Репост из: Bahiru Teka
👉 በሙስሊምነትህ አትፈር
ወንድሜ አላህ በባሮቹ ላይ ከዋለው ፀጋ ወደር የሌለው የእስልምና ፀጋ ነው ። ይህን የሚያውቀው ከኩፍር ፅልመት ወጥቶ ወደ ኢስላም ብርሃን ተሸጋግሮ በአይነ ህሌናው ያለፈውን ፅልመት እያየ የሰራ አካላቱ ከሚወረው አስፈሪ ጭንቀት ራሱን በኢስላም ብርሃን ላይ የሚያገኝ ሰው ነው ። በዚህን ጊዜ የትኞቹም ቃላቶች ለአላህ የሚገባውን ምስጋና ለማቅረብ አቅም ያጥራቸውና አልሐምዱ ሊላህ የሚለው አላህ ራሱን ያመሰገነበት ቃልን ተጠቅሞ እሱን ሲያመሰግን ነው በፍስሓ የሚሞላው ።
የኩፍርን ጨለማ ያላየ የኢስላምን ብርሃን ምንነት ለመረዳት ቀላል አይሆንለትም ። በጣም የሚገርመው ግን በዚህ ኢስላም የሚያፍር ማየት ነው ። ወንድሜ በየትኛውም የእውቀትና ክህሎት ላይ ብትሆን ሙስሊም ሆነህ ነው ወደዛ ደረጃ የደረስከው ። ታዲያ ለምን ታፍራለህ እስኪ ራስህን ጠይቅ መልሱን የምታውቀው አይመስለኝም ። ያንተ በእስልምናህ ማፈር ምክንያት ከየት እንደመጣ በኔ እይታ ምን እንደሆነ ልንገርህ ። የአፄአዊያኑ ተፅኖ ውጤት ነው ። አፄዎቹ የተማረ ሙስሊም እንዳይኖር ፣ በየትኛውም የመንግስት ስልጣን ውስጥ እንዳይሳተፍ ፣ ራሱን እንደሁለተኛ ዜጋ እያየ በእነርሱ መልካም ፈቃድ እየኖረ መሆኑን እንዲያስብ ማድረጋቸው ነው ። ሙስሊም ተማሪ ፣ ሙስሊም የቢሮ ሰራተኛ ፣ ሙስሊም አስተማሪ ፣ ሙስሊም የጦር መሪ ፣ ሙስሊም ሐኪም እንዳይታሰብ አድርገው ስለነበር ከላይ በተጠቀሱ ዘርፎች ላይ አልሐምዱ ሊላህና አሰላሙ ዐለይኩም የሚል አልነበረም ። የእነዚህ አካላት የኩፍር አስተሳሰብ ፅልመት ከተገፈፈ በኋላም የስነልቦና ጫናው ቶሎ አለቀቀም ። እስከ ዛሬም እያየነው ነው ። ብዙ በመንግስት መስሪያ ቤት ላይ በተለያየ እርከን ያሉ ሙስሊሞች አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ሲባሉ ወዐለይኩሙ ሰላም ለማለት ያፍራሉ ።‼ እንዴት ናችሁ ሲባሉ እግዚአብሄ ይመስገን ወይም በድፍኑ ምስጋና ይገባው ይላሉ ። !!! ትንሽ ደህና የሆኑት ስለወደፊት ሲያወሩ ፈጣሪ ካለ ይላሉ ። ይህ በአብዛኛ አ/አ ላይና አማራ ክልል ላይ ይስተዋላል ። ይሁን እንጂ ሌላ ቦታ የለም ማለት አይደለም ።
በፖለቲካው አለም ታዋቂነትን ያገኙ ሙስሊሞችም ቢሆን አንገታቸውን ቀና አድርገው በእስልምናቸው ሳያፍሩ አልሐምዱሊላህ ፣ አላህ ካለ ሲሉ አይሰማም ። የዚህ አይነቱ የሙስሊሞች የስነልቦና ልሽቀት በጣም ያሳምማል ። ሰው እንዴት በሙስሊምነቱ ያፍራል ? በእውቀትም ፣ በሀብትም ፣ የትም ቢደርሱ የአላህ ፀጋ ነው ። አንድ ሙስሊም አላህ በለገሰው ፀጋ እንዴት ሌላውን ያወድሳል ? እንዴት ሌላውን ያመሰግናል ? እንዴት እሱን ለማመስገን ያፍራል ?
ለማንኛውም አንተ አላህ የእስልምና ፀጋ ያጎናፀፈህ ወንድሜ ሆይ ራስህ ላይ ያለውን ዘውድ ተመልከተው !!! ለዚህ የሚረዳህ ኢስላምን ማወቅና መረዳት ነውና ሲሉ ሰማሁ ብዬ እንዳይሆንብህና ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከምትፀፀት ዛሬ ከተጫነብህ የጘፍላ ሸክም ተላቀቅ ።
አንተ ሙስሊም መሆኔን ማወቅ የለበትም ብለህ የምታፍረው አካል ማለት ካልነበረበት ያስገኘውን አላህን የካደ የዚህን ረቂቅ ፍጥረተ ዐለም ፈጣሪን ያስተባበለ ከህሊናው ጋር የተጣለ ነው ። እሱ ነበር እንጂ በአላህ ላይ በመካዱ ማፈር የነበረበት እንዴት አንተ ታፍራለህ ? ቶሎ ካልተመለስክና ራስህን መሆን ካልቻልክ ጎሳም ፣ ሀብትም ፣ ዘመድም ፣ ስልጣንም በማይጠቅምበትና ከሀዲ ሁሉ ምነው አፈር ሆኜ በቀረሁ ብሎ በፀፀት አካሉን በሚበላበት ቀን አብረህ ትከስራለህ ።
አንተ አላህ ፀጋውን ያንቧቧብህ ባሪያ ሆይ የተኛ መሰሎ የተሸነፈውን ማንነትህን ቀስቅሰው ። ወደ ልቅናው አመላክተው ። የተዘጋጀለትን የክብር ልብስ አጥልቅ አንገትህን ቀና አድርግ በለው ። አሁኑኑ ወደ ራሱ ተመልሶ ከብርሃን ያራቀውን አለማወቅ አውልቆ ጥሎ ወደ ማወቅ ለመሸጋገር እንዲወስንና ወደ ተግባር እንዲገባ ሰበብ ሁነው አላህ ይርዳህ ።
https://t.me/bahruteka