። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ግን የሁሉንም አቋም እየፈተሸ የሚገደለውን ገደለ፣ የሚታሰረውን አሰረ፣ ብላክ ሜል የተደረገውን በሙሉ ደግሞ ገሚሱን ሳይለንት ሙድ ላይ አስቀመጠው፣ ገሚሱን የራሱ ባሪያ አድርጎ አስቀመጠው። እናም እንዲህ አድርጎ ነበር በመጨረሻ ሚዲያዎቹም፣ ጋዜጠኞቹም ሥራቸውን ሲጨርሱ የዘጋቸው። የቆለፈባቸው። ምንአልባት አሁን ምርጫ ተብዬው የፉገራ መድረክ ሲቃረብ እንደገና ፈትቶ ይለቃቸዋል ብዬ እገምታለሁ። እናም ሚዲያዎቹ አቋም መገምገሚያ ነበሩ።

"…አሁንም ይሄም ከዚያ አያልፍም ብዬ ነው የምገምተው። አባ ገብርኤል ይናገር፣ ከዚያ ለእሱ መልስ የሚሰጠው እንደተለመደው ዘመድኩን በቀለና ኢትዮ ቤተሰብ ናቸው ወይስ ማን ማን ናቸው የሚመጡት ተብሎ ለግምገማም እንዲያመች ነው ጳጳሱ እንዲያጓሩ ያደረጓቸው። በመሆኑም እንደ ድሮው እኔ ብቻዬን አልጮህኩም። ወይም ኢትዮ ቤተሰብ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው ብቻ አልጮኸውም። ኦሮሞ ነው፣ ጳጳሱ ዘሩ ሥልጣን ላይ ነው ሳይሉ፣ ሳይፈሩ፣ ሳይሳሱ፣ ሳይሳቀቁ በድፍረት ለሊቀ ጳጳሱ ምላሽ የሰጡት ሊቃውንት ብዛት ታይቶም፣ ተሰምቶም አያውቅ። ጭራሽ ቤዛነት ተተንትኖ አስደመመን፣ የማናውቀውን ማወቅ ጀመርን። እኔ በሕይወቴ እንደ ሰሞኑ ተመስጬ የሊቃውንቱን ምላሽ አንብቤም ዐላውቅ። መልሱ ፖለቲካ ስላልሆነ፣ ዕወቀት ላይ ተመርኩዞ የሚሰጥ ምላሽ ስለሆነ እጅግ አስደማሚ ነው። እነ ዳንኤል ክብረት ስንቱን አጥቁረው ይዘልቁታል። ምላሽ የሰጡት ከጥቂቶች በቀር በአብዛኛው ስለተሰለፉ ለይቶ ለመምታት አያስችልም። የሆነው ሆኖ አባ ደጀኔ እነኳንም ተናገሩ። እንኳንም ሳቱ፣ እሳቸው ባይስቱ እንዲህ ያለ ጮማ ዕውቀት ከወዴት እናገኝ ነበር?

"…ዶር መስከረም ለቺሳም እንዲህ አለች።

"…ቤዛዊተ ዓለም፡ በነፍሷ ሰይፍ ያለፈው፡ ስለሰው ልጆች ድኅነት ነው። ለእመቤታችን የሚሰጡ የማዕረግ ስሞች በሙሉ፡ ተነጻጻሪነታቸው፡ ከፈጣሪ ጋር እንጂ፡ ከፍጡራን ጋር አይደለም።

እሱ "አምላክ ወሰብ".... እሷ "ድንግል ወእም"
እሱ "ዳግማዊ አዳም" .... እሷ "ዳግማዊት ሔዋን"
እሱ "የዓለም ብርሃን".... እሷ "እመብርሃን"
እሱ "አምላክ".... እሷ "ወላዲተ አምላክ"
እሱ "ቅዱሰ ቅዱሳን".... እሷ "ቅድስተ ቅዱሳን"
እሱ "ንጉሠ ሰማይ ወምድር".... እሷ "ንግሥተ ሰማይ ወምድር"
እሱ "ቤዛ ኩሉ ዓለም".... እሷ "ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም"
እሱ "መለኮት".... እሷ "ማኅደረ መለኮት"
እሱ "ጌታችን"...እሷ "እመቤታችን"
ወዘተ...

ለርሷ የተሰጡት እነዚህን መሰል ስሞች በሙሉ፡ ለሌሎች ፍጡራን አልተሰጡም። የርሷ የብቻዋ ስሞች ናቸው። የተቀዱትም፡ ከልጇ ልዩ ማንነት እንጂ፡ ከሌሎች ፍጡራን የጋራ ማንነት አይደለም። ምክንያቱም፡ እመቤታችን የተመረጠችው፡ የአምላክን ማንነት ለማሳየት እንጂ፡ የፍጡራንን ማንነት ለማሳየት አይደለም። "የእመቤታችን መልኳ የአምላክን መልክ ይመስላል" የተባለው ለዚያ ነው።

ስለዚህ፦ "እመቤታችን ቤዛ አትባልም፤ ምክንያቱም ፍጡር ቤዛ አይኾንም" የሚለው አባባል፡ የመጀመሪያው ስኅተቱ፡ እሷንም ኾነ የርሷን ቤዛነት፡ ከማንኛውም ፍጡር ጋር ለማነጻጸር መሞከሩ ነው። "መልዕልተ ፍጡራን" ማለትም "ከፍጡራን ኹሉ በላይ" (ከፈጣሪ ብቻ በታች) መኾኗን የዘነጋ አባባል ነው። እሷ ስለሰው ልጆች ድኅነት የከፈለችው ዋጋ፥ ማለትም፡ "በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል" ያስባላት በልጇ ምክንያት የተቀበለችው መሪር ኀዘንና መከራ ኹሉ፡  ከማንም የተለየ ቤዛነትን ለመክፈሏ ማረጋገጫ ነው። ምክንያቱም፡ ጌታን ለመጽነስ የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት "ይኹንልኝ" ብላ የተቀበለችው፡ ልጇ ተወልዶ ለዓለሙ ቤዛ እንደሚኾን ስለተነገራትና በዚያ ስለተስማማች እንጂ፡ እንደኛ የሥጋ ፈቃዷን ለመፈጸም፥ ወይም፡ አሳድጋ ኩላ ልትድረውና ወግ ማዕረግ ልታይበት፥ ወይም እንዲላላካትና እንዲያገለግላት፥ ወይም አንዳች የመካንነት ስድብን እንዲያርቅላት፥ ወይም ስታረጅ እንዲጦራት ብላ አልወለደችውም። እናትነቷ የተለየ ስለኾነ፡ ቤዛነቷም የተለየ ነው። ይኽን ያላወቀና ያላመነ ሰው፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ሊባል ፈጽሞ አይችልም።(በሰነፎች ንግግር ግር ላላችሁ የተጻፈ ነው እንጂ ለዐውቆ አበዶች አይደለም።) ብላ የጦመረችው ጦማር እንዴት አንጀቴን እንዳራሰው ልገልጽላችሁ አልችልም። ስለ ቤዛ ትርጉም የማያውቅ ጳጳስ ሆኖ ሲሾም እግዚአብሔር ያሳያችሁ። የኔታ ያሬድም እንዳሉት "…ጉባኤ ቤት ገብቶ በእመቤታችን ስም ለምኖ የተማረና ያልተማረ አሁን ለየ። ክብር ለቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ኲሉ ዓለም።

"…መጋቤ ብሉይ ወሀዲስ አባ ገብረ ኪዳን ነሐሴ / 17 2012 ዓም ካስተማሩት የቤዛነት ትምህርት አንድ ልጨምርላችሁና ርእሰ አንቀጻችንን ለዛሬ እናብቃ። "…ቤዛ መሆን ማለት መዋጀት ፣ነጻ ማውጣት፣ መታደግ  እዳ መክፈል ፣መለወጥ ማለት ነው።፡ለምሳሌ ጠበቃ ይከራከራል ነገር ግን  ሲከራከርለት የቆየው ሰው ላይ ፍርድ ቢፈረድበት ጠበቃው አቅሙ እስከፈቀደ ድረስ ይሟግታል እንጆ እስራቱን  እኔ ልታሰር፥እዳውን እኔ ልክፈል፥የሚመጣውን ሁሉ በእኔ ጣሉት አይልም። ቤዛ ማለት ግን ስለሚቤዠው አካል መተካት ነው። ቤዛነትም ለሚቤዡት አካል አንደኛ የሌለውን ነገር በመክፈል፤ ሁለተኛ በዚያ ሰው ላይ የሚደርሰውን መከራ ተቀብሎ ከመከራ ማውጣት ነው።

"…ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስንመለስ የዓለሙ ሁሉ ቤዛዊት ናት። ዓለም የተባለው በላይ መላእክትን በምድር ደቂቀ…👇③✍✍✍


👆② ✍✍✍ …የጠላት ኃይል ኅብረት፣ ቅንጅት አንድነት ፈጥሮ፣ ተሃድሶው፣ የወሃቢይ እስላሙ፣ ጴንጤው አንድ ላይ አብሮ እንዳይቆም ነው የተደረገው። እነ እፎይ እስላሙን፣ እነ ዘማርያም፣ እነ ቀሲስ ዲበኩሉ የእነ አክሊለን፣ የመናፍቁን ገትረው ይዘው ነው ልክ ያገቡልን። አንዱ እፎይ ሲገርመን ሃምሳና መቶ እፎዮች ከወንድም፣ ከሴትም ብቅብቅ ብለው እያስደመሙን መጥተዋል። የመናፍቃን መነሣት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ያፈራል። ያስነሣልም። ብዙ መጻሕፍት ይጻፋሉ፣ ብዙ ስብከት ይሰበካል። የካቶሊካዊው ዶክተር አየለ መነሣት ሰው ሆይ የተሰኘውን የመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬን፣ መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና የሚለውን የሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌውን፣ የጀርመናዊው ቦንኬ መምጣት "እምነት የለየንን መቃብር አንድ አያደርገንም ወዘተ የመሳሰሉ ዘመን ተሻጋሪ መጻሕፍት እንዲጻፉ ነው በር የከፈተው። እናም የመናፍቃን መነሣትም ለቤተ ክርስቲያን መልካም ዕድል ነው ይዞ የሚመጣው። ምንፍቅና እብድ ውሻ ነው። ከጥልቅ ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ፣ ንቁ የሚያደርግ ምርጥ እብድ ውሻ።

"…የአሕዛብም ሰይፍ ይዞ መነሣት አዳዲስ ሰማእታትን ነው የሚያስገኘው። እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ እነ ቅዱስ መርቆሬዎስ፣ እነ ቅድስት አርሴማ የተገኙት ከሰይፍ፣ ከመንኮራኩር ውስጥ ነው። ሰማእታት የቤተ ክርስቲያን ምርጥ ዘር ናቸው እንዲል ሊቁ። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬም የተገኙት ከመድፍና ከመትረየስ ፊት ቆመው በጽናት ተሰይፈው አልፈው ነው። ሞትማ አይቀሬ ነው። ብዙ ጳጳሳት ሞተዋል፣ ነገም ይሞታሉ። ስማቸው ከመቃብር በላይ የሚቆየው ግን የጥቂት ሰማእታት ሊቃነ ጳጳሳት ስም ነው። የዘመኑን ቲክቶክም በአግባቡ የሚጠቀሙበት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም እየተሳተፉበት ስለሆነ መናፍቁም፣ አሕዛቡም የትም አይደርስም። በመጨረሻም…

"…ደጀኔ ቶላ
ሣህለማርያም ቶላ vs ዲን ምሕረት መላኩ
አቡነ ገብርኤል

"…ማዕረገ ጵጵስና በዕውቀት፣ በእምነት፣ በሃይማኖት ሚዛን ተሰፍሮ፣ ተቆጥሮ፣ ተለክቶም የሚሰጥ ሹመት መሆኑ ከቀረ ትንሽ ዋል አደር፣ ከረምረም፣ ሰንበትበትም ብሏል። እንደቀደሙቱ መነኮሳት አይደለም ለጵጵስና፣ ለአበምኔትነት ተመርጠሃል ሲባል እልም፣ ብን ብዬ ነው የምጠፋው፣ አይሆንልኝም፣ አልችልም ብሎ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ መነኮስ ከቀረ ስንትና ስንት ዘመን አልፎታል። በዘመድ፣ በጉቦ፣ በፓርቲ ምደባ ለመሾም፣ በዘር ኮታ ለመመደብ የሚራወጥ፣ እኔ ካልተሾምኩ ምድር ትገልበጥ ብሎ የተቃውሞ ሰልፍ የሚያስወጣ፣ እንደ ሻሸመኔ በመሰዊያው ፊት ምእመናንን በመትረየስ የሚያስጨፈጭፍ አለሌ ነውረኛ፣ አረመኔ መነኮስ ነው የሞላው። ነጋዴ፣ አመንዝራ፣ የ40 ሚልዮን መኪና በ0 ሺ ብር ደሞዝ የሚነዳ መነኮስ ነው ተፈትቶ የተለቀቀብን። ውዳሴ ማርያም፣ መልክአ ማርያም፣ መልክአ ኢየሱስ በቃሉ መዝለቅ ቀርቶ አጭሯን ጸሎተ ሃይማኖትን በቃሉ የማይዘልቅ፣ ቅዳሴ የማይቀድስ፣ ሰዓታት ማኅሌት የማይቆም ጳጳስ መሾም ከተጀመረም ቆየ። "ይትፍርህ እም" እንዲል አቡነ ሩፋኤል።

"…ፍኖተ ጽድቅ የሚባለው ማኅበር ሲጀመር የምንፍቅናና የመናፍቃን ማፍሪያ ጎሬ ሆኖ በመገኘቱ በብዙዎች ርብርብ በስንት ፍልሚያ የማኅበሩ መሥራች የሮቶና የሮዳስ ቀለም ባለቤት አቶ ፀጋዬም በግልጽ በአደባባይ ወጥቶ በሕዝብ ፊት ሊቀጳጳሱ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ባሉበት እነ ምህረተአብ በጠሩት ጉባኤ ላይ በቦሌ መድኃኔዓለም ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተንበርክኮ እያለቀሰ ስህተቱንም አምኖ ይቅርታም ጠይቆ ተመልሻለሁ በማለቱ ምክንያት ከተመለሰማ መልካም ብለን ፍልሚያችንንም አቁመን የተኩስ ስምምነት በማድረግ ፀጋዬ መመለሱን በደስታ ተቀብለን ነገሮችን አለዝበን ማለፋችንም ይታወሳል። ነገር ግን አሁን እየሆነ ያለው ነገር ሲታይ "ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ" ዓይነት ነገር ነው እየሆነ ያለው። ባለሀብቶ የቤተ ክርስቲያኒቱን ኃላፊዎች በሙሉ በገንዘቡ አፍኖ መያዙም እየታየ ነው። ማኅበረ ቅዱሳንና ቤተ ክህነቱም የሚዲያ ክፍላቸው በዚሁ ባለፀጋ መገንባቱ ማኅበሩም፣ ቤተ ክህነቱም አፋቸው እንዲለጎም መደረጉ ነው የሚነገረው። የሆነው ሆኖም ግን አሁን ጂኒው ከጠርሙሱ ወጥቷል። አለቀ።

"…በዚህ በፀጋዬ አዳራሽ ውስጥ በዲያቆናት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ መምህራን ነን ባዮች ይዘራ የነበረው ምንፍቅና አሁን ደረጃው ከፍ ብሎ በጵጵስና ማዕረግ ወደሚጠሩ ሰዎች ተሸጋግሯል። ጵጵስና ሹመት፣ ሥልጣን፣ ክብር ሊያስገኝ ይችላል። ጵጵስና ዕውቀት ሊያስገኝ፣ ሊያሰጥም ግን አይችልም። ያውም በዚህ ዘመን። ለዚህ ማሳያው ደግሞ ዲን ምሕረት የተባለ ታዳጊ ወጣት ሰሞኑን በሀገረ አሜሪካ በ12 ደቂቃ ክርክርና ሙግት፣ ጥያቄና መልስም ሁለት አባትና ልጅ የሆኑ የፕሮቴስታንት ፓስተሮችን አፍ አዘግቶ፣ ዱዳም አድርጎ በቲክቶክ ተሰራጭቶ ያየነው ቪድዮ ነው። ዓለም ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓይኑን እንዲጥል፣ ፊቱንም እንዲያዞር፣ እንዲጎርፍም እና ሲያደርግም ያየነው አሁን በቅርቡ ነው። እነ አባ ወልደ ትንሣኤ አሜሪካ ተቀምጠው፣ በዚያው አርጅተው፣ በስብከቶቻቸው ሁሉ የሀበሻ ጴንጤና ፓስተር ሲያስደምሙ ኖረው ባየንበት አይናችን፣ አንድም ነጭ፣ አንድም የነጭ ጴንጤ በእነ አባ ወልደ ትንሣኤ ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ዐወቅኩ፣ ወደድኩ የሚል ሳንሰማ፣ የሀበሻ ፓስተሮች ጭራሽ "በኦርቶዶክስ ሆነው ጌታ የበራላቸው፣ የገባቸው" ተብለው ሲሞካሹ ነው ያየነው። ይሄ በእውነት አሳፋሪ ነው። የኦርቶዶክስ ጳጳስ ሆኖ በጴንጤ መወደድ ምን የሚሉት ተአብ እንደሆነ ፈጣሪ ይወቅ። ወይ ጠቅልለው ቆቡን አስቀምጠው ቢሄዱ እኮ ግልግል ነበር።

"…የዚያ ቅጥያ ነው አሁን ያየነው። አባ ገብርኤልም ከአሜሪካ ይዘው የመጡት ይሄንኑ ኑፋቄ ነው። ከመኖሪያ ፈቃዱ ጋር ውል የገቡ ነው የሚመስሉት አባ ገብርኤል። ዲያቆን ምሕረትን ባየንበት ዓይናችን ነው አሁን ደግሞ ቀላሉን በጣም ቀላሉን ስለ "ቤዛነት" ትርጉም ሳያውቅ፣ ሳይረዳም፣ በምርጥ፣ ንፁሕ ኦሮሞ በሚል መስፈርት በኦሮሞነቱ በዘሩ ብቻ ጳጳስ የሆነው ደጀኔ ቶላ፣ ይቅርታ ሳህለማርያም ቶላ፣ ይቅርታ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን ሲወራጩያየናቸው። ያውም በተናገረው ነገር የፀጋዬ ፋብሪካ ሠራተኞችና በግድ ነጠላ ለብሰው እንዲቀመጡ የተገደዱት ምእመናን ሲደነግጡ "አትደንግጡ" እያለ የፕሮቴስታንቱን ዓለም ጮቤ ሲያስረግጥ ያየነው። በተለይ አምልኮ የሚባለው የፕሮቴስታንቶች ዩቲዩብማ እናመሰግናለን አባ ሁላ ብሎ ነው የፖሰተው። ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሀዲስን በውድድር ሀ ገደሉን ብፁዕ አቡነ ሩፋኤልን "ይትፍርህ እም"ን ያለተወዳዳሪ በጋምቤላ ክልል ደብዳቤ አሳልፈህ ጳጳስ ስታደርግ ነው ነገር ዓለሙ ሁሉ የሚያበቃው። እኔ አስቀድሜ ተናግሬአለሁ ሰካራም፣ መናፍቅ፣ ወላድ ጳጳስ አይሹም ብዬም ጮሄአለሁ። ብቻውን አንድ ጠርሙስ ውስኪ የሚጨርስ ሰው ምንስ ቢዘባርቅ ይፈረድበታልን? በፍጹም። በዚህ ቢያቆም፣ ቢያበቃ መልካም ነው። እነደጁ ገና አያሌ ተአምራት ነው የሚያሳዩን። ገና ምኑ ተነክቶ። መችስ ጀመረና። የሳዊሮስ አቋም አልጨበጥ ማለት፣ የአቡነ ማንትስ በምኒልክ ጉዳይ በኦህዴድ ኦነግ ዘንድ ቂም መቋጠር በአቡነ ማትያስ ምትክ ከኦሮሞ ለሚዘጋጀው ፓትርያርክ ብቁ ሆኖ ለመገኘት እንዲህ በግልፅ አለሌ መናፍቅ ሆኖ መገለጥ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። አባ ደጀኔ ቶላ ቀጣዩ ፓትርያርክ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ ይህንንም ራሳቸው ራት ጋብዘዋቸው የነበሩ ሰዎች ለእኔ ለራሴ ነግረውኛል፡፡ በአሜሪካም የሟቹ አቡነ ገብርኤል የልደታ ቤተ ክርስቲያንም የበላይ…👇② ✍✍✍


"ርእሰ አንቀጽ"

"…በደጁ በኩል በደጀኔ ቶላ፣ በሳሕለ ማርያም ቶላ፣ ወይም በምርጡ ንፁህ ኦሮሞ ተብሎ በተሾሙት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል በኩል ይመጣሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር እንጂ በሀገረ አማሪካ የሚኖረው ኢትዮጵያዊው ዲያቆን ምሕረት መላኩ ከአባትና ልጅ የመናፍቃን ፓስተሮቹ ጋር ክርክር አድርጎ በዚያች አጭር 12 ደቂቃ ውስጥ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በዓለሙ ሁሉ በክብር ከገለጣት ጌዜ በኋላ በተደራጀ እና በተጠና መልኩ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ፀያፍ ዘመቻ እንደተነሣ ዝም ብዬ እታዘብ ነበር። ነገር ግን ይሄን ዘመቻ ምርጥና ንፁሕ ዘር ተብሎ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተመረጠ የኦሮሞ ጳጳስ በዚህ ፍጥነትም ይቀላቀለዋል ብዬም አልገመትኩም ነበር።

"…ደጀኔ፣ አባ ሳህለማርያም ቶላ ወይም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሟቹን የብፁዕ አቡነ ገብርኤልን ስም ነው ተረክበው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያስቀጥሉ የተሾሙት። ሟቹ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እንዲሁ በሹመታቸው ዘመን የመጀመሪያ ዓመታት ውስጥ ሃይማኖት ክደው፣ መንፍቀው በመገኘታቸው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዟቸው፣ ማእረጋቸውም፣ ክህነታቸውም ተገፍፎ፣ ከብፁዕ አቡነ ገብርኤልነት ወደ አቶ ኢያሱነት ተቀይረው ወርደው ኋላ ላይ ነው ይቅርታ ጠይቀው፣ ቀኖናም ተሰጥቷቸው ወደ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልነት የተመለሱት። አሁንም ይህኛው ምርጡ፣ ንፁሕ ኦሮሞ ተብለው የተሾሙት ሳህለ ማርያም ቶላ ወይም አቡነ ገብርኤል የሌለ አፍልተው ሳያቸው በዚህ ፍጥነት ያደርጉታል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር እንጂ በብልፅግናው አገዛዝ "ለፓትርያርክነት ዕጩ ተደርገው ከተያዙት አንደኛው እንደሆኑ ስለሚነገር አገዛዙን የሚያስደስት ነገር መሥራታቸው እንደሚጠበቅ ተጠባቂ ነበር በእኔ ዘንድ። ሳስበው፣ ተደጋግሞም ሳየው አቡነ ገብርኤል መባል በራሱ በኑፋቄ ያስፈትናል ማለት ነው? እንዴ ብዬም አስባለሁ።

"…በዚህ ዘመን ሕዝብ ከማይጠፋበት በተለይ ወጣቱ ትውልድ በሚርመሰመስበት በቲክቶኩ መንደር ያለው ትንቅንቅ ገራሚ ነው። ዕድሜ ለእፎይ እና ለጓደኞቹ ይስጣቸውና በቲክቶክ መንደር የሌለ አፍልቶ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ እንደ ጉድ ሲያቀረሽ የነበረው የወሃቢይ እስላሙ ቡድን አደብ ገዝቶ ሲተነፍስም ያየነው በዚህ ዘመን ነው። የእኛን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን መሳደብ በሕገ መንግሥቱ የተፈቀደ ይመስል አፉን ሲከፍት ይውል የነበረው የወሃቢይ እስላም ከዚያው ከቁርዓራኑና ከሀዲሱ እየተጠቀሰላቸው የኢየሱስን ጌትነት፣ አምላክነት፣ ያለወንድ ዘር መወለዱን እያነበቡ በነቢያቸው እንዲያፍሩ እንዲፈረጥጡ የሚያደርጉ እሳት የሆኑ ትውልዶች ተገልጠው ያየነውም አሁን ነው። ታቦትን ጣኦት ሲል የነበረው የወሃቢይ እስላም በሙሉ ስለ ጥቁሩ ድንጋይ፣ በሴት ብልት ቅርዝ ተዘጋጅቶ ዘይት የተቀባ ድንጋይ ለመሳም ስለሚጋደለው ስለ እሱ ሲነገረው መግቢያ አጥቶ ሲጨነቅ ያየነውም አሁን ነው። አዎ ሶሻል ሚዲያውን ንቀን ትተን የነበርነው በሚገባ ተቆጣጥረን ማጥቃት የጀመርነውም አሁን ነው። እሱም ቢሆን ሊበላሽ ስለሚችል በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባዋል።

"…የቲክቶኩ አናብስት የነበሩት የወሃቢይ እስላም ኡስታዞች ለክርክር፣ ለሙግት፣ ለውይይት ቢጠሩም በአካል ከመቅረብ ይልቅ ወደ ፌደራል ፖሊስ በመሄድ ነቢያችን ተነካ ብለው ወደ ክስ ሲያመሩም ያየነው የሰማነው አሁን ነው። ከ40 በላይ መጻሕፍት ጽፈው፣ ሲዲ ቪሲዲ አዘጋጅተው በንጽጽር ስም ዋይዋይ ሲሉ ሲያቀረሹብን የነበሩ የወሃቢይ እስላሞች አቅም ሲያጡ የፈጢራና የኢድ ሶላት፣ የአርብ ጁምአ ላይ "እፎይ ለፍርድ ይቅረብልን" በማለት ወደተለመደው ሁከትና ግርግር ገብተው ያየናቸውም አሁን በቅርብ ነው። ወሃቢይ ባይነሣ ኖሮ፣ ተነሥቶም ክርክር ግጠሙኝ ባይል ኖሮ እፎይ የሚባል ሰው ከየት ዕናውቅ ነበር? እፎይን ያስገኘው የወሃቢያ ለንፅፅር ብሎ ያለ አቅሙ መነሣት ነው። ከቤተ ክህነት ከሊቃውንት ጉባኤ ያልሆነ፣ ከመንፋሳዊም፣ ከአብነት ትምህርት ቤትም ያልሆነ፣ በቃ ሰባኪ ነው፣ መምህር ዲያቆን ያልተባለ ሰው አስነሥቶ ድራሽ አባታቸውን ነው ያጠፋቸው እግዚአብሔር።

"…ጎጋው ጴንጤ ለዘመናት እስላሙን ፈርቶ ሲያቀረሽ የኖረውም ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ ነበር። እነሱ ሳይቀሩ እስኪደመሙብን ድረስ ነበር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእነ እፎይ ላይ አድሮ ሥራውን የሠራው። በእነ እፎይ መነሣት ከወሃቢይ እስላሙ እኩል ጓ ብሎ ተነሥቶብን የነበረው በምሥራቅ ጎጃም በቆጋ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ መርጦ ያስቀመጠው የቅባቴዎቹ ቡድን ከወሎው የወሃቢያ እስላም ቡድን ጋር በመጣመር ነበር ወደ ቲክቶክ መንደር በጋለሞታዋ አዝማሪት አልማዝ ባለጭራዋ እየተመራ ከቺሳ ብሎ የነበረው። ቅባቴው ሞጣ ቀራኒዮም ሳይቀር ጓ ብሎ የነበረው ከእነ እፎይ መነሣት በኋላ ዲያቆን ምህረት በአማሪካ መናፍቃኑን በዝረራ ካጋደመ ወዲህ በተለይ ከሆሳዕና ዕለት ጀምሮ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮና በአማኞቿ ላይ ሁሉ እንዲሁ ሲያስታውክብን እያየሁ ስታዘብ ነበር የከረምኩት። በእውነት ይሄ ነው የማይባል ከፍተኛ ስድብና ዘለፋ ነበር ሲዥጎደጎድብን የሰነበተው።

"…በሌላም በኩል ቀደም ብለው ፈልተው የፈሰሱብን ዋነኛውና አፍቃሬ ግብፅ ሆኖ ተደራጅቶ የተለቀቀብን የእነ አክሊለ አኬ እና የእነ ጋዲሳ ቡድንም እንደ አዲስ ነበር "ቤተ ክርስቲያን ተሳሳች ነች" የሚል አጀንዳ ይዞ ብቅ ያለው። ይሄ አደገኛ ቡድን ቆዳውን እየቀያየረ ቢመጣም አንደዜ ቅስሙና ጅስሙም ስለፈሰሰ ከመሽለጥለጥ በቀር አቅም ባይኖረውም ነገር ግን ለቤተ ክርስቲያን አጀንዳ እየቀፈቀፈ መነሣቱ አልቀረም። እንዲያውም በዲያቆን ዳዊት ቤት በነበረው ክርክር ላይ ለእነ አክሊሉና ለእነ ጋዲሳ ቡድን ሞጋቾች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እንዲህ በማለት ነበር የግብፅ ቅጥረኞቹ ሲመልስ የተደመጡት።

ጥያቄ፦ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሳሳች ነች?
መልስ፦ አዎ
ጥያቄ፦ የኤርትራ ቤተክርስቲያን ተሳሳች ነች?
መልስ፦ አዎ
ጥያቄ፦ የኢትዮጵያና የኤርትራ አብያተክርስቲያናት በጋራ ይሳሳታሉ?
መልስ፦ አዎ

ጥያቄ፦ የግብጽ ቤተክርስቲያን ተሳሳች ነች?
መልስ፦ እሱን አላውቅም።

"…የግብፅን አያውቁም። የሚያስቀድሱት ግብፅ ቤተ ክርስቲያን ነው። የሚያስጠምቁት፣ የሚቆርቡትም ግብፅ ቤተ ክርስቲያን ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን እያዋረደ የግብፅን የሚክብ ፀረ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሆነ መናፍቅ ግሩፕ ነው የተፈጠረው። የሆነው ሆኖም ግን እነዚህንም እየተከታተለ ፍሬን የሚያሲዝ ኃይልም የዚያኑ ያህል ነው የተፈጠረው። ይሄ በሚገባ የተጠና ፀረ ኦርቶዶክሳዊ ዘመቻ ነው። ኢትዮጵያ ተቀምጦ ግብፅን የሚናፍቅ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ተሳሳች ናት ሲል ሳያፍር የግብጽን ቤተ ክርስቲያን ፍጽምት የሚያደርግ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ዝም ብሎ አይነሣም። በኦርቶዶክሳውያኑ ላይ ሳቁባቸው፣ አንቋሿቸው፣ በየቲክቶኩ ባህልና መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸውን ዝለፉ፣ ጠይቁ፣ ፋራዎች፣ ማይማን፣ ዛሬም እዚያ ላይ ናችሁ? እያላችሁ ስደቧቸው ተብለው በሥርዓቱ የተደራጁ ኃይሎች ናቸው ይህን ሲያደርጉ የከረሙት። ነገር ኦርቶዶክሳውያኑ አልተቻሉም። እነ ቀሲስ ዲበኩሉ፣ እነ ቀሲስ ቴዎድሮስ፣ እነ ዘማርያምን የመሳሰሉ ትንታጎች የቲክቶኩን ፕላትፎርም ወጥረው ይዘው አላላውስ ብለው ቀፍድደው ነው የያዙአቸው።

"…ደግነቱ ከላይ እንደጻፍኩላችሁ በዚያው መጠን የወሃቢ እስላሙን ዱዳ፣ ደንቆሮ፣ ሯጭ፣ አምላጭ፣ ፈርጣጭ የሚያደርጉ ልጆችም ተፈጥረው ልክ ማስግባት በመቻላቸው ከውስጥም፣ ከውጭም…👇① ✍✍✍



Показано 15 последних публикаций.